Translate

Friday, September 22, 2017

ወይዘሮ አዜብ መስፍን በድጋሚ ሙልጭ ያልኩ ደሃ ነኝ አሉ

 የቀድሞ የህወሓት መሪ አቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ምንም የሌላቸው ደሃ መሆናቸውን በድጋሚ ተናገሩ፡፡ በሀገር ውስጥ ከሚገኝ አንድ የሬድዮ ጣብያ ጋር ቃለ መልስል ያደረጉት ወይዘሮ አዜብ መስፍን፣ ስማቸው ከሙስና ጋር ተያይዞ መነሳቱም አግባብ እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ከሙስና ጋር በተያያዘ ስማቸው ሲነሳ እንደነበር ያስታወሱት ወይዘሮዋ፣ ይህ ጉዳይ ጋዜጠኞች ያናፈሱባቸው ወሬ እንጂ ትክክለኛ ነገር እንዳልሆነ በቃለ ምልልሳቸው ወቅት ተናግረዋል፡፡ ወይዘሮዋ ከዚህ ቀደም በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ ደሃ በመሆናቸው ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት የእሳቸውን እና የባለቤታቸውን ደሞዝ አጠራቅመው እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
‹‹በሙስና የሚጠረጠር ሀብት ካለኝ ምድረ ጋዜጠኛ ያጋልጥና የኢትዮጵያ ህዝብ ይውረሰው፡፡›› በማለት የተናገሩት ወይዘሮ አዜብ መስፍን፣ እንዲህ ዓይነቱ ወሬ የሚናፈስባቸው ለምን እንደሆነ ግራ እንደሚያጋባቸውም አክለው ገልጸዋል፡፡ ወይዘሮ አዜብ ባለቤታቸው ከማለፋቸው አስቀድሞ በሰጡት አንድ ቃለ ምልልስ ላይ፣ ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት እሳቸው እና ባለቤታቸው የሚያገኙትን የመንግስት ደሞዝ እያጠራቀሙ እንደሆነ ተናግረው ነበር፡፡ ሆኖም ከወይዘሮ አዜብ ሶስት ልጆች ሁለቱ ማለትም ሰምሃል መለስ ዜናዊ እና ሰናይ መለስ ዜናዊ በአሜሪካ እና በእንግሊዝ በሚገኙ ውድ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሩ ናቸው፡፡

ባለቤታቸው በስልጣን ላይ በነበሩበት በአንድ ወቅት፣ ቀዳማይ አመቤት የነበሩት ወይዘሮ አዜብ መስፍን፣ በአንድ ወቅት ለተወሰኑ የአፍሪካ ቀዳማይ እመቤቶች በነፍስ ወከፍ እስከ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ወርቅ ገዝተው በስጦታ መልክ ሰጥተው ነበር፡፡ የህወሓት ንብረት የሆነውን ኤፈርት እያስተዳደሩ የሚገኙት ወይዘሮ አዜብ፣ ከእግር ጥፍራቸው እስከ ራስ ጠጉራቸው ድረስ በሙስና የተጨማለቁ ስለመሆናቸው ከበቂ መረጃ ጋር ሲነገር ቆይቷል፡፡ ሆኖም ከህወሓት የበላይነት አንጻር እሳቸውን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው ባለስልጣናትን ደፍሮ በሙስና የጠየቃቸው አካል የለም፡፡

No comments:

Post a Comment