Translate

Saturday, May 25, 2013

ሽፈራው ሽጉጤን ከሃላፊነታቸው ለማንሳት ወያኔ በሚስጥር እየሰራ ነው፤


shiferaw-shigute
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል የተከሰተው የፖለቲካ አለመረጋጋትና አለመተማመን ያሰጋው የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ አቶ
ሽፈራው ሽጉጤን ከሃላፊነታቸው ለማንሳት የሲዳማን ህዝብ የማሳመን ስራ ጀምሯል።ታማኝ ምንጮች እንዳሉት አቶ ሽፈራውን
እንዲተኩ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ታጭተዋል።
ባለፈው ወር በክልሉ በተካሄደ ግምገማ ፕሬዚዳንቱ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በኪራይ ሰብሳቢነትና በሙስና ተፈርጀው ለህግ
ተላልፈው እንዲሰጡ ሲወሰን “እኔ ከተከሰስኩ ወ/ሮ አዜብ መስፍንም መከሰስ አለባቸው” በማለት መልስ ሰጥተው ስብሰባውን
ረግጠው መውጣታቸውን የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በስፍራው የሚገኙትን ምንጮች ጠቅሶ መዘገቡ የሚታወስ ነው።
በክልሉ አብላጫ የህዝብ ብዛት ካለው የሲዳማ ብሔረሰብ የተወለዱት አቶ ሽፈራው፣ከስልጣናቸው ተወግደው ለፍርድ
እንዲቀርቡ ቢወሰንም ውሳኔው ተግባራዊ ያልሆነው በሁለት ምክንያቶች እንደሆነ መረጃዎች እየወጡ ነው።የመጀመሪያው
ምክንያት ፕሬዚዳንቱ በተገመገሙበት የሙስና ወንጀል የአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት መካተታቸው ሲሆን፣ሁለተኛው ደግሞ
የሲዳማ ህዝቦች ያምፃሉ በሚል ፍራቻ ነው።

“የሙስና መሸሸጊያና የሙስና እናት”በሚል ስያሜ የሚታወቁት የአቶ መለስ ባለቤትና የትግል አጋር ተካተውበታል በተባለው
የሙስና ወንጀል በኩል ከፍተኛ ቅሬታ ነግሷል።ፕሬዚዳንቱን አስመልክቶ ግን ለጊዜው ተግባራዊ እንዳይሆን የተያዘው ጉዳይ
በሚስጢር ቅድመ ሁኔታዎች እየተካሄዱበት ነው።
ጉዳዩን የሚከታተሉት ምንጮቻችን አቶ ሽፈራውን ህግ ፊት ለማቅረብና ከሃላፊነታቸው ለማባረር በመጀመሪያ የሲዳማን
ህዝቦች ማሳመን አግባብ ሆኖ ተገኝቷል።በዚሁ መሰረት ከላይ በወረደ ትዕዛዝ በወረዳ ደረጃ አቶ ሽፈራው በህዝብ እንዲጠሉና
ድጋፍ እንዲያጡ ለማድረግ የሚያስችል ዘመቻ ተጀምሯል።
“ማስተፋት”በሚለው የወያኔ ጥበብ በህዝብ እንዲጠሉና እንዲገለሉ ዘመቻ እየተካሄደባቸው ያሉት አቶ ሽፈራው በበኩላቸው
በሚያምኗቸውና እሳቸው በዘረጉት የሲዳማ መዋቅር አማካይነት ከፍተኛ ዘመቻ መጀመራቸው ታውቋል።ዘመቻው እሳቸው
ከተነኩ የሲዳማ ህዝብ ዳግም ወደ ሃላፊነት ሊመጣ ስለማይችል በጥንቃቄ እንዲጠባበቅ ነው።
ይህንን የተረዳው ወያኔ አቶ ሽፈራውን በሌላ የሲዳማ ተወላጅ ለመተካት ዝግጅቱን እያጣደፈ ይገኛል።በዚሁ መሰረት በጃፓን
አምባሳደር ሆነው እየሰሩ ያሉትን አቶ ማርቆስ ተክሌን የሲዳማ ህዝብ “መሪዬ”ብሎ እንዲቀበላቸው የ“የስር ለስር ”ስራ እየተሰራ
ነው።የሲዳማ ህዝቦች አቶ ሽፈራውን እየጠሉ አቶ ማርቆስን እንዲወዱ ለማድረግ እየተካሄደ ያለው ዘመቻ የሚከናወነው
በወረዳ የተለያዩ መዋቅሮች ላይ ባሉ የሲዳማ ብሄር አባላት አማካይነት በመሆኑ ሚስጥር የተባለውን ጉዳይ ገሃድ
እንዳያወጣውና ብጥብጥ እንዳይፈጠር ስጋትም አለ።
በ 1993 ዓ ም ውህዳኑን በመደገፋቸው ክልሉን ከጀርባ ሆነው ይመሩ ከነበሩት አቶ ቢተው በላይ ጋር በሙስና ወንጀል ሰበብ
የታሰሩት አቶ አባተ ኪሾ ከሰባት ዓመት በሁዋላ ያለ ወንጀል በነፃ የተለቀቁት የሲዳማ ህዝብ ባቀረበው ማስጠንቀቂያ ነበር።
በተመሳሳይ ዜና የከተማ መሬት ወረራ ጋር በተያያዘ እስከ የካቲት 30 ቀን 2004 ዓ ም ድረስ ከሁለት መቶ ሃምሳ የሚጠጉ ሰዎች
ታስረው ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ተዛውረዋል።ከከተማ አስተዳደር፣ማዘጋጃ ቤቶችና የዞን አስተዳደሮች ተለቅመው የታሰሩት
ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመዋጋትና ህገወጥ የመሬት ደላሎችን እንቅስቃሴ ለመግታት በሚል ነው።
“ህገወጥ የመሬት ደላሎችን ለመግታት”ተብሎ በተካሄደ ግምገማ በመድረክ በዋናነት የክልሉን መሬት እየቸበቸቡ ያሉት
የህወሃት ሰዎች እንደሆኑ ቢገለፅም የተወሰደው ርምጃና እስር እነሱን ባለማካተቱ በግምገማው ላይ በግልፅ የተናገሩትን ክፍሎች
ስጋት ላይ እንደጣለ ምንጮቻችን ያነጋገሩዋቸው የድርጅት አባላት ተናግረዋል።
እንዲህ ያለው ኢሰብአዊ ድርጊት የሚፈፀመው ኢህአዴግ በቅርቡ ያወጣውን አፋኝ የከተማ መሬት ሊዝ አዋጅ ለመተግበር
መሆኑ ዘግይቶ እንደገባቸው የሚገልፁት የግምገማው ተሳታፊዎች “እንዲህ አይነቱ ተግባር አቶ መለስ አገር ትግራይ
የማይተገበር ነው”ሲሉ ቅሬታቸውንና ተቃውሟቸውን ገልፀዋል።
በዚህም ሳቢያ የተፈጠረው ቅራኔና አለመግባባት፣ወደ ፖለቲካ አለመተማመን መሸጋገሩን ያስረዱት ምንጮች፣ከ 45 በላይ ብሄር
ብሄረሰቦች የሚኖሩበት የደቡብ ክልል በአንድ ተረግጦ በሞግዚት አስተዳደር አንዲተዳደር አድርጓል።ክልሉ የራሱ አስተዳደር
መዋቅር ቢኖረውም አሁን እየተመራ ያለው በህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ጥብቅ ክትትልና መመሪያ እንደሆነ ለማወቅ
ተችሏል።ስም ያልጠቀሱት ምንጮች እንዳሉት ወያኔ በደቡብ ክልል ሊገጥመው የሚችለውን ተቃውሞ በመገመት ሙሉ በሙሉ
የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ በስለላ መዋቅር ውስጥ ለማስገባት ከፍተኛ ገንዘብ እያፈሰሰ ይገኛል።አንዳንድ ጠንካራ ቀበሌዎች
ላይ ህዝቦችን በብድር፣በማዳበሪያና በምርጥ ዘር አቅርቦት እየቀጣ ይገኛል።
(በመምህሩ መልካሙ)   source: amnewsupdate.file

No comments:

Post a Comment