Translate

Monday, September 9, 2013

“በስልጣን ምክንያት ህወሓት ለሁለት የተከፈለ ይመስለኛል” – አቶ ገብሩ አስራት (ቃለ ምልልስ)

ሐገር ቤት የሚታተመው ሎሚ መጽሔት አቶ ገብሩ አስራትን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አነጋግሯቸዋል። ዘ-ሐበሻ ለአንባቢዎቿ ይጠቅማል በሚል እንደወረደ አቅርባዋለች።
246522dcb1a158f71378732826ሎሚ፡- ባለፈው መቀሌ ላይ “አረና” ሕዝባዊ ስብሰባ አከናውኖ ነበር፡፡ የነበረው ሁኔታ በአጠቃላይ ምን ይመስል ነበር;
አቶ ገብሩ፡- እንግዲህ የመቀሌውን ስብሰባ ከሁለት ጉዳዮች አንፃር ልንመለከተው እንችላለን፡፡ አንዱ ሕዝቡ እንዴት እንደተቀበለው ስብሰባውን … ሁለተኛው መንግስት ወይም በክልሉ ያለው ፓርቲ ስብሰባው እንዳይካሄድ ያደረጉትን ጫና በተመለከተ መመልከት ይቻላል፡፡ እንግዲህ አስቀድሜም መንግስት ስብሰባው እንዳይካሄድ የፈጠረውን ጫና ነው የማየው፡፡ እንግዲህ ትግራይ ውስጥ ገዢው ፓርቲ ህወሓት ነው፡፡ ህወሓት ከእሱ ውጭ ሌላ ፓርቲ እዛ ቦታ ላይ እንዲንቀሳቀስ ፍላጐት የለውም፡፡
ይህም ባፈለው 2002 ዓ.ም. በተካሄው ምርጫ ጠ/ሚ መለስ ትግራይ ውስጥ ምንም አይነት ክፍተት መኖር የለበትም፣ ምንም አይነት የሀሣብ ልዩነት መኖር የለበትም ብለው የተናገሩበትና በርካታ ስድቦች የተሰነዘረበት በተለይም በ”አረና” ላይ በርካታ ስድቦችን ያወረዱበት ጊዜ ነበር፡፡ እንግዲህ አሁን ያለው አመራርም የእሣቸውን “ሌጋሲ” ፈለግ እከተላለሁ የሚል ስለሆነ አካሄዱ ተመሳሳይ ነው፡፡ በትግራይ ውስጥ ምንም አይነት የፖለቲካ አስተሳሰብ እንዲኖር አይፈልግም፡፡ በህገ መንግስትም ፣ በቃልም ተቃዋሚ ቢኖር አንጠላም ሊሉ ይችላሉ፡፡ ዋናው ስጋታቸው በአካባቢው የተለየ ሀሣብ ፣የተለየ አመለካከት ፣ የተለየ አደረጃጀት እንዳይኖር ስጋትና ጭንቀት ያለባቸው ስለሆነ አጠቃላይ ድርጅቱን በእነሱ ስር የተደራጀ ሲቪክ ማህበረሰብ፣ የመንግስት ድርጅቶችን አደራጅተው ነው አንድ ፓርቲ በዛ አካባቢ ስብሰባ እንዳያካሂድ የሚያደርጉት፡፡ ባለፈው ጊዜም ስብሰባ ስናካሂድ እንደውም እነሱ በሚመሯቸው ድርጅቶች ፣ ኩባንያዎች /ኢፈርት/ ሠራተኞችን ሰብስበው በዚህ ስብሰባ ላይ መገኘት ከጠላት ጋር እንደማበር ይታሰባል ብለዋቸዋል፡፡ እና ስለዚህ ስራ ለማግኘት አትችሉም፣ ስጋት ላይ ትወድቃላችሁ ፣ ከጠላት ጋር የመተባበር ያህል አድርገን ነው የምናየው ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡
ይህንን ካሉ በኋላም በዚህም አላበቃም በኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ መሠረት እንደተፈቀደው ማንም ፓርቲ ሊቀሰቅስ ይችላል፡፡ መቀስቀስ የማይችለው በትምህርት ቤትና በቤተ እምነት ቦታ ውስጥ እንጂ በሌላ ቦታ ድምፅ ማጉያ ተጠቅሞ መቀስቀስ ይችላል የሚል ነገር አለ፡፡ መቀሌ ላይ ግን ሌላ ህግ አውጥተዋል ወይም አውጥተናል ነው የሚሉት፡፡ እኛ ግን አላየነውም፣ ህጉ ምንድነው የሚለው ማንኛውም እንቅስቃሴን ማጉያ ተጠቅሞ መቀስቀስ አይቻልም ነው የሚሉት፡፡ ይሄ እንግዲህ ከሀገሪቱ ህግ ፣ ከፌዴራል ህግ ጋር የሚጣረዝ ህግ ነው፡፡ ህግም ቢሆን …read more,,http://www.zehabesha.com/amharic/archives/7183

No comments:

Post a Comment