Translate

Tuesday, May 21, 2013

በአዲስ አበባ በባልና ሚስት የተደረገ ታይቶና ተሰምቶ የማያቅ ዘግናኛ ድርጊት


‹‹ጉዳዩ የተፈፀመው በአዲስ አበባ ጎተራ ኮንዶሚኒየም ቤት ውስጥ ነው፡፡ ባል እና ሚስቱ የህክምና ዶክተሮች ለብዙ ዓመታት
አብረው በሞቀ ትዳር ውስጥ ቆይተው ነበር፤ ከትዳራቸውም አንዲት የ9 ዓመት እና አንዲት የ6 ዓመት ልጆችን አፍርተዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለሀይማኖታቸው የተለየ ፍቅር በማሳደር ከፍተውት የነበረውን ክሊኒካቸውን ዘግተው ራሳቸውን አስገዝተው ሲኖሩ አንድ ሀሳብ ብልጭ አለላቸው፡፡
ይሄውም እንደ ጌታ እየሱስ 40 ቀን እና 40 ሌሊት ለመፆምና ለመፀለይ ቆርጠው ተነሱ! ለልጆቻቸውም ፓስታ ምናምን ገዝተው ፆሙን ጀመሩ፤ ልጆቻቸውም ከቤት እንዳይወጡ ቆለፉባቸው፡፡ የልጆቹን ምግብ የሚያበስለው አባትየው ነበር (ትንሽ ትንሽ ቀምስ ነበር አሉ)፤ የሆነ ሆኖ የልጆቹ ምግብ በ25ኛው ቀን አለቀ ልጆቹም በርሃብ ደከሙ፤ እነ ዶክተር ግን ፆማቸውን ቀጥለዋል፡፡

 በ36ኛው ቀን ትልቋ ልጃቸው ከእናቷ ጋር መተኛት አቁማ ብቻዋን ሶፋ ላይ መተኛት ጀመረች፤ ምክንያቱም እናቷ የተለየ ሽታ በማምጣቷ፡፡ ይሄን ጉዳይ ለአባቷ ብትነግረውም አባቷ እርሱም ስለደከመ እናቷ አልቻለም፡፡ ይህችው ልጅ በ40ኛው ቀን ‹በረሃብ ሞትን› ብላ በመስኮት ስትጣራ የሰማች የጎረቤት ልጅ ለፖሊስ በመጠቆም ፖሊስ ቤቱን ፈልቅቆ ሲገባ እናት በረሃብ ሙታለች፤ አባት ነብሱ ባትወጣም ራሱን አያውቅም፤ ሁለቱ ህፃናት ደግሞ በረሃቡ ምክንያት በአጥንታቸው ቀርተው ተገኙ፡፡››
source: yehabesha.com

No comments:

Post a Comment