Translate

Tuesday, June 23, 2015

የሰላማዊ ትግልን እሬሳ ሳጥን የጨመረው ህወሃት፣ ቀይ ሽብር እንደገና

ክቢላል አበጋዝ – ዋሽንተን ዲሲ
እንግዲህ የሰላማዊ ትግል በኢትዮጵያ አከተመ። ህወሃትን በሌላ መንገድ የሚፋለሙት የጉልበት ሚዛኑን እስኪቀይሩት ድረስ የሰላማዊ መንገድ አብቅቷል። በኢትዮጵያ ታሪክ ሰው በሰው ላይ መንግስት በዜጋው ላይ ጭካኔ ፈጽሞ አያውቅም ብንል የታሪክ ማህደራችን ሩቅ ሳንሄድ በወታደራዊ ደርግ ዘመናት ብቻ እንኳን የተጻፈው፡ የተነገረው፡ የምናስታውሰው ብቻ በቂ ነው።የዛሬውስ ከፋ።ቀኑ ጨለመብን።ሰምተን አይተን ዝም ሆነ።ደነዘዝን።የሃይማኖት አባቶችም ዝም።የየቀዬው አባወራዎችም እናቶችም፤ ትልቁም ትንሹም የሆነውን ዋጥ አድርጎ ከለት ወደ ዕለት መንሳፈፍ ሆነ። ህወሃት ደርግን በቀይ ሽብር እየከሰሰ ዛሬ የሚያስንቅ ሆኖ ተገኘ።ሽብሩን ለመድነው::Samuale Aweka
የሰላማዊ ትግል ስልጣኔ፡ ፈሪሃ ፍትህ፡ፈሪሃ እግዚአብሄር ባሉበት የሚካሄድ ቢሆንም፤በትግሉ ዘዴ አጥብቀው ያመኑ ህወሃትን በዚህ መንገድ ሊጋፈጡት የሞከሩትን ካቸነፈ በኋላ እንኳን ይሄው አልማራቸውም። ህወሃት እንደ ድርጅት በጣም ዝቅ ያለባቸው በርካታ ጊዜያት የተመዘገቡ ቢሆንም የሰሞኑ አውሬነት ነው::ከመካከላቸው ጨርሶ ዘለቈታውን የሚያስተውል አንድም ዘዴኛም ሰው የለም የሚያሰኝ ነው።
ምርጫ ተካሄደን ከሰማን ሰነበትን።ህወሃት ትንሽም አልተጫረ።ድል በጁ ነው።አስተናባሪው፡ድምጽ ቆጣሪ እሱ ራሱ::አቸነፍኩ ብሎአል።ከዚህ በተረፋ ያለው አውሬነቱ፤ተራ ወንጀለኝነቱ ነው::ያለንበት አሜሪካ ከሜሂኮ ይዋሰናል:: ሜሂኮ በሚባለው አገር የእጽ ነጋዴዎቹ አይናቸው ያረፈበትን በጥይት በስለት ለሞት ይዳርጋሉ::ተማሪ ወጣት ልጆችን ገድለው እሬሳ በሳት ያቃጥላሉ:: ለህወሃት አምሳያ ብፈልግ የሜሂኮን እጽ ሻጭ ድርጅት/ካርቴል ነው ላቀርብ የምችለው:: በሜሂኮ መንግስት አለ:: በኢትዮጵያ ግን የለም። የሰማያዊ ፓርቲው ወጣት መሪ አሟሟት እጽ ሻጭ ድርጅት/ካርቴል እንፈጸመው ያለ ነው።

ምርጫው አልቋል። ግድያው የተራ ቂም በቀል ነው።ልክ እጽ ሻጭ ድርጅት/ካርቴል እንደሚያደርገው ሁሉ። የሰማያዊ ፓርቲው ሳሙኤለ አወቀ ወንጀል አልሰራም:: ማንንም አልበደለም::ተቃዋሚ መሆኑ ብቻ ለሞት አበቃው።አሟሟቱ ዘግናኝ ነው።የደርግ ዘመን ቢሆን ወረቀት ተለጥፎበት “ቀይ ሽብር ተፋፋመበት” ይባል ነበር።ዛሬ የህወሀት ገዳይ ቡድን በሚስጥር ይገድላል መንግስትም ይክዳል።
ህወሀት ለምን እነዚህ ዓይነት ዘግናኝ አስደንጋጭ እርምጃዎችን ይወስዳል?ገና ወደፊት ይነሳብኛል የሚለውን የበረታ አመጽ አመክናለሁ በማለት ሳይሆን ዛሬ ከፊት ለፊቱ ከቴፒ እስተ ጎንደር የተነሳውን እሳት አጠፋለሁ ከሚል ከንቱ ግምት ነው። የሰላማዊ ተቃዋሚ ድርጅቶች መሪዎችና አባላትን መተናኮሉ ብረት ያነሱበትን ማጎልበቱ መሆኑን መረዳት ያቃተው፤ምላጭ መሳብ ባቻ ሙያ ዘዴ የሆነው ያበዱ ሰዎች ክምች ነው።
ጉዳዩ ዘመናዊ ትምህርት መማር አለመማር አይደለም። ነጻ አገር ያስረከቡን አባቶቻችን ዘመናዊ ትምህርት አልነበራቸውም።እግዚአብሔርን የሚፈሩ ነበሩ። የህወሀት መሪዎች ድንቁርናቸው፡የዝቅተኝነት ስሜታቸውን መጨመሩ ገሃድ ነው።ይህ ባይሆን እንዴት ልጅ አይደግ ይላሉ? ሳሙኤለ አወቀ ነገ መሪ የሚሆን፤ያገር አለኝታ ሊሆንም የሚችል ነበር::እንዲህ ያለውን ወጣት ባጭር ከመቅጨት በላይ ምን ዝቅ ማለት ይኖራል? በትግራይም ታደሰ አብረሃ የተባለው ጎልማሳ ህይወቱ ተቀጥፏል።የዚህ ሁሉ ያለፈው ላይ ሲደመር ህወሀትን ከፖለቲካ ድርጅት ዝቅ አድርጎ ጠባብ የተራ ወንጀል ፈጻሚ፡ ዝግ የወንጀል ድርጅት ያደርገዋል። እኒህ ሰማዕታትን ሲያጠፏቸው ከኛ የሚጠበቅ ብዙ ነው።ዓላማቸው ህያው እንደሆነ በመገለጽ በቁርጠኝነት መግፋት ይኖርብናል።
ሌላው ምክንያት ከምርጫው አገኛለሁ ያለው ተቃዋሚዎችን ዝም ማሰኘትን: አለማግኘቱ ለባዕድ አገሮችም አሳያለሁ የሚለውን መልኩን ተቃዋሚዎች ስላጎደፉት ሁሉም ካልሆ የቀረው፡ግደለው እሰረው ብቻ መሆኑ ነው። የግድያው ቡድን ከማንም ቁጥጥር የወጣ ነው ማለት ፈጽሞ አይቻልም።አሁን ካለበትም አካሄድ ሊቀየር ህወሀት ፈጽሞ አይችልም:: የሚያስችለው ጊዜም ፋታም ሳያገኝ ወደ ድቀት የሚያመራ እንጂ ከሃያ ዓመታት በኋላ ሊታረም ችግሩ ነው።ሌላ ዘዴ የለውም።
ያቄመባቸውን አይምርም።ህወሃት ያበደ ውሻ ነው። ያበደን ውሻ መድሀኒት ፍለጋ አይደከምለትም።ማስወገድ ብቻ ነው ያለው አማራጭ።
ኢትዮጵያን አምላክዋ ይጠብቃታል:: እብሪተኞችን ያንበረክካል::
በግፍ የታሰሩ ጋዜጠኞች፡የሀይማኖት መሪዎችን፡ የፖለቲካ መሪዎችን ለማስፈታት እንጩህ! የፍርድ ያለህ ! የነጻነት ያለህ!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

No comments:

Post a Comment