
‹የክርስቶስ አንዲት በግ መከራን ስትቀበል ከማይ እኔ የበጉ እረኛ መከራ መቀበልን እመርጣለሁ›
ይህንን የተናገረው ዮሐንስ አፈወርቅ ነበር፡፡ የቁስጥንጥንያዋ ንግሥት አውዶቅስያ የአንዲት ክርስቲያን ምእመንን መሬት ወስዳ ባሰቃየቻት ጊዜ ለተግሣጽ የተናገረው ነው፡፡ እንዳለው አልቀረም አውዶቅስያ ባደረሰችበት መከራ ተግዞ በዚያው ሞትን ተቀብሏል፡፡



የኢትዮጵያ ህወሓት ሰራሹ “ፌደራሊዝም” ወደ ተፈራው ቀውስ እየተንደረደረ መሆኑንን የሚያሳዩ የዜና ዘገባዎች የተሰሙት ገና ከጅምሩ ነበር። በርካታ ባለሙያዎችና የተቀናቃኝ ፖለቲካ መሪዎች በተደጋጋሚ ስጋታቸውን ቢገልጹም ተቀባይነት ሊያገኙ ባለመቻላቸው የጎሣና የብሄርተኛነት በሽታ እያደር ኢትዮጵያን እየበላት አሁን ያለችበት ደረጃ አድርሷታል።
የቀድሞ የህወሓት መሪ አቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ምንም የሌላቸው ደሃ መሆናቸውን በድጋሚ ተናገሩ፡፡ በሀገር ውስጥ ከሚገኝ አንድ የሬድዮ ጣብያ ጋር ቃለ መልስል ያደረጉት ወይዘሮ አዜብ መስፍን፣ ስማቸው ከሙስና ጋር ተያይዞ መነሳቱም አግባብ እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ከሙስና ጋር በተያያዘ ስማቸው ሲነሳ እንደነበር ያስታወሱት ወይዘሮዋ፣ ይህ ጉዳይ ጋዜጠኞች ያናፈሱባቸው ወሬ እንጂ ትክክለኛ ነገር እንዳልሆነ በቃለ ምልልሳቸው ወቅት ተናግረዋል፡፡ ወይዘሮዋ ከዚህ ቀደም በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ ደሃ በመሆናቸው ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት የእሳቸውን እና የባለቤታቸውን ደሞዝ አጠራቅመው እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ገና ከመነሻው በበረሃ ያወጣው ፕሮግራሙ በግልጽ እንደሚያመለክተው የህወሓት ዋንኛ ዓላማ ኢትዮጵያን አዳክሞና በጎሣ ከፋፍሎ ትግራይን ታላቅ በማድረግ ሪፑብሊክ መመሥረት ነው። ባለፉት 26 ዓመታት ይህንን ለማሳካት በኢትዮጵያ ውስጥ ያልፈነቀለው የጎሳ ድንጋይ የለም፤ ያላጋጨው ሕዝብ፤ ያላጋደለው ወገን የለም፤ ትግራይን ሳይጨምር!

ሳራ ከሞላ አስገዶምና ከጓደኞቹ ጋር በመሸታ ቤት
የውጩን ንግድ በሞኖፖል ይዘውት የነበሩት የአባይ ልጆች በአሁን ሰዓት በአሜሪካን ሃገር ውስጥ እንደሚገኙ የተጠቆመ ሲሆን ከሚኖሩበት ስፍራ ሰው በቀላሉ እንዳያጘኛቸው ማህበራዊ ገጾቻቸውን እና ስልኮቻቸውን አጥፍተዋል።
(BBN) በምስራቅ ሐረርጌ ሜኢሶ በአንድ ትምህርት ቤት ላይ በተወረወረ ቦምብ በርካቶች ቆሰሉ፡፡ ከስፍራው የተገኘው መረጃ እንደጠቆመው፣ ቦምቡ የተወረወረው በአካባቢው ጥቃት እያደረሰ በሚገኘው የሶማሊያ ክልል ልዩ ኃይል አማካይነት ነው፡፡ የሶማሊያ ክልል ልዩ ኃይል፣ ባለፉት ተከታታይ ቀናት በምስራቅ ሐረርጌ ሜኢሶ በጦር መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ሲፈጽም ቆይቷል፡፡ ከኦሮሚያ ክልል መንግስትም ሆነ ከፌደራሉ መንግስት ምንም ዓይነት ከለላ ያላገኘው የአካባቢው ነዋሪ፣ ባለው አቅም ራሱን ከጦሩ ለመከላከል የአልሞት ባይ ተጋዳይ ትግል እያደረገ ይገኛል፡፡