Translate

Thursday, June 15, 2017

ህወሃት በሜካናይዝድና (ብረት ለበስ በከባድ መስራያ የታገዘ) ጦርነት ተጋርጦብኛል ይላል


ሰበር መረጃ (ሰኔ 7/2009)
በልኡል አለሜ
በሰሜን ግንባር ሁለት የጦር ቀጠናዎች ቀይ መስመሩን ማለፋቸዉ እየተነገረ ነዉ። ሦስት የህወሃት ክ/ጦሮች በመረባረብ ላይ ናቸዉ።

በብረት ለበስ እና በከባድ መሳሪያዎች የታገዘዉ ጦርነት በሁመራ ግንባር በተለይም በሱዳንና በህወሃት ህብረት ቡድን ላይም ጥቃት ሊደርስ እንደሚችል ቃኘዉ ደህንነት ለሐገር መከላክያ ሰራዊት አስታዉቀዋል።
ከተለያየ ክልል ማሰልጠኛ ተመርጦ በሰሜን ግንባር ደጀን ጦር የተዋቀረዉ አዲስ ሐይል በክፍለ ጦሮች ምድብ ዉስጥ በተካተተ በጥቂት ቀናት ዉስጥ እንዲህ ያለዉ የጦርነት አስደንጋጭ ዜና የስነ ልቦና አደጋን ይፈጥራል በሚል ሙሉ መረጃዎች እንዲገደቡ ተደርጓል።
ወታደራዊ ጥቃቶች ሁሉ ላይ የኤርትራ እጅ አለበት የሚለዉ ወታደራዊ ደህንነት መረጃ ክንፍ ለመከላከልና ጥቃት ለመመለስ በሚቻልበት መልኩ ዝግጅት እንዲደረግ በተለይም ታንኮች እና ከባድ መሳሪያዎች በተመሳሳይ የጥቃት ቀጠናዎች ዙሪያ እንዲሰማሩ፣ ቃኘዉ መጠነኛ ወታደራዊ በረራዎችም ተደጋጋሚ እይታ እንዲያደርጉ፣ ራዳር መቆጣጠሪያዎች ሬዲዮ ቴሌስኮፖች እና እግረኛ ቃኚ ስልጡኖች እንዲሰማሩ መረጃ የወረደ ሲሆን በወሰን ተሻጋሪ መረጃ ሐይሎች በኩል በሰሜን ድንበሮች አካባቢ ልምምዶች እየተደረጉ መሆኑን በተለይም የግብጽን የመከላከያ ወታደራዊ ደንብ ልብስ የለበሱ ሐይሎች በስፍራዉ እየታዩ እንደሚገኙ ፍንጮች አመልክተዋል።
የህወሃት ወታደራዊ ደህንነት ከወሰን ተሻጋሪ ምንጮች የደረሰዉን መረጃ በማጣጣል እንዲህ ያለዉ ወታደራዊ ስልጠና ድንበር ጥግ ላይ እንደማይሞከር ይልቁንም ከዝግጅቱ ከፍተኛነት የተነሳ ወታደራዊ ጥቃት እንደሚፈጸም ከበቂ በላይ መረጃ እንዳለዉ በማስጠንቀቅ ዝግጅቱ ላይ ትኩረት እንዲደረግ አስገድዷል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

No comments:

Post a Comment