Translate

Friday, June 30, 2017

ጎንደር ቅዳሜ ገበያ ፈንጂ ፈነዳ

Image result for Gonder Ethiopia sateday shop
(ዘ-ሐበሻ) መሬታችንን እና መሪዎቻችንን አስበልተን አንቀመጥም ያሉት የጎንደር አማራ ታጋዮች የሕወሓትን መንግስት በየአቅጣጫው እየተፈታተኑት በሚገኙበት በዚህ ወቅት ዛሬ በጎንደር ከተማ ቅዳሜ ገበያ አካባቢ ከተማዋን ያናወጠ ፈንጂ መፈንዳቱ ተሰማ::
የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከስፍራው እንደገለጹት ቦምቡን ያፈነዳው አካል ማን እንደሆነ ባይታወቅም በጎንደር የአማራ ተጋድሎ እያደረሰበት ያለውን ሽንፈት በሽብርተኝነት ስም ለመደፋፈን ስርዓቱ ሆን ብሎ ያፈነዳው ሊሆን ይችላል በሚል ሕዝቡ እየተነጋገረበት መሆኑ ታውቋል:
:
በተለይም ፈንጂው ከመፈንዳቱ በፊት የሕወሓት ሰላዮች ተብለው የሚጠረጠሩ ወገኖች በስፍራው መታየታቸው ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ሴራ ሊሆን ይችላል የሚለውን ጥርጣሬ አጉልቶታል የሚሉት ምንጮቻችን በፈንጂው የሞተውን ሰው ቁጥር እያጣሩ መሆኑን እና የቆሉም በሁለት አሃዝ የሚቆጠሩ መሆናቸውን ነግረውናል::
ይህን ዜና ተከታትለን እንዘግባለን::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ መንግስታዊው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ስለዚህ ፍንዳታ የሚከተለውን ዘግቧል:: ለግንዛቤ እንዲረዳዎት እንደወረደ አቅርበነዋል::
በጎንደር ከተማ ቅዳሜ ገበያ ልዩ ስሙ አሮጌ ብረት ተራ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የሞርታር ቀለሃ(ጥይት) ፈንድቶ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የሰዎቹ ህይወት ያለፈው የሞርተር ቀለሃን ለብረት ሙቀጫ እንዲውል በማሰብ በመጋዝ በመቁረጥ ላይ እንዳሉ ፈንድቶባቸው መሆኑን፥ የከተማው ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ማረልኝ ወንድሙ ገልጸዋል፡፡
ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት ተኩል አካባቢ በደረሰው በዚሁ አደጋ፥ ህይወታቸው ካለፉት በተጨማሪ በአካባቢው የነበሩ ሶስት ሰዎችም የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ቁስለኞችም በአካባቢው ህብረተሰብ ትብብር በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝም ዋና ኢንስፔክተሩ አስታውቀዋል፡፡
ህብረተሰቡ እንደዚህ ዓይነትና ሌሎችም አደጋ ሊያደርሱ የሚችሉ ቁሳቁሶችን ሲጠቀም፥ መጀመሪያ ምንነቱን ማወቅና ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም ተመልክቷል፡፡

No comments:

Post a Comment