Translate

Wednesday, September 27, 2017

የቀድሞ የአማራ ክልል የደህንነት ኃላፊ በርካታ ምስጢሮችን ዘረገፉ | ልደቱ አያሌውን ጨምሮ ማታ ማታ ስለሚታሰረውና ቀን ሰዎችን ስለሚያሳፍነው የግንቦት 7 ‘አባል’ የሚናገሩት አላቸው

“የአገር ውስጥ ደህንነት ሀላፊ የነበረው ወልደስላሴ በደህነት ውስጥ ቅጥል ስሙ ኦሮሞ ገዳይ እንደውም የሕወሃት አባላት የሆኑት …ገዳይ ነው የሚሉት”

“ዒላማ የተደረጉ እስረኞች መርዝ እንዲሰጣቸው ይደረጋል የውሻ መግደያን ጨምሮ ሚሰጡት መርዞች ሶስት አይነት ናቸው” 

“የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ባለሃብቶች የንግድ ተቋመኖቻቸውን፣ህንጻዎቻቸውን ለደህነቱ ድብቅ ማሰቃያነት ይፈቅዳሉ ለምሳሌ በጎንደርና በባህርዳር ካሉት ጥቂቶቹን በምሳሌ ብጠቅስ…”

“አቶ ልደቱ ከመጀመሪያም የደህነቱ አባል ነበር።  ልደቱ ብቻ ሳይሆን ለደህነት መስሪያ ቤቱ እንዲሰሩ የሚመለመሉ የተቃዋሚ መሪዎችና አባላት አሉ። አንዳንዶቹ ብዙ ካሳሰሩ በሁዋላ እኔኔም እንዳይነቃብን እሰሩኝ ይሉ ነበር”

“የአዲስ አበባ የግንቦት ሰባት አባል የነበረ ከግንቦት ሰባት የተሰጠውን ተልዕኮ ቀን ቀን ከደህነቱ ጋር ተገናኝ የተባለውን እየተገናኘ ሲያሳፍን ይቆይና  ማታ ማታ እስር ቤት ያድር ነበር በሁዋላ ተጠቅመው ሲጨርሱ ግን… በአገር ውስጥም በውጭም አሉ ተቃዋሚዎች ራሳቸውን መፈተሽ አለባቸው…”

“ሰዎች የሚታፈኑባቸው የደህነቱ ድብቅ እስር ቤቶች ብዙ ናቸው”

“የአማራና የኦሮሞ የደህነት አባላት የተለየ ሀሳብ ስላቀረቡ ብቻ በራሱ በደህነቱ ተመልሰው ሳይለቁና ምስጢር ሳያወጡ ይገደላሉ ።ለምሳሌ የባሌ ልጅ የነበረው …በሚበላው ምግብ ተመርዞ ተገሏል”

“የደህነቱ ድብቅ እስር ቤቶች መካከል ጥቂቶቹ ን ለመጥቀስ ያህል በባህር ዳር ኦርፖርት ጀርባ በጎንደር…”

“ከምርጫ 97 በፊት የኦብኮ አባል የነበረችው በፖለቲካ ንቁ ተሳታፊ የነበረችው ሴት በደህነቱ ታፍና እዚህ ለመግለጽ የሚከብደውን ከፈጸሙባት ቡዋላ ያንን በቪዲዮ አንስተው መልሰው እነ ዶ/ር መረራን እንድታወግዝ ነበር ያደረጉዋት ብዙ ሳትቆይ ግን በተፈጸመባት ተሸማቃ ራሱዋን ከፖለቲካው አገለለች”

“እነዚህና ሌሎችን ምስጢሮች ያብራሩት አቶ አያሌው መንገሻ በስልጣን ላይ ባለው አገዛዝ የደህነት /ቤትየአማራ ክልል የደህነት ቢሮ ሀላፊነትን ጨምሮ  በተለያዩ ሀላፊነቶች ያገለገሉ በወቅታዊ ጉዳይ ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ሰፊ ቃለመጠይቅ የተወሰደ ሙሉ ቃለ መጠይቁን  ያዳምጡት”

No comments:

Post a Comment