Translate

Thursday, May 23, 2013

ኢሳት ጋዜጠኞች ጆሮ ላይ ስልክ ለምትዘጉ ባለስልጣኖች ማሰጠንቀቂያ


እስከ ነጻነት

Ethiopian Satellite Television (ESAT)መረጃ የማግኘት መብት የስብዓዊ መብት ዋናው መሰረት ነው፡ መረጃ የማግኘት መብት ዋናው የሰብዓዊ መብት ምሰሶ መሆኑን የሃገራት ደርግ (League of Nations) የደነገገው በ1946 ዓ.ም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ነበር፡ ያደጉ ሃገራት ይህንን መብት በሚገባ ይጠቀሙበታል፡ ገልብጦ መጻፍ እንጂ ማንበብ የማይችልው የወያኔ ዘረኛ ስርዓትም ይህንኑ መብት በህገመንግስቱ ላይ አሰቀምጦታል። ለነገሩ ያላሰቀመጠው ነገር የለም ግን ማን አንብቦት ተግባራዊ ያደርገዋል እንጂ። ተግባራዊ እየሆነ ያለው ዘርን ለማጥፋት የተወጠነው የጫካው ህጋቸው ብቻ ነው።

ይህን እዚሁ ላይ ላቁምና ወደተነሳሁበት ልመለስ፤ የውነትም ይሁን የውሸት ስልጣን ይዛችሁ መረጃ ስትጠየቁ ስልክን ጋዜጠኛ ጆሮ ላይ የምትዘጋ፤ የምትዘጊ፤ የምትዘጉ ግለሰቦች ወንጀል መሆኑን ካልተገነዘባችሁ እንድትገነዘቡት ላስታውሳችሁ አወዳለሁ፡የእሳት ጋዜጠኛ መረጃ ሲጠይቃችሁ ጆሮው ላይ ስትዘጉ፡ የዘጋችሁበት መሳይ፤ ፋሲል፡ ሲሳይ ወይም፡አንድ የእሳት ጋዜጠኛ ጆሮ ላይ ሳይሆን የ90 ሚሊየን የኢትዮጵያ ህዝብ ጆሮ ላይ መሆኑን ልብ ካላላችሁ ላስታውሳችሁ፡ ለያንዳንዷ ለዘጋችሗት ስልክ የምትጠየቁ መሆኑን ደግሜ ደጋግም ላስገነዝባችሁ እወዳለሁ።
በእርግጥ አማራ ነን ብላችሁ አማራ ህዝብን የምታስፈጁት፤ ኦሮሞ ነን ብላችሁ የኦሮሞን ደም የምታፈሱት፤ ኢሳ ሆናችሁ የኢሳን ህዝብ የምታስፈጁት ሌሎቻችሁም የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር ካድሬ ከላይ ተጭኖ እንደሚያዛችሁ አለም የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡ ምናልባትም ለእሳት መረጃ ለመስጠት የፍርሃት ቆፈን ቀፍድዷችሁ ሊሆን ይችላል። ፈቃደኝነቱ ኖሮ ችግራችሁ ፍርሃት ከሆነ መረጃውን ለሌላ ለምታምኑት ሰው አቀብላችሁ መረጃ የሰጣችሁትን ስው ስልክ ቁጥር ለእሳት ጋዜጠኛ ልትነግሩ ትችላላችሁ፡ ሲሆን ሲሆን አንድ የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር ጨባጣ ካድሬ እንደ አውራ ዶሮ ሲንቀባረርባችሁ እንደ ሲካካ ዶሮ እኔ እኔ እያላችሁ ከመሽቀዳደም በጋራ ማሰወገድ ትችሉ ነበር፡ይህ ባይሆን እንኳ የወገናችሁን ሰቆቃ እና የወያኔን ሚስጥራዊ ወንጀል ማጋለጥ ከናንተ የሚጠበቅ ትንሹ ተግባር መሆን ሲገባው ጋዜጠኛ ጆሮ ላይ ስልክ ትዘጋላችሁ።
እስኪ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ በተለይ አማራ ነን ያላችሁ የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር መጋዣዎች፤ አማራን ለማጥፋት በተግባር እቅዱ ላይ ነድፎ የሚንቀሳቀስ ድርጅት እናንተን እንደማይበላችሁ ማረጋገጫችሁ ምንድነው? መረጃውን እዚህ ላይ አንብቡት አሁን በሙስና ተብለው የታሰሩት በርግጥ በሙስና ነው? እናነተስ ነገ ወደቃሊቲ ላለመላካችሁ ዋስትናችሁ ምንድነው? ስለዚህ ቀኑ ሳይመሽ ወደ ህሊናችሁ ተመልሳችሁ ወደ ወገናችሁ ተደባለቁ። ይህ ጥሪ ላማራ ብቻ አደለም፤ ለኦሮሞ፤ ለሲዳማ፤ ለኦጋዴን፤ ለአፋር፤ ለሲዳማ፤ በአጠቃላይ ወያኔ በየቦታው የወዘፋችሁ ባለስልጣናትን ሁሉ ይመለከታል፡ ይህ ሁሉ ሳይሆን ቀርቶ፤ ጋዜጠኛ ጆሮ ላይ ስልክ እየዘጋችሁ የወያኔን ወንጀል ደብቃችሁ ቀኑ ከመሸ እያንዳንዳችሁ ከተጠያቂነት እንደማታመልጡ መረዳት አለባችሁ፡ ወያኔ እንኳን የናንተን ገመና ሊሸፍን የራሱን ገመና መሸፈን የማይችል የፍየል ጅራት መሆኑ አይናችሁን ካልጨፈናችሁ በስተቀር በግልጽ የሚታይ ጉዳይ ነው።
በህግ ስላላወቅሁ ነው የሚባል ነገር እንደሌለና ለሰራችሁት ወንጀል ሁሉ ተጠያቂ መሆናችሁን አስረግጬ እዚህ ላይ ላብቃ።
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ

No comments:

Post a Comment