Translate

Wednesday, February 24, 2016

የህወሃት ልዩ ነፍሰ ገዳይ ሠራዊት አመሰራረት፣ የገዳይ ቡድኑ አጋዚ እና የእናት እንባ

የእግሊዝኛው ጽሁፍ አዘጋጅ – ዓለም ማሞ
የአማርኛው ተርጓሚ – ቢላል አበጋዝ
 “ፔንታጎን ያሰለጠናቸው የኢትዮጵያ ሠራዊት ፤ክፉውን አጋዚ የተሰኘውን ልዩ ኅይልም ይጨምራል።”
–ጄረሚ ስከሂል
ኢንተር- ሴፕት ኤንድ ናሽናል ሴኩሪቲ ለተባለው ጋዜጣ መስራችና ቃል አቀባይ ከአሜሪካ መንግስት ክፍተኛ ምክር ቤት የፍርድ ኮሚቴ ዘንድ ቀርቦ ከሰጠው የምስክርነት ቃል የተወሰደ ጥቅስ። ዲሴምበር 9 ፣2010
ታሪኩ እነሆ
ከእድሜዋ በላይ የጠናች መስላ ትታያለች።በአካል ያያት ስድሳ ዓመት ሞልቷታል ብሎ መገመት ይችላል።እውነቱ ግን አርባ ዓመትዋ ብቻ ነው።The Ethiopia TPLF/Agazi force
“ወታደራዊው መንግስት ስልጣን ከመያዙ ሁለት ዓመት በፊት ነው የተወለድኩት” ትላለች ታሪክ እየጠቀሰች።የተጨማደደው ቆዳዋ፤ማዲያቷ እና ሽበትዋ መከራን ያሳለፈችን እናት ታሪክ ይናገራሉ።ያለፉት አስር ዓመታት በችግር የተሰቃየችባቸው ናቸው። “የበኩር ልጄን ከአስር ዓመት በፊት ቀበርኩ፤እኛ ተቃዋሚዎች አቸንፈን ድምጣችንን በቀሙን ጊዜ” አለች ወደ አድማሱ ቃኝታ ከተራሮቹ ሰው ብቅ የሚል እንደሁ ትጠብቅ ይመስል።

“እንዴት ሞተ?” ብዬ ጠየቅኋት ላለፉት አስራ አምስት ደቂቃዎች ከማታው ውርጭ ላይ ከቆየንበት ውጭ ወደቤት እየተከተልኳት።
“በጠራራ ጸሃይ ከሚወደው ጓደኛው ጋር ነው የገደሉት።አንዲት ቦታ፤ በአንዲት ቀን ነው አዲስ አበባ ላይ የተገደሉት።” አለች በተጎሳቀለው ፊትዋ ላይ እምባዋ እየወረደ።ምሬትዋንና ያለችበተን የከፋ ሃዘን ጥልቀት በቃላት ለመግለጥ ይከብዳል። ከተቀመጥኩበት ብድግ ብዬ እጆችዋን ይዤ ካጠገብዋ ቁጢጥ አልኩ። “ማን ገደላቸው ?” ብዬ ጠየቅኋት።ትክዝ ብላ ቆይታ ወደበሩ ራመድ፡ ራመድ ብላ በሩን ከዘጋችው በኋላ ሚስጥር እንደምትነግረኝ ሁሉ ዝቅ ባለ ድምጥ “አጋዚ። ጋዚ። ነው የገደላቸው” እያለች የሟች ልጆችዋን ፎቶግራፎች ሳም ሳም አድርጋ እንዳያቸው ሰጠችኝ።ለትምህርት ምረቃ ቀን የተነሷቸው ነበሩ።ምስላቸው በፈገግታ ተሞልቷል።ምኞትና ተሰፋ ይታይባቸዋል።ፎቶግራፎቹ በእምባዋ ርሰዋል የንባዋ ዘለላ በፎቶ የሚታየውን የልጆችዋን ፈገግታ ሲሸፍነው ሀዘንዋን የሚጋሯት መስሎ ታየኝ። ሙታንና ቁዋሚዎች አብረው የሚያለቅሱበት አገር። በምናቤ ልጆቹ ቤቱ ውስጥ ያሉ መሰለኝ።በናትና ልጅ መሃል ሞትም የማያስቀረው ውህደት በማህፅንና በእትበት መሃከል ያለው ቁርኝት ይሆን ? እንጃ። ብቻ የልጆቹ ውቃቢና የዓፍላ መንፈሳቸው ክቤቱ ውስጥ አለ።ካደጉበት።ከምዬ ቤት።ገና ባጭር ሳይቀጩ ከነበሩበት።ከኪሴ መሃረብ አውጥቼ እንባውን ከፎተግራፎቹ በዝግታ ጠረግሁ።በጥልቅ አዘኔታ ሳያቸው ወንድሞቼ፤የወንድሜ ልጆች፤ያጎት ያክስቶቸ እንዲያው የናቴ ልጆች መስለው ታዩኝ።በህይወት ባሉበት ጊዘ አግኝቻቸው ባላውቅም የማውቃቸው መሰሉኝ።የኔ የራሴን ያለፈ የልጅነቴንና የወጣትነት ዘመን ከፊቴ ደቀኑብኝ።ወጣትነቴን፤ፍርሃት አልባነቱን፤ለፍትህ፤ለነጻነት፤በቁርጠኝነት ተከራካሪነት መቆሙን።
ዲሞክራሲ! ለምእተ አመታት እውን ያልሆን ስንቀርበው የሚርቀን  የኔ ትውልድ ህልም፤ያለፈው ትውልድም ህልም፤የዛሬው ትውልድም። “አዬ እርግማን” ብዬ ለራሴ አጉተመተምኩ።
ለመሄድ ስነሳ አዘንተኛዋ  እናት እቅፍ አረገችኝና  እባክህ ደግመህ መጥተህ ጠይቀኝ አለችኝ።እምባ እየተናነቀኝ ይሁን መጣለሁ። እጠይቅሻለሁ አልኳት።ስለያት ብቸኝነትዋን አሰብኩት።የሞቀ የደመቀ ሁለት ልጆችዋ ይቦረቁና ይጫወቱ የነበረበትን የዛሬውን ኦና ቤትዋን አሰብኩት።የናትን ሃዘን ጥልቀቱን እንድረዳው፤እንዲሰማኝ ሞከርኩ። የእናትን ሃዘን ፤የዘጠኝ ወር ቤትን ህመም ፤ ክናት ሌላ ማን ሊረዳው? አልኩ ለራሴ።
አጋዚ የሚለውን ስም በተደጋጋሚ ሰምቸዋለሁ።ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች ስለ አጋዚ የሚናገሩት ልክ እንደ ውጭ ወራሪ ሀይል አድርገው ነው።የዚህ ቡድን ሰለቦችና ተግባሩን ያዩት እንደሚናገሩት “ግኡዝ ገዳይ ሮቦቶች፤ ምንም ልዩነት የማያደርጉ ትንሽ ከትልቁ መለየት ህጻናት ከአዋቂ፤ወጣት ሽማግሌ፤ ሴት፤ ወንድ፤ የታጠቀ ወይ ጀሌ አንዱንም የማይመርጡ።ጨፍጫፊ።ግፍ መስራቱን ይወዱታል ቢባል ከውነት የራቀ አይሆንም።
አንድ የፋሺት ጣሊያ ወረራ ጊዜ የነበሩ አርበኛ አጋዚን ከጣሊያኑ ጊዜ ካራብኘሪ ጋር ያመሳስሉታል።
“ቋንቋቸው ግራ ነው።ባህልና ወግ ግዳቸውም አይደል።ባሻቸው ጊዜ መጥተው ወንዶችን፤ልጆችን መንጭቀው ይሄዳሉ።ሲሻቸው እዚው ረሽነው ይሄዳሉ። መንደር ቀበሌ ከተማ ይወርራሉ።አየህ አጋዚ ልክ እንደ ጣልያን ካራብኘሪዎች ነው።” የአረጋዊው የነጣው ረጅም ጢም፤የተሸበሸበው ግንባራቸው ብሩህ አይኖቻቸው ምስክርነት የቆሙ ይመስላሉ።
“ታውቃለህ እንዲህ ያለ በገዛ ህዝቡ ላይ የሚጨክን መንግስት ኖሮን በታሪካችን አያውቅም። ካራብኘሪዎችን ምን እንዳደረግናቸው ልንገርህ።” አሉ በኮራ ድምጻቸው “የእግዜርን እርዳታ ይዘን ከአርበኞች ጋር ሁነን ነቅለን ጣልናቸው።” የሚነደው ያገር ፍቅራቸው እንደ እሳት  ወላፈን ሙቀቱ እየተሰማኝ። “አጋዚዎችንም ዋጋቸውን እንሰጣቸዋለን።አዲሱ ትውልድ የኛን አርበኝነት ተዋርሷል።የጊዜ ጉዳይ ነው።አገራችን ነጻ ትወጣለች።” አሉ ምርኩዛቸውን ጠበቅ አድርገው እየጨበጡ።የታሪክ ምጸት ቢሆንም የአጋዚን ከጣሊያን ካራብኘሪዎች ማነጻጸር አሁን ብቻ አይደለም የሰማሁት።በስልጣን ላለው መንግስት ተወዳዳሪ ለሌለው ጭካኔ ማመሳከሪያ በመሻት ነው።
ባገሪቱ የትኛውም ክፍል ህዝባዊ እምቢተኝነት ወይም አመጽ ሲነሳሳ ከየት መጣ ሳይባል አጋዚ ከቸች ብሎ የአፈናና የግድያ ተግባሩን ያከናውናል።ብዙ ተመሳሳይ የአጋዚን ዘግናኝ ተግባራት፤ኢሰባዊ ድርጊቶችም  የሚገልጡ በርካታ ምስክርነቶች ሰምቻለሁ።ሁለት ወንዶች ልጆችዋን ለአጋዚ የገበረችውን እናት ካነጋገርኩ ወዲህ ግን አስተሳሰቤ ተለወጠ።ሀዘንም ዋጠኝ።ከዚህ ሌላስ ምን ግፍ ተሰርቷል?ምን ግፍስ ይሰራ ይሆን? እያለ አእምሮዬ ወተወተ።የዚህን የገዳይ፤አፋኝ ቡድን አሳዛኝ ድርጊት በሚቻለኝ መጠን ለማጋለጥ ቁርጠኛ አደረገኝ።
አጋዚ የሚለው ስም በኢትዮጵያ ፍራትና ሽብርን ይፈጥራል።ልክ ካራቫን ዴላ ሙኤርቴ (የሞት ቅፍለት) ተብሎ በቺሌ ላቲን አሜሪካ ይታወቅ እንደነበረው አይነት ነው።ይህ ቡድን አውጉስቶ ፒኖቼ የተባለው ወታደራዊ አምባ ገነን በ1973 ዓም መፈንቅለ መንግስት እንዳካሄደ ያቋቋመው ነው።ሌላው ተመሳሳይ ደግሞ ጄኔራል ሆዜ አልቤርቶ ሜድራኖ ያቋቋመው ኦርጋኒዛሲኦን ዴሞክራሲያ ናሺናሊስታ[1] የተባለው የኤል ሳልቫዶር (ላቲን አሜሪካ) ገዳይ ሰራዊት ነው። ይህ ሰራዊት በስውር የሚያግት፤በህይወት ፈራጅ፤ሰቆቃ ፈጻሚ ነበር። ለማንም መንግስትን ለተቃወመ ወይንም ተቃውሙዋል ተብሎ ለሚጠረጠር ቡድን ወይም ግለ ሰብ ያለ ምህረትና ሰባዊነት የግፍ ቀንበሩን ያሰፈረ ቡድን ነበር።
አጋዚ ምስጢራዊ  ራስ ገዝ ተጠያቂነቱ ቱባ ለሆኑት እፍኝ የማይሞሉ የህወሃት አመራሮች ነው።አጋዚ የተሰየመው ከህወሃት መስራቾች አንዱ በነበረው ዘሩ ገሰሰ የትግል ስሙ አጋዚ ነበርና።በውነተኛ ወታደራዊ አደረጃጀት ሲመዘን አጋዚ የግል ጦር፤ቅጥረኛ በጦር ቱጃሮች (war lordes) የግል ጥቅማቸውን ለመጠበቅ የሚቆሙትን ዓይነት ነው።የእዝ ሰንሰለቱ ከቋሚው ዘረኛና በዘር ከተዋቀረው የህወሃት መደበኛ መከላከያ መዋቅር ውጭ ነው።የአጋዚ መኖር ዋነኛ ምክንያት ወያኔ ኢሃዴግን በስልጣን ማሰንበት ነው።መንደርም በእሳት ተለኩሶ ይውደም፤ንጹሃን በጥይት ይፈጁ፤ ቀዬዎች የሽብር አምባ ይሆኑ፤ወያኔ ብቻ ይሰንብት። የአጋዚ መኖር ለዚህ ነው።አጋዚ ቀድሞ ሲመሰረት “ጸረ ዓለማቀፍ ሽብርተኛ” የሚል ጭንብል ነበረው። ይህ የሆነው የምእራብ አገር መንግስታትን ለማማለልና ደስ ለማሰኝት አልፎም ድጋፍ፤ስልጠና እና ትጥቅም ለማግኘት ነበር።ቍም ነገሩ ግን አገር በቀል የሆኑትንና ለዲሞክራሲ ፤ ለፍትህና ለነጻነት ራእይ የሚደረጉ ትግሎችንና እቢተኝነትን መደምሰስ ነው።
በዚህ ጉዳይ ላይ ጥቂት መርማሪ ጋዜጠኞች ስለ አጋዚና የውጭ ድጋፉ ጠይቀዋል።ይህን ግፈኛ ቡድን ማነው የሚያስታጥቀው ማንስ አሰለጠነው እያሉ።ከኒህ ጋዜጠኞች መካከል ጄረሚ ስከሂል ተቀዳሚው ነው።የዩ ኤስ አማሪካን ተመሳሳይ ሚና በአፍጋኒስታን፤ በማሊ፤ በሶማሊያ፤በየመን መርምሯል። በዲሴምበር 9 ቀን 2010 ዓም ለአሜሪካ ምክር ቤት በዝርዝር ምስክርነት ሰጥቷል።ምስክርነቱ ሰው አልባ የሚበር አውሮፕላንን  እቅስቃሴ፤የዩ ኤስ አሜሪካንና የሶማሊያ ጎሳ ጦር አበጋዞች ጋር ግንኙነት አካትዋል። “ሽብርተኝነትን መዋጋት” በሚል ሰበብ እንዴት አሜሪካ እንደ አጋዚ ያሉ የገዛ አገራቸውን ዜጎቸ የሚያሸብሩ ወታደራዊ ተቋሞችን መደራጀት ልታግዝ እንዴት እንደቻለች ጠይቋል። እንደ ሚስተር ሺል ጥናት “የዩ ኤስ አሜሪካን ልዩ ወታደራዊ ቡድን ለረጅም ጊዜ የአጋዚን ሰራዊት ሲያሰለጥን ኖርዋል”[2] የስከሂል የጥናት ጭብጥ እንደ ህውሃት ካሉት ጋር መቧደን የዘለቄታው ጉዳቱን  ለአሜሪካና ለአገራችንም የሚያስከትለውን ጉዳት ማመላከት ነው።
ቃሌን ጠብቄ የሁለቱ ልጆች እናት የወላድ መሃንዋን ልጠይቃት ተመለስኩ።ጭጋጋማ ቀዝቃዛ ምሽት ነበር።ከጓሮዋ  ካለችው ትንሽ ያትክልት ስፍራ እየቆፋፈረች ነበረ።”በልጆቼ ሃሳብ የተጨናነቀውን አእምሮየን ቢያስታግስልኝ ብዬ እማስናለሁ።” አለች እጅዋን እየጠራረገች። ክበሩ መግብያ ስደርስ ጠበቅ አድርጋ አቀፈችኝ። የናት ፍቅር ሙቀቱ እየተሰማኝ ወደቤቱ ውስጥ ተከተልኳት።
“እግዜር ይባርክህ ልትጠይቀኝ በመምጣትህ።” አለች ወደ ማድቤቱ እያመራች። “ሻይ አፈላልሃለሁ” አለች።
“አመሰግናለሁ” ብዬ መለስኩ።
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በእጅ በተሰራ ቅርጫት ብስኩት፤ ሻይ በፊንጃል ይዛልኝ መጣች።ስለ ብዙ ነገሮች አወራን።”ዛሬማ ብዙ እናቶች ለሞቱ ልጆቻችው ጥቁር ይለብሳሉ” አለችኝ አንዳንዶቹን በስም እየጠራች።
“ዛሬ እኮ ጨለማ ዘመን ነው።ጓደኞቸ፤መንደርተኞቸ፤የከተማውም ሰው አንድ ሰው ቢያንስ ተገሎባቸዋል” አለችኝ።
ደግሜ ልጠይቃት የመጣሁት ስለሟች ልጆችዋ ለመጠየቅ የሷንም መጽናናት ላውቅ ብዬ ነው።እንቅልፍ አጥታ እንደሰነበተች እንዲያው ድክም ብሏታል።ትንሽ ተኝታ ታድር እንደሁ ጠየቅኋት። “ሽለብ ሲያገኝ ልጆቼ ከፊቴ ድቅን ይላሉ።ከትምርት ቤት ሲመጡ፤ያዘዝኳቸውን ሲከውኑ፤የትምህርት ቤት የቤት ስራቸውን ሲሰሩ።እንቅልፍ የለኝም።ደህና እንቅልፍ የተኛሁበት ምሽት ይናፍቀኛል።”  ጥልቁ ሃዘንዋ፤አንዱ በሌላው ላይ የተደራረበው መከራዋ ህወሃት የፈጸመውን በደሎች ያመለክታሉ።ፈተናዋ አድክሟታል።
“የት ነው ልጆችሽ የተቀበሩት ?” አልኳት
“ተዚህ ግድም።ሩቅ አይደለም። በግር ያስኬዳል።በሰንበት ሁሌ ልጆቼን ላጫውት እሄዳለሁ” አለች።
“ዛሬ ትወስጅኛለሽ?” አልኳት
“አዎ! እወስድሃለሁ” እያለች ጥቁር ጥለት ነጠላዋን ተከናንባ “ተከትለኝ” አለችኝ። “በዚህ ጋ” ስትል ተከትያት ለአስራ አምስት ደቂቃ በደረቀው ሳራማ ሜዳ ላይ የግር መንገዱን ተከትለን ተጓዝን።ከሩቁ የሚግጡ ከብቶች ይታዩኛል።ጥቂት ሄደን ቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ደረስን።ጥቂት ጸሎት አድራጊዎች ተውጭው ይታያሉ ሌሎችም እየመጡ ነበር።ተገረገራው ስትደርስ አማተበችና እየሰገደች ጸለየች። እኔም እንደስዋ አደረግሁ። ጥቂት ራመድ እንዳለች ከበተ- ክርስትያኑ ደቡባዊ ጠርዝ ልጆችዋ ካረፉበት ደረስን። ጠጋ ስንል ንግግርና ልቅሶ ተደባልቀው እንሰማለን።
“እዚህ ነው ትኝት ያሉት።ልክ ከቤታቸው አብረው በልጅነታቸው ተቃቅፈው ይተኙ እንደነበረው፤አበቦቼ፤ልጆቼ” እያለች ፊትዋ ላይ ያለውን እንባ ጠረገችው።የራሴን እንባ እየታገልኩ እሷን ላጽናናት ሞከርኩ።ትንሹ ሲገደል ገና አስራ ስድስት ዓመት እንደነበረና ሰላማዊ ሰልፍ ሲካፈል እንደተገደለ ነገረችኝ። “ልክ እንደኔው ልጆቻችው በአጋዚ ጥይት የረገፉባቸው እናቶች እጅግ ብዙ ናቸው።” አለች ጉዞአችንን ወደ መጣንበተ ማምራት ስንጀምር።
“እንደምሰማው አጋዚዎች የሰለጠኑት በአሜሪካኖች ነው።ይህ እውነት ነው?” ብላ ጠየቀችኝ።አጥብቃ ነው የጠየቀችው ድምጽዋ ንንዴትም ብሶትም የተቀላቀለበት ይመስላል።
“አዎን ተመሳሳይ ዜና ሰምቻለሁ” ብዬ መለስኩላት።
“ለምን ልጆቻችንን የሚገድል ታጣቂ ቡድን ያሰለጥናሉ? ሳስብ የነበረው አሜሪካኖች ደግ ሰዎች ናቸው ብዬ ነበር። አዛኞችም ናቸው ብዬ ነው።”
“የአሜሪካ ህዝብ አይደለም።ይህ የፖለቲከኞች ውሳኔ ነው።” ብዬ ተገቢውን መለስኩላት። ትንሽ ቢያጥናናት ብዬ።
“ምን አልባት እንዳንተ የተማሩ ሰዎች የኛን በደል ለአሜሪካ ፖለቲከኞች ማድረስ አለባቸው። አጋዚ የሚባለው ልጆቻችንን መግደል እንዲያቆም።” አለች።
ለአሜሪካ ፖለቲከኞች ፤ለአሜሪካም ህዝብ ለዓለምም ሁሉ መልክትዋን ለማድረስ ቃል ገባሁላት።
ለመሄድ ስነሳ እንደምትማጠነኝ ሁና ወዳይኔ ብረቱ እያየች፤
“እባክህ በደላችንን ዓለም እንዲያውቀው አድርግ።አጋዚን አሰልጥነው ማስታጠቃቸው፤ በጅምላ ገዳዮችን ማሰልጠናቸው መሆኑን ይወቁት።አንድ ብቻ ሳይሆን ሁለት ልጆችዋን የተቀማችዋን እናት ታሪክን ንገራቸው።የወላድ መካንን እናት ምን ይሏታል? መካን የሆንኩት ሁለቱን ባንዴ አጋዚ ሲቀማኝ ነው።” አለች።
እኔ ለዚህ ሁሉ ጥያቄዎችዋ መልስ የለኝም።መልስም የምትጠብቅ አይመስለኝም።እንደው ሀዘንዋ ይውጣላት ብላ እንጂ።ምናልባት ሁለቱንም።እኒህ እለት ተእለት የማብሰለስላቸው ጥያቄዋች ናቸው።እስተማውቀው ድረስ ጥያቄዎቹ በሺ የሚቆጠሩ እናቶች ባገሩ በሞላ የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ናቸው።
ምስኪንዋን እናት ተሰናብተን መንደሩን ለቀን ስንጓዝ አይኖቼ አካባቢውን አማተሩ።የሚጫወቱ ልጆች አይታዩም።በማሳው ላይም ገበሬዎች የሉም ።መንገደኛም አይታይም።ህይወት እርጭ ብሎ፤ታግቷል።ተሩቅ የተኩስ ድምጥ ይሰማኛል።ማን ይሆን ባለሳምንት? ሌላ ወጣት? ወንድ ?ሌላ ወጣት ሴት?ሽማግሌ ማን ይሆን? ማነው ባለተራ ? ማን ይሆን የአጋዚ እራት ብዬ ተከዝኩ።
ባልጋዬ ጋደም ብዬ ያን ማታ የዚህን ጭካኔ መነሻ ልደርስበት አሰብኩ።ዘመናዊ ስልጣኔና ተቋም አቀድ የሆነ አረመኔያዊ ጥፋት በንጹሀንና ባልታጠቁ ህዝቦች ላይ! ሃሳቤ ከቦታ ቦታ ተንክራተተ፤ከአንድዋ እናት እምባ ወደ ሌላዋ። ከአንዱ አባት ምሬት ወደ ሌላው።ሸለብ ያረገኝ ብዬ ባስብ አእምሮዬ እምቢ አለ።“ሽለብ ሲያደርገኝ ልጆቼ ድቅን ይላሉ” ብላ ያለችው ደግሞ ደጋግሞ ባሳቤ ይመጣል።ልጠይቃት መሄዴ ሃዘንዋን አባብሶት ይሆን? ብዙ ተገላብጨ እንቅልፍ እምቢ ሲለኝ ተስፋ ቆረጥሁ።አጣጥፌ ከደብተሬ ያኖርኩትን የተጣጠፈ ወረቀት ሳብ አደረግሁት።የጥንቱ ሮማዊ ገጣሚ ጋየስ ቫሌሪየስ ከታለስ (84᎔54 ከክርስቶስ ልደት በፊት)ግጥም ነበር። ለሟች ወንድሙ የገጠመው፤
“በባእድ ባህሮች ቀዘፋ፤ ባልታወቁ ወደቦች ለቀናት በባህር ስጓዝልህ
ከዚህ የመጣሁት ለሽኝት ነው የናቴ ልጅ ላንተው ስንብት፤
ለሞትከው የቋሚን የመጨረሻ ስጦታ ይዥልህ
ቃሌ ከንቱ ነው ትቢያ ለሆነው ሰው።
አይ ወንድምየ ይኸው አንተን ነጠቁኝ
አንተን አብሮ አደግ ወንድሚን ቀሙኝ!
በጨካኝ እጃቸው ቀጠፉህ እኔንም በሀዘን ወጉኝ።
ይሄው ተዝካርህ ድሮም ለሄደ ድንግጉ
ትዝካርህን እነሆ በማእርጉ
የወንድምህ እምባ ያራሰውን
ውሰድ አድናቆቴን በሞቴ የእምባየን ንዳድ ስንብቴን”
ግጥሙን በህወሃቱ አጋዚ ለተገደሉት ሁሉ ደጋግሜ አነበብኩት።ደጋግሜ ባነበብሁት ቁጥር  አገሩን ማሰስ አማረኝ። እያንዳንድዋን አጋዚ ልጇን የቀማትን እናት ላናግር።ላዳምጣቸው፤ ሀዘናቸውን እካፈል ብዬ።ስሜቴና ፍላጎቴ ቢገፋፉኝም በተግባር ማዋሉ አቀበት መሆኑ አልጠፋኝም።የአጋዚ ግድያ ከመብዛቱ የተነሳ ቁጥሩ አያሌ ነውና በጥቂት ዓመታት ላዳርስ የምችለው ጥቂቶችን ብቻ ነው።ጥቂቶችን ብቻ።ጠዋት ሲነሱ ባዶ ወንበሮችን የሚያዩትን እናቶች። ከትምሀርት ቤት የቀሩባቸውን፤ለሰርጋቸው ያልበቁላቸውን፤አያቶች ያደርጉናል ብለው ይጓጉላቸው የነበሩትን።
ቆይቶ አእምሮዬ ተረጋግቶ አሰበ።አገሩን አስሼ የእናቶችን የሃዘን ህመም ሁሉ ማዳመጥ ወሰንኩ።የግል የምስጢር ፍላጎቴም ይሆናል የአባቴን አገር፤ውቡን አገር ያያት የቅማያቴን አገር ላይ።ቀኑ፤ቦታው፡ሰአቱ፡ምክኛቱ ወይ ሰውዬው የተለየ ይሆናል ወይ ጠመንጃውን የተኮሰው ሰውዬ አንድ አይሆን ይሆናል። የናቶች መሪር ሀዘን ግን ከሰሜን ተራሮች ይሁን ከምዕራብ ጥቅጥቅ ጫካ ፤ከሜዳማው አገር ይሁን ከደቡቡ ሳራማ መሬት፤ክምስራቅ፤ከከተማ ይሁን ባላገር የትም ቢሆን የእምዬ ሀዘን ያው ነው።እርር፤ድብን ነው።የዘጠኝ ወር ቤት ንዳድ።
ላሁኑ ስለማውቃት እናት መናገር መርጫለሁ።ስለተዋወቅኋት ደስታና ክብር ስለሚሰማኝ እናት።በስም ልጠራት የማልችለው እናት።የሁለት ልጆችዋ ምስል በአእምሮዬ ታትሞ የቀረው።ጀምበር በወጣች ቁጥር እኔን ወጥረው ይይዙኛል።ሁሌም ለፍትህ ቁም።ለስልጣን ለሹመት ሳይሆን እያሉ። ይህ ደግሞ ላደርግ ከምችለው ትንሹ ነገር ነው።
ደራሲውን ለማግኘት

No comments:

Post a Comment