Translate

Sunday, June 21, 2015

የመድረክ ምርጫ አስተባባሪ በደቡብ ኢትዮጵያ ተደብድበው ተገደሉ

የአቶ ብርሃኑ ኤረቦ አስከሬን ወንዝ ዳር ነው የተገኘው

medrek


የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ በደቡብ ክልል አንድ የምርጫ አስተባባሪው አርብለት ተገድለው መገኘታቸውን አስታወቀ። የተቃዋሚ ፓርቲም በምርጫ 2007 ዙሪያ የዛሬውን ጨምሮ 4 አባላቱና ደጋፊዎቹ መገደላቸውን አስታውቋል።

በዚህ ሳምንት እንደተገደሉ ተቃዋሚዎች ከገለጿቸው ሶስት ሰዎች በተጨማሪ በኦሮሚያና ደቡብ ክልል ህይወታቸው ማለፉ የተገለጸው አጠቃላይ ቁጥር ስድስት ደርሷል።
በደቡብ ክልል ሀዲያ ዞን ሶሮ ወረዳ የተገደሉት አቶ ብርሃኑ ኤረቦ ሐሙስለት በሁለት ፖሊስ ባልደረቦች ከመኖሪያ ቤታቸው ከተወሰዱ በኋላ ተደብድበው ህይወታቸው አልፎ ወንዝ ዳር መገኘታቸውን የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ምርጫ 2005 በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ወደ 46ሽህ የሚጠጉ የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ሰላማዊ በሆነ መልኩ መከናወኑን የኢትዮጵያ መንግስትና ምርጫ ቦርድ ይገልጻሉ። የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሂደቱ በወከባ እስራትና አልፎ አልፎ ግድያዎች የታዩበት ነው በሚል፤ ሂደቱንና ውጤቱን አንቀበለም በማለት መግለጫዎች አውጥተዋል።
ዘገባውን ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ። (ምንጭ: ፎቶና ዜና የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ)

No comments:

Post a Comment