Translate

Saturday, May 25, 2013

ሰማያዊ ፓርቲ :-የፖለቲካ መብረቅ!!

ተጻፈ በምንሊክ ሳልሳዊ
semayawiወያኔ ሆይ እኔ ምንም አልልም…ሃሃሃሃ…በፓርቲሽ ውስጥ ሰማይዊ ፓርቲን በተመለከተ የተፈጠረው ውዥንብር እስከዛሬ አለመታየቱ አሊያም በቅንጅት ሜዳ ላይ አለመፈጠሩ አንድም መለስ ዜናዊ አለመኖሩ ይሆናል አሊያም መውደቂያሽ መድረሱን እየጠቆመ ይሆናል እኔ ግን ምንም አልልም ..መረጃውንም ዘግየት ብየ ከሰልፉ በኋላ እለቀዋለሁ ::ግን አንድ አጠር ያለ ነገር ልል ነው ከተለመደው ሳልወጣ ማለት ወያኔ በፖለቲካ መብረቅ እንደተመታች ልናገረው :;
ወገን ብዙ እየተባል ነው ስለሚባለው ትጠን አንዳንድ ፖለቲካ ሳያኝኩ የሚውጡ ዲያስፖራዎች ግን ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍ ቀኑ መዘዋወሩን እንደ ፖለቲካ ክስረት ያዩት ለምን እንደሆን አይገባኝም ::ቢገባኝም እነሱ ምን አገባቸው ኪሳራ ብለው ፈርጠም አሉ ይህን የፈጠሩት ደሞ መሃል ሰፋሪ ሰኣቱን ጠብቀው ከባለድል ሊቀላቀሉ የሚፈልጉ ባለሟሎች የመኖሪያ ፍቃድ የማሳደሻ ሰነድ እንዳዘጋጁ በሰው ሃገር መቀበሪያ የገዙ ሲሆኑ እነሱም እነሱ እነሱም በፖለቲካ መብረቅ ተመተዋል::

እንዲሁም በሃገር ቤት የሉ የፖለቲካ ብስለት የሌላቸው ጠባብ ቡድኖች እና ግለሰቦች ድጋፋቸውን መንፈጋቸው ፖለቲካችን አለማደጉን ያመለከተ ሲሆን አቋም እና መመሪያ እንዲሁም ማኒፌስቶ የሌላቸው እነዚህ በአዛውንቶች እና በተሳዳቢዎች የተሞሉ ቡድኖች 22 አመት ሲንዘላዘሉ የቆዩ የመንግስት አጋር ምሁራን ተቃዋሚ ነን ባዮች የተደለዙ የፖለቲካ አሽከሮች የሰልፉን መርዘም ሲሰሙ የት እንደተደበቁ እንኳን ሳይታወቅ ለድጋፍ ያልጮሁት ሰልፉ የከሸፈ በማለት መንጣጣት ለራሳቸው የፖለቲካ ክስረት መሆኑን አላወቁትም…እነዚህም በመብረቁ ተፈንክተዋል::
የፖለቲካ ሚዛኖች ወደ ሰማያዊ ፓርቲ አጋድለዋል:: የመንግስት እብሪት በፓርቲው እንቅስቃሴ ተፈትኗል :: የሰማያዊ ፓርቲ እንቅስቃሴ እና ጫና መንግስትን አስደንግጦታል:: ከባድ ሽንፈቱን ያሳያል:: ጠረጴዛ ላይ ጥለውለት ለመጡት እና አንቀበለውም ላለው ደብዳቤ መልስ መስጠቱ ምን ያህል የፖለቲካ ኪሳራ ውስጥ ወያኔ መግባቱን ያመለክታል …በፖለቲካ ቋንቋ ሲዘረዘር ….አንድ ወዳጄ ስናወራ ከሃገር ቤት እባክህ አላመንኩትም ሰማያዊን …እንደ ልደቱ ኮስማና አጋር ፓርቲ ዳጎስ ያለ ጉርሻ ወስዶ እንዳይሆን የሚዘባርቀው አለ ….አንዱም በፌስቡክ ግድግዳዬ ላይ ቾኩን ጣል አደረገ…አዎ መጠራጠሩ አይከፋም ..ሰልፉ ቢሰረዝ ኖሮ መጠራጠር ባልከፋ ስለተዘዋወረ  ዋናው ለአለማቀፍ ህብረተሰብ በአለማቀፍ ሚዲያ መተላለፉ ነው::..እነሆ..”50ኛ አመት የአፍሪካ ህብረት ልደትን ባከበረችው ኢትዮጵያ ክብረበዓሉን ተከትሎ የአዲስ አበባ ህዝብ በመንግስት ላይ ተቃውሞውን አሰማ::”…ይህንን ያስቡ …እና ስለ ኢዴፓ እና ዳጎስ ስለለው ጉርሻ የተጠራጠራቹህ በፖለቲካ መብረቅ ሊትመቱ ስለምትችሉ ሽሹ::
ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ ጊዜያት በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች የተነሳ ሰላማዊ መሆናቸው የወያኔ ጁንታ የሚጠልፍበት ወይም አደጋ ሊጥልበት የሚችልበት ምክንያት ስላጣ እና እንዲሁም በውስጡ የተከሰተው አጣብቂኝ ድርጅቱን በአባሎቹ ኢ-ዲሞክራሲያዊ እያሰኘው መምጣቱ በምርጫ ላይ የተከሰቱ ሂደቶች የሙስሊሙ ህብረተሰብ የትግል ችቦ መቀጣተል ወያኔን እግሩን ስላሰሩት ያለው እድል በሂደት ለማሻሻል መጓዝ እና በትእግስት እየጠለፉ መጣል ነው ::
የዚህ ሰልፍ መፈቀድ ከህዝብ ሮሮ ጋር ተዳምሮ ሊፈጥር የሚችለውን የፖለቲካ ፍጆታ ብቻ ያየው የወያኔ ድብርት ፖለቲካ በመብረቅ ተመቷል;; እነሱ ያሰቡት ወያኔ ዲሞክራሲያዊ መብቶችን መፍቀድ ጀምሯል ብሎ ህዝቡ የሚረጋጋ መስሏቸው ነው ሆኖም የአፈና እና የአፈሳ ስራዎችን የሚሰራው የፖሊስ እና የደህንነት ሃይል አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ መቃጣቱን ጅምሩ ያስረዳል ይህ ደሞ የርስ በርስ አለመነባበብ በወያኔ ባለስልጣናት መሃል አለመኖሩ ያሳያል:: እያንዳንዱ ባለስልጣን በገዛ ፍቃዱ እንደፈለገ ፖሊሱን እያዘዘው ባለበት በዚህ ወቅት ከከንቲባው ጋር አምባጓሮ መፍጠር እንደማይፈልግ ያመለክታል::ይህም ሳያውቁት የወረደባቸው መብረቅ መጥፊያቸው እንደተቃረበ ያመለክታል::
በአጠቃላይ ይህ ለወያኔ የፖለቲካ ክስረት ውስጥ እንዲገባ ያደረገው የሰላማዊ ተቃውሞ ሰልፍ ዝግጅት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሊደግፈው የሚገባ ጉዳይ ሲሆን ሃገር ቤት ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በዚህ ህዝባዊ ጥያቄ በሚቀርብበት ሰልፍ ላይ አብረው በመተባበር መስራት እና የአምባገነኖችን ገመድ መበጣጠስ እንዳለባቸው ለመናገር እወዳለሁ ::ወያኔ መግቢያ ባጣበት እና አጣብቂኝ ውስጥ ባለበት በዚህ ሰአት ላይ እያንዳንዳችን ተባብረን ሳንጠላለፍ በመተሳሰብ ይህንን የሰው በላ ማፊያ ቡድን ማስወገድ የእያንዳንዳችን ድርሻ ነው::
አንድ ነገር ግን ይወቁ:-የፖለቲካ ሚዛኖች ወደ ሰማያዊ ፓርቲ አጋድለዋል:: የመንግስት እብሪት በፓርቲው እንቅስቃሴ ተፈትኗል :: የሰማያዊ ፓርቲ እንቅስቃሴ እና ጫና መንግስትን አስደንግጦታል:: ከባድ ሽንፈቱን ያሳያል:: ጠረጴዛ ላይ ጥለውለት ለመጡት እና አንቀበለውም ላለው ደብዳቤ መልስ መስጠቱ ምን ያህል የፖለቲካ ኪሳራ ውስጥ ወያኔ መግባቱን ያመለክታል …:: አወቁ???
ቅስቀሳው ይቀጥል:: የተቃውሞ ሰልፉ ግንቦት 25/ 2005 አ.ም. በኢትዮ-ኩባ አደባባይ ከጠዋቱ 4 ሰአት- 8 ሰአት

No comments:

Post a Comment