Translate

Saturday, September 9, 2017

መንግስት ከህወሓት የንግድ ድርጅቶች የመኪና ግዢ ሊፈጽም ነው

Image may contain: 4 people, people smiling, outdoor
መንግስት ከህወሓት የንግድ ድርጅቶች የመኪና ግዢ ሊፈጽም መሆኑ ታወቀ፡፡ ሰሞኑን በስራ ላይ የዋለው የመንግስት መመርያ አስቀድሞ የነበረውን የመኪና ግዥ ስርዓት አፍርሶ በአዲስ ተክቶታል፡፡ በአዲሱ የመንግስት መኪና መግዣ ህግ እና ደንብ ስርዓት መሰረት፣ ከዚህ በኋላ መኪና መገዛት ያለበት ከውጭ ሀገር ሳይሆን ከሀገር ውስጥ እንዲሆን ተደንግጓል፡፡ አሁን ባለው የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ መኪና የመገጣጠም እና የማምረት ኢንዱስትሪውን ተቆጣጥረው የያዙት የህወሓት የንግድ ድርጅቶች በመሆናቸው፣ መንግስት መኪና ሊገዛ የሚችለው የግድታ ከህወሓት ድርጅቶች መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡


ኤፈርት የሚባለው የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የንግድ ድርጅት በውስጡ በርካታ የንግድ ድርጅቶችን የያዘ ሲሆን፣ የመኪና ማምረቻ እና መገጣጠሚያም አንደኛው የድርጅቱ የንግድ አካል ነው፡፡ መስፍን ኢንደስትሪያል የሚባለው የህወሓት ድርጅት መኪና በማምረት እና በመገጣጠም ስራ ላይ የተሰማራ ሲሆን፣ በመንግስት በኩል የሚደረጉት የመኪና ግዥ ውሎች በአብዛኛው ከዚህ ድርጅት ጋር የሚፈጸሙ ናቸው፡፡ ህወሓት የግል መኪና አምራች እና መገጣጠሚያ ድርጅቶችን አስቀድሞ ከገበያ በማስወጣቱ፣ ኢንዱስትሪውን ለብቻው እንዲቆጣጠረው አስችሎታል፡፡

ከመስፍን ኢንዱስትሪያል ቀጥሎ በመኪና መገጣጠም እና ማምረት ዘርፍ በሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የገበያ ድርሻ ያለው፣ የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ነው፡፡ ኮርፖሬሽኑ በመከላከያ ሚኒስቴር ስር ይቋቋም እንጂ በጠቅላላ ኃላፊዎቹ የህወሓት ጄኔራሎች ሲሆኑ፣ ከድርጅቱ የሚገኘውም ገቢ በዘረፋ መልክ ወደ ህወሓት ባለስልጣናት ኪስ እንደሚገባ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከዚህ በኋላ መኪና መግዛት ያለባቸው ከሀገር ውስጥ እንዲሆን በሚያዘው ህግ መሰረት፣ አብዛኞቹ ግዢዎች ከሁለቱ የህወሓት ድርጅቶች እንዲፈጸሙ እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የህወሓት የንግድ ድርጅቶች፣ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ በጅምር ላይ የነበሩ የግል የመኪና መገጣጠሚያ ድርጅቶችን የንግድ ፈጠራ ሀሳብ በመስረቅ ድርጅቶቹን በኃይል ከገበያ አስወጥተዋቸዋል፡፡

No comments:

Post a Comment