Translate

Wednesday, February 24, 2016

ትግሬና ሌሎች ( ሄኖክ የሺጥላ ) ባንድ ሃገር ሁለት ዜጎች !

ትግሬና ሌሎች ( ሄኖክ የሺጥላ )Henoke Yeshetlla's photo.
ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት ኣይነት ህዝቦች ኣሉ ። የመጀመሪያዎቹ እና ህገ መንግስታዊ መብታቸው ቢከበርም ባይከበርም ፥ ያለ ኣንዳች ቅሬታ እና በፍፅም መንግስታዊ ፍቅር ስር የሚኖሩት ትግሬዎች ሲሆኑ ፥ የተቀሩት ሌሎች የሚባሉት ናቸው። ከትግሬ ወገን የሆነ ሰው ቢያጠፋ እንኳ ክፍ ቅጣት ኣይቀጣም ።
ምሳሌ ስዬ ኣብርሃ ፥ ኣማረ ኣረጋዊ ፥ ገብሩ ኣስራት ፥ ዳዊት ( ኣውራምባ ) ፥ ፃድቃን ገ/ትንሳይ ፥ እና ወዘተ ። ከሌሎች ወገን የሆነ ግን ባያጠፋ እንኳ ኣይቀጡ ቅጣት ይቀጣል ፥ በየ እስር ቤቱ ይወረወራል ፥ በኣደባባይ በጥይት ይገደላል ፥ ቤት ንብረቱን ይቀማል ፥ ከስራ ገበታው ይፈናቀላል ፥ ሃገሩን ለቆ እንዲሰደድ ይደረጋል ። ምሳሌ ፕ/ሮ ኣስራት ወልደየስ ፥ ዶ/ር ታዬ ወ/ሰማያት ፥ ኦልባና ሌሊሳ ፥ እስክንድር ነጋ ፥ ኣንዷለም ኣራጌ ፥ ተመስገን ደሳለኝ ፥ ህፃን ነብዩ ፥ ሽብሬ ፥ ኣሰፋ ማሩ ፥ ኣሁን ደሞ በኦሮሚያ በስም ጠርተን የማንጨርሳቸችው ዜጎች ፥ ብቻ ምን ኣለፋችሁ ፥ በዚህች ሃገር ሁለት ኣይነት ዜጋ ኣለ ። ኣንደኛው ደርግን ስለመጣሉ የሚያወራ ፥ ጀግንነት ባጥንቱ የተዋረሰው ፥ የሱ ብቻ የሚመስለው ግብዝ ፥ ሌሎች የመናገርም ሆነ ቀጥ ብሎ የመራመድ መብት ያላቸው የማይመስለው ፥ የድሃውን ቤት በዶዘር ለማፍረስ የሃውዜን እልቂትን እንደ ምክንያት የሚያቀርብ ፥ ጋዜጤኞችን ለማሰር በደርግ ጊዜ ያልነበረ የመፃፍ ና የመናገር መብት እሱ እንደሻማ ቀልጦ ያመጣልን ስለሆነ ፥ እኛን ዝም የማስባል የማይገስ መብት ያለው መስሎ የሚሰማው ፥ ከትግሬ ሌላ ሌላው ፈሪ ፥ ኣቅመ ቢስ ፥ ደካማ እና ወኔ ኣልባ ሆኖ የሚታየው ሲሆን ፥ ቤሌሎች ስር የሚመደቡት ይህ ትግሬ ነኝ ባይ ባሌጌ የሚያደርስባቸውን በደል ዋጥ ኣድርገው ቁጭ ያሉት ናቸው ። ወደዳችሁም ጠላችሁም ኣሁን ባለችው ኢትዮጵያ ውስጥ የዚህ ኣይነቱ ክፍፍል ተፈጥሯል ። ለምሳሌ በሰላሙ ጊዜ ቄስ ፥ እንዲህ እንደዛሬ መንግስትን የሚፈታተን ህዝባዊ ተቃውሞ በተነሳ ጊዜ ደሞ ቀስት ሆኖ ህዝቡን የሚወጋ ልማታዊ ቀሲስ ፥ ትግሬኔቱ ከማንኛውም ሰብኣዊ ኣስተሳሰብ የገፋው ፥ በሃገሩ ሳይሆን በዘሩ ኣይን ብቻ ለማየት የተፈጠረ ማህበረሰብ በኣሁኗ ኢትዮጵያ መኖሩ እውነት ስለመሆኑ ጠቅሰን የማንጨርሰው የግብር ማሳያ ኣለን።
ትግሬ እና ሌሎች በሚኖሩባት ሃገር ፥ ሌሎች ይገደላሉ ፥ ይበደላሉ ፥ ይዋረዳሉ ፥ መሬታቸው ይቀማል ፥ ከተሞቻቸው ለኣከሌ ፋውንዴሽን ፥ ለኣከሌ ራእይ ማስቀጠያ ተብለው ይወረሳሉ ፥ ደኖቻቸው ይመነጠራሉ ፥ ለባዕዳን ተሽጠው ይታረሳሉ ፥ ይራባሉ ፥ የመንግስት ወገኖች ግን በየ ከተማው ግድግዳ ላይ ውስኪ ያስታውካሉ ፥ ቢራ ይሸናሉ ፥ ቁርጥ ያራሉ ፥ ቅቤ ይናፈጣሉ ። ባንድ ሃገር ሁለት ዜጎች !
የባሌ ገበሬ መብቴ ይከበር ሲል ፥ የሃረማያ ተማሪ ህገ መንግስቱ ይከበር ሲል ፥ የሱሉልታ እና የሰላሌ ኣርሶ ኣደር መሬቴን ኣልቀማም ሲል፥ የሌሎች ወገን ናቸውና ፥ በተመረጡት ወገኖች ጥይት ይገደላል፥ በተመረጡት ወገኖች ታንክ ይጨፈለቃል ፥ በተመረጡት ወገኖች ወህኒ ይማቅቃል ።
የጎንደር ገበሬ እኔነቴን ኣውቀዋለሁ ሲል ፥ እሱነቱን እስኪክድ ድረስ ይደበደባል ፥ እሱነቱን እሲኪረሳ ድረስ ይበደላል ፥ የሌሎች ወገኖችን ህግ ኣለማደማጥ ፥ «የተመረጡትን ፥ ሃያሎቹን ትግሬዎች» እንደመካድ ይቆጠራል ፥ ስለዚህ የሞት ደጃፎች ደርሶ እስኪመለስ ድረስ ቶርቸር ይደረጋል ።
ኣዎ ኢትዮጵያ በምትባል ሃገር ውስጥ በኣሁኑ ሰኣት ሁለት ኣይነት ዘር ነው ያለው ፥ ትግሬ እና ሌሎች ፥ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት ኣይነት ኑሮ ነው ያለው ፥ የትግሬ እና የሌሎች ፥ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት ኣይነት ህግ ነው ያለው ፥ የ ለትግሬዎች እና የ ለሌሎች ህግ ፥ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት ኣይነት መንግስት ነው ያለው የትግሬዎች እና የሌሎች ፥ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት ኣይነት ሞት ነው ያለው በትግሬ መንግስት ምክንያት መሞት እና ትግሬ ስላልሆንክ መሞት !
እርግጥ ነው ይህ የምለው ነገር እውነት ኣለመሆኑን ለማሳየት የሚዳክሩ ሌሎች « ኣብርሃ ደስታስ? » ሊሉ ይችላሉ ። እኔ ደሞ « ኣብርሃ ደስታ ምን ? » ብዬ ለመጠየቅ እገደዳለሁ ! ኣብረሃ ደስታ ዛሬ በኦሮሚያ ከተገደሉት 20 ንፁሃን ሰዎች ውስጥ ኣንድ ሃያኛውን ነብስ ነው የያዘው ፥ ኣብርሃ ደስታ ከ 5 ሚሊዮን ትግሬ ውስጥ በኣስተሳሰቡ መለየቱ የሚያስፈራ እንጂ የሚደንቅ ኣለመሆኑን ነው የማውቄው! በይበልጥ በዚህ 25 ኣመት፥ በህውሃት በደል እና ጭቆና ተማረው መንግስት ላይ ተቃውሞ ያቀረቡ ትግሬዎች ቁጥር በኣመት ኣንድ ሰው እንኳ ኣለመሁኑን ማወቅ እና ማሰብ ራሱ ፥ ትግሬ እና ሌሎች የሚለውን ክፍፍል ( ልዩነቱን ) የትግራይ ህዝብ በኣብረሃ ደስታን በማበርከት ኣይደልም የመፅሃፍ ቅዱሱን ኣብረሃም ቢያዋጡ እንኳ ሊያጠቡት እንደማይችሉ ነው የሚሰማኝ ! ኣዎ ይህ ህዝብ በትግሬዎች ሴራ ተጎሳቁሏል ፥ በትግሬዎች ዝምታ ተርቧል ፥ በትግሬዎች ከመንግስት ጋ መወገን ዛሬም በኣደባባይ የጥይት እራት እየሆነ ነው ፥ ይህ ማለት ደሞ ሌሎች የተነሱ ግዜ ፥ ትግሬዎች እጣ ፈንታቸው ምንድን ነው የሚሆነው የሚለውን እኔ ሳልሆን የህዝቡ ብሶት እና ቁጭት ነው የሚመልሰው ። ኣይን ያጠፋ ኣይኑ ይጥፋ የሚለው ህግ ለትግራይ ህዝብ ይገባዋል ወይ ? ይህንን ለመመለስ ፥ የትግራይን ህዝብ የምጠይቀው ጥያቄ ኣለኝ—-እኛ ሌሎች በእውነት ይሄ ሁሉ ይገባን ነበር ? ኣሁንስ ይገባናልን ? በመልሳችሁ ልክ እንግዲህ መልሴን ኣስሉት ! ያም ሆን ይህ በኔ ሰኣት ኣቆጣጠር ጊዜው ደርሷል ባይ ነኝ ! «በጥሞና እና በኣርምሞ ብቻ እንጠብቀው ! »

No comments:

Post a Comment