Translate

Saturday, February 27, 2016

የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን መከላከያ ሰራዊት በሰሜኑ በኩል የሚያደርገዉ ዉጊያ እና ሰራዊቱ።

ሰበር ዜና ! !

የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን መከላከያ ሰራዊት በሰሜኑ በኩል የሚያደርገዉ ዉጊያ እና ሰራዊቱ።
መላዉ ኢትዮጵያዊያንን በሐይልና በጉልበት ሲገዛ የነበረዉ ህዝባዊ ጠላት ወያኔ አሉኝ የሚላቸዉን የመከላከያ ሰራዊት አባልት በኤርትራ ላይ ለማዝመት ሁለት ዋነኛ አላማዎ ችን ለሰራዊቱ አስቀምጧል


• ኤርትራ ለዘመናት የደከምንበትን እና ያጎለበትነዉን ሐገራዊ እድገት ለመቀልበስ አሸባሪዎችን አሰልጥና ወደ ሐገራችን እየላከች አርበኞች ግንቦት 7 በተባለ የሻቢያ ሐይል እየተመታን እንገኛለን በመሆኑም ከኤርትራ ድንበር ዉጭ በገዛ መረችን ላይ ገዢ ቦታዎችን በቁጥጥራቸዉ ስር ያደረጉት እነዚህ የሻቢያ ተላላኪዎችን መደምሰስ ዋና አጀንዳ ሆኖ የተቀመጠ ሲሆን 
• ኤርትራ የተቀመጠዉ መንግስት በኢትዮጵያ ዉስጥ ለተቀሰቀሰዉ ህዝባዊ አመጽ ዋነኛ ተጠያቂና ምክንያት ነዉ በመሆኑም ይህንን ለአመታት ሲፈጽምብን ዲፕሎማቲካዊ በሆነ መልኩ ለማግባባት ብንሞክርም አልቻልንም ዛሬ የኦሮምን ህዝብ በመቀሰቀና መንግስትን በመገልበጡ ሂደት ላይ እየሰራ የሚገኘዉን ሻቢያ ከስር መሰረቱ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በሌላ መተካት አላማችን ነዉ፡

የሚል መንደርደሪያ በመሆኑ ምክንያት የመከላከያ ሰራዊቱ በሁለት ጎራ ተከፍሎ እንዲጋጭ አይነተኛ መንገድ ተከፍቷል።
በተለይም የኦሮሞ ብሔር ተወላጆችና የአማራ ብሔር ተወላጆች የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ወገናዊ ተቆርቋሪዎች... ከአመራር ጀምሮ እስከ ጓድ መሪ ድረስ የስልጣን እርከን ዉስጥ የሚገኙ... የህዝብን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ለጦርነት መማገዱ አግባብ አይደለም! አርበኞች ግንቦት 7ም ኦነግ ወገኖቻችን ናቸዉ መንግስት ሰላማዊ በሆነ መልኩ ልዩነቶችን ለመፍታ ያደረገዉ ጥረት የለም! ለምን ጦርነትን እንደ መፍትሄ ይወስዳል! በሚል እስተሳሰብ እርስ በእርሱ እየተመካከረ ሲሆን ..ገና ጦርነቱ ሳይጀመር ሰራዊቱ እየተሰወረ ለመሆኑ ታማኝ ምንጮቻችን ገለጸዋ!!! 


በተለይም ከሁመራ ጀምሮ እስከ አማሃጅር ድረስ ለማጥቃት በዝግጅት ላይ የሚገኘዉ በሜካናይዝድ ክ/ጦር የተዋቀረዉ የተዉጣጣ ሰራዊት በየቀኑ ክፍተት እያመጣ መሆኑ ወያኔን ከባድ ችግር ዉስጥ የከተተዉ ሲሆን አንዳንድ አመራሮችን ባለማመን ምክንያት ከፍተኛ ጄኔራሎች መሬት ወርደዉ እየሰሩ ሲሆን የአየር ሐይል ሄሊኮፍተር አብራሪዎች በብዛት በትግሬዎች እንዲያዝ ተደርጓል።


በባድሜ በኩል በተመሳሳይ መልኩ በአየር ሐይል የታገዘ ዉጊያ ለማድረግ ዝግጅቱ እየተጧጧፈ ሲሆን ደብረ ዘይት እና ድሬ ዳዋ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ የአየር ሕይል 70% ለትግራይ ነጻ አዉጭ የስልጣን ማራዘም ፍላጎት ሲባል ብቻ.. ወደ መቀሌ ተወስዶ በባድሜ በኩል የሚወረወረዉን የወያኔ እግረኛና ሜካናይዝድ እንዲያግዝ ንዱፉ በወያኔ የጦር መሐንዲሶችና ጄኔራሎች የቀረበ ቢሆንም... በዚህ በኩል ለሚደረገዉ ማጥቃት ሻቢያ ከፍተኛ ዝግጅት እንዳላት እና በዚህ ክንፍ ለምናደርገዉ ማጥቃት በአንድ ብሔር ብቻ ማለትም በትግሬ ህዝብ ብቻ እንደምንዋጋ እንድታዉቁ ምክንያቱም ሌሌች የኢዮጵያዊ ብሔሮች ከእንግዲህ ለእኛ እንጂ ለሐገራቸዉ የሚሞቱ አይመስላቸዉም በማለት የፖለቲካ ወታደራዊ መረጃ ክፍሉ በድፍረት መናገሩን ከስፍራዉ የደረሰን መረጃ ጠቁሟል።

No comments:

Post a Comment