Translate

Wednesday, April 30, 2014

ዓባይ እንደ ዋዛ–ኢትዮጵያዊነትን አጥፍቶ ዓባይን ለመታደግ ይቻላልን?

አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ክፍል ሁለት

Click here for PDF

“ውኅ እየጠማው ያባዪን ልጅ
እሚያዘጋጅለት ቢጠፋ

እሚያበጃጅ ለልማት የሚያመቻች ዓባይን
አኮላሽቶለት ፈንጂውን”

ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው፤ ዐባይ–ፈንጅ የቀበረ ውሃ
ኢትዮጵያ ታላቅና ሃብታም ለመሆን የምትችል አገር ናት። የተፈጥሮ ሃብቷ፤ አቀማመጧና የሕዝብ ስርጭቷ ለታላቅነቷ የማይገኙ ምሰሶዎች (Social Pillars) ናቸው። ሆኖም፤ ይህ የአገርና የማህበረሰብ ታላቅነት መሰረት ጎሳዊና አምባገነናዊ የሆነ ስርዓት ባመጣው ጦስና ቀውስ እየባከነ ነው። ህወሓት ከተመሰረተበት ጀምሮ የተካውን መንግሥትና ሌሎችን በማዋረድ፤ በማጋለጥ፤ በማጥላላት፤ በማሰር፤ በመግደልና ከሃገር በማባረር ሃያ ሶስት ዓመት ገዝቷል። የጥቂቶችን ኪስ በሚያሳፍር ደረጃ ሞልቶ፤ ቢያንስ ሃያ አምሥት ቢሊዮን ዶላር ከሃገር ተዘርፎ ወደ ውጭ ሃብታም አገር ባንኮች እንዲዘዋወር አድርጓል። ይኼን ሲያደርግ ደጋግሞ የሚነግረን ተግባሩ ሁሉ ለጭቁን ሕዝቦች፤ ለድሃዎች ጥቅም የሚል ፕሮፓጋንዳ እየተጠቀመ ነው። ኢትዮጵያ የብዙ ምሁራን፤ ጠበብቶች፤ ሰራተኞች፤ አገር ወዳዶች ወዘተ አገር ብትሆንም ዛሬ የተማረና አገሩን ለማልማት የሚችል የተማረና የሰለጠነ የሰው ኃይል ድሃ ሆናለች። በሃያ አንደኛው መቶ ክፍል ዘመን ተቀባይነት የሌለው በኢትዮጵያ ተከስቷል።
ገዢው ፓርቲ ኢትዮጵያውያንን በጎሳ እየከፋፈለ፤ እያሰረ፤ እያባረረ፤ እያደኼየ፤ ኃይላቸውን እያባከነ፤ ተስፋ እያስቆረጠ፤ መብታቸውን እየገገፈፈ፤ ተሰደው የውጭ ምንዛሬ እንዲልኩ እያደረገ ከሕንድ፤ ከቻይናና ከሌሎች አገሮች የሰው ኃይል፤ የቀን ሰራተኞች ጨምሮ፤ ይሽምታል። ኢትዮጵያውያን ሊሰሩት የሚችሉትን በውጭ አገር ሰዎች ያሰራል። አገሪቱ የማትችለውን ደሞዝና አበል ይከፍላል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተማረውና ያሰለጠነው የሰው ኃይል፤ በተለይ ወጣቱ ትውልድ በአገሩ የመስራትና የስራ እድል የመፍጠር አቅምና መብቱ ስለታፈነ ወደ መካከለኛው ምስራቅ፤ ሰሜንና ደቡብ ሱዳን ወዘተ ይጎርፋል። የሳውዲ፤ በቅርቡ የኩዌት መንግሥትና ሌሎች በኢትዮጵያውያን የቀን ሰራተኞች ላይ የወስዱት አሳፋሪ እርምጃ በግልፅ ያሳየን አስደናቂ እድገት ታሳያለች የምትባለው አገራችን የኢትዮጵያውያንን የስራ፤ የገቢና የኑሮ ፍላጎት ለማሟላት አለመቻሏን ነው። በተደጋጋሚ እድገቱ የጥቂቶች መጠቀሚያ ሆኗል የምለው ለዚህ ነው።
አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ በኑሮው፤ በመብቱ፤ በመንግሥቱና በተፈጥሮ ሃቡቱ ለማዘዝ አይችልም። በአገር ቤት መሬት ለመመራት፤ ቤት ለመግዛት፤ የግል ተቋም ለመመስረት የሚችለው ገቢና አቅም ያለው ዲያስፖራ፤ በአብዛኛው የገዢው ፓርቲ አጋር ሆኗል ለማለት ይቻላል። በዓለም ድሃ፤ የሕዝባቸው ጤና ያልተጠበቀበትና ኋላ ቀር ከሆኑ አገሮች መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የተማረ የሰው ኃይል ድሃ መሆኗን በአንድ ምሳሌ አቀርበዋለሁ። የካናዳው ኩሶ ኢንተርናሽናል ባደረገው ጥናት ከ1990-2006 ዓም ባለው ጊዜ ብቻ ኢትዮጵያ ካሰለጠነቻቸው 3,700 የህክምና ባለሞያዎች 700 ብቻ አገር ቤት ይሰራሉ። ሶስት ሽህ የሚሆኑት ወጥተው ሌሎች ሕብረተሰቦችን፤ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያገለግላሉ። በሌሎች ሞያዎች የተሰማራነውም ተመሳሳይ ሚና አለን። ገዢው ፓርቲ ፈቃድና ፓሥፖርት በመስጠት ቀልጣፋ ነው። መብትን በመግፈፍ የሰለጠነ ነው። የሚፈልገውን ያገኛል። የሚፈልገው ሁለት ነገሮች አሉ። አንድ የውስጥ ተወዳዳሪና ተቃዋሚ እንዳይኖር። ሁለት ወደ ውጭ የሚጎርፈው የሰው ኃይል የውጭ ምንዛሬ እንዲልክና ለገዢው ፓርቲ ደጋፊ እንዲሆን። ብንቀበልም ባንቀበልም ይህ እቅድ እየሰራ ነው። የእድገቱ አድናቂ ከሆኑት ውስጥ ሃብትና ቤት ያለው ዲያስፖራ የመጀመሪያውን ደረጃ ይዟል። ከመቶው ዘጠናው የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፍስ ወከፍ ገቢ ዓለም ባንክ ካወጣው በቀን አንድ ዶላር ከሃያ አምስት ሳንቲም በታች መሆኑን ረስቶታል ወይንም አያየውም። ስለዚህ ነው፤ “ዓባይ ዓባይ ዓባይ” የሚለው አነጋጋሪ አርእስት ከስርዓቱ አፋኝነት ጋር አብሮ መታየት አለበት የምለው። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]
The Nile is a major north-flowing river in northeastern Africa

No comments:

Post a Comment