Translate

Friday, February 19, 2016

ብርሃኑ ነጋ ለስልጣን ነው የሚታገለውን ? ( ሄኖክ የሺጥላ )


ብርሃኑ ነጋ ለስልጣን ነው የሚታገለው ለሚሉ ሰዎች ዛሬ የመልስ ምት መፃፍ ኣምሮኛል ። እንደሚከተለው ይቀርባል ።
ከጥያቄው እንነሳ
ብርሃኑ ነጋ ለስልጣን ነው ወይ የሚታገለው ?
ቀጥተኛ ያልሆነ መልስ « ኣዎ!» ብርሃኑ ለስልጣን ነው የሚታገለው። 


ስልጣን ማለት ግን ምን ማለት ነው ? ስልጣንስ እንዴት ነው የሚያዘው ? የሚገኘው ኣላልኩም። እሰሚገባኝ እውነተኛው የስልጣን ጉልበት ያለው ህዝቦች በፈቀዱት የመገዛት ምርጫ ና ያንን ምርጫቸውን በኣግባቡ በሚረዳ የስልጣን መንፈስ ውስጥ ያለ ማህበራዊ የመሪና እና የተመሪ ኣስተዳደራዊ መግባባት እና መስተጋብር ነው የሚመስለኝ ። ምን ማለት ነው? የሚመራውን ያልመረጠ ህዘብ ፥ መሪህ ነኝ ላለው ኣካል መንፈሱን ኣይገብርም ። የማይፈልገው ኣለቃ የተሾመበት ህዝብ ፥ የሚፈልገውን ኣይናገርም ። ስለዚህ ህዝቡ ከሞላ ጎደል የስልጣኑ ባለቤት ሳይሆን ፥የስልጣኑ መጠቀሚያ ዕቃ ነው የሚሆነው። በቀላል ቋንቋ የኣገዛዙ ባሪያ ነው ማለት ይቻላል ። መሪውን ያልመረጠ ህዝብ በ « ጌቶችህ ነን» ባዮቹ የመገዛቱ ነገር ከምርጫ የመጣ ሳይሆን « ጌቶቹን» በሚገባቸው ቋንቋ ሊገገዳደርበት የሚያስችለው ኣቅም የማጣቱ ጉዳይ ነው የሚሆነው ። ስለዚህ ስልጣን ታግሎ የማሸነፍ ወይም ሞክሮ የመሸነፍ ጉዳይ ሳይሆን የመመረጥ ጉዳይ ነው ፥ ስልጣን የራዕይ ጉዳይ ነው፥ ስልጣን በብረት ክንድ የሚገኝ ወይም ደሞ በለሰለሱ መዳፎች የማይጨበጥ ቁስ ኣይደለም ። ስልጣን በሃሳብ ሞግቶ ቅቡል የሆነ እና ለህዝቡ የሚጠቅም ኣመለካከትን ለሚያመነጭ ጭንቅላት ህዝቡ በይሁንታ እና በህብረት የሚለግሰው የተመራጭነት ልዕልና ነው ። ለዚህም ነው ወያኔ የለበሰው የስልጣን ካባ ሰፍቶት የምንመለከተው ። የሱ ስላይደለ ፥ ለካባው የሚሆን ተክለ ሰውነት ስለሌለው ። ካባውን ቢደርብም ኣካሉ ላይ መጋረጃ የመሰለበት ፥ በህዝቡ የፍትህ እና የመልካም ኣስተዳደር ጥያቄ ልክ የተሰፋው ካባ ፥ ለወያኔ ኣይነት የዲሞክራሲ ማራስምስ ለያዘው ስርኣት እጅግ ስለማይመጥን። ያልመረጠውን ህዝብ ሊመራ ቆርጦ የተነሳ ኣካል፥ በእንዲህ ያለ ውሳኔው የመምራት ብቃት እና ኣቅሙን ሳይሆን ግብዝነቱን ነው የምታይበት፥ ስልጣንን ላራሱ ችሮ በጉልበቱ እያስፈራራ የህዝብ ጥያቄ ኣፍኖ «ባለ ስልጣን» ነኝ የሚልህ ኣካል ፥ እሱ በጉልበቱ ካስገበረው የህዝብ መንፈስ ውስጥ ያለውን የእምቢተኝነት ስሜት መረዳት ኣለመቻሉን እንጂ መምራት መቻሉን ልትመለከት ኣትችልም ፥ ምክንያቱም ስልጣን ስለሌለው ። ስልጣን በጠመንጃ ኣፈ ሙዝ ተገኝቶ ኣያውቅም። የጠመንጃ ኣፈ ሙዝ ስልጣንን ያለ ህዝብ ፍቃድ እየባለገበት ያለን ኣንድ ደፋር ስርኣት ሊያስወግድ ይችል ይሆናል እንጂ ፥ የስልጣን መሰረት ይጥላል ብሎ ማሰብ ከንቱነት የሚሆነውም ለዚያ ነው ። ስልጣን የሚገኘው በሃሳብ በመላቅ ነው ፥ የተሻለ ሆኖ በመገኘት ነው፥ ስልጣን የስልጡንነት ውጤት ነው ። ለምሳሌ ኣባትነት ስልጣን ነው ። ስልጣኑን የሰጠው ደሞ የኣባትነት ሚናው ነው ። ለልጆቹ የሚሆን ምግብ ፥ ልብስ ፥ መጠለያ ያቀርባል ፥ ልጆቹን ሲያማቸው ያሳክማል ፥ ሲወድቁ ያነሳል ፥ ኣንዱን ካንዱ ኣያበላልጥም ። ይህ በተግባር ላይ የተመሰረተ የሃላፊነት ተቀባይነት ስሜት ኣባት ያደርጋል ፥ በልጆች ልብ ውስጥ ፍቅርን ይጭራል ፥ ተሰሚነት ብቻ ሳይሆን ታማኝነትንም ያለ ኣንዳች ሰባኪ በልጆች ልቦና ውስጥ ያኖራል ። የመንግስት ስልጣንም ከዚህ የተለየ ኣይደለም ። ህዝቦቹ በተራቡ ጊዜ በኣፋጣኝ ከጎተራው ዝቆ ያበላል ፥ በስደት መከራ መገጠማቸው ጊዜ ኣለሁላችሁ ይላል ፥ በተቻለ መጠን ኣያዳላም ፥ ኣንደኛ ዜጋ ፥ ሁለተኛ ዜጋ የሚባል ነገር ስልጣን በተሰጠው ስርኣት ውስጥ ኣይንፀባረቅም ። ይህ ደሞ የወያኔ ባህሪ ኣይደለም፥ ምክንያቱ ደሞ ወያኔ ስልጣን ስለሌለው።

ባጭሩ ብርሃኑ ነጋ ለስልጣን ነው የሚታገለው፥ የሱም የስልጣን ትግል ለልጆቹ ከቆመ ኣባት ወይም የኣባትነት ስልጣን ከተሰጠው ሰው ጋ ይመሳሰላል ። ብርሃኑ ለኢትዮጵያ እና ለህዝቦቿ በጎ ነገር ያስባል ፥ ለሱ ሁለተኛ ዜጋ የሚባል ነገር የለም ፥ ኣንደ ኣንድ ትልቅ ኣባት ኣንድ ህይወቱን ኣደጋ ላይ ጥሎ የምንፈልገው ነፃነት ይመጣ ዘንድ ይታትራል ። ብርሃኑ ህዝብን ወደ ተሻለ መንገድ መምራት የሚያስችል ዘመናዊ እውቀት ባለቤት ነው ፥ቅን ልቦና ባለቤት ነው ፥ የትእግስት ባለቤት ነው ። ብርሃኑ በሲደሃርታ ወይም በቡድሃ ሊመሰል ይችላል። ቡድሃ መልካም ህይወትን ኣልናቀም ፥ ግን ከኣባቱ ቤተ መንግስት ኣጥር ስር የወደቀው ድሃ ሰው ከሱ ሰማያዊ ህይወት በለጠበት ፥ ኣላማውም የኣባቱን ሰማማዊ ህይወት ወደ ርካሽ የድሃ ህይወት መቀየር ኣልነበረም ። የቡድሃ ህይወት ፥ የድንጋይ ግንቡን ጥሶ ፥ ልቡን ዘልቆ የገባ ኣንድ ነገር ብቻ ነው ፥ የ ሰው ልጅ ፍቅር ፥ የእኩልነት ፍቅር ፥ የመብት ፍቅር ፥ የብርሃን ፍቅር ። ብርሃኑም በነዚህ ፍቅሮች የተመታ ሰው ነው ፥ በፍቅር የወደቀለት ነገር ደሞ መሪ የሚያደርገው ነው ። ይገባዋል እኛም እንደግፈዋለን ፥ ከጎኑም እንቆማለን ። ቃላችን ኣይታጠፍም !!!

No comments:

Post a Comment