Translate

Thursday, June 4, 2015

በኢትዮጵያና ሱማሊያ ድንበር ውጥረቱ አይሏል በትናንትና ዛሬ ጠዋት ጦርነት 19 ሰዎች ሞቱ

በኢትዮጵያና ሱማሊያ ድንበር ውጥረቱ አይሏል በትናንትና ዛሬ ጠዋት ጦርነት 19 ሰዎች ሞቱ

2ኛ ሳምንቱን የያዘውና በሶማሊያና በኢትዮጵያ ድንበር ባሉ መንደሮች አካባቢ በተነሳ ጦርነት ትናንት ረቡዕ እና ዛሬ ሐሙስ በተደረጉ ውጊያዎች የ19 ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ዜጎች ቁስለኛ መሆናቸውን ዘ-ሐበሻ ከስፍራው ያገኘችው መረጃ አመለከተ::

በድንበሩ አካባቢ ትናንትና ዛሬ በ3 መንደሮች አካባቢ 2 ውጊያዎች መደረጋቸውን ያስታወቁት የአካባቢው የዜና ምንጮች በዚህ ውጊያ ሳቢያ የአካባቢው ነዋሪዎች ንብረታቸውን እና ቤታቸውን ጥለው ለመሰደድ በቅተዋል::

በሶማሊያና በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ባሉት መንደሮች አካባቢ የተነሳው ጦርነት እስካሁን ግልጽ አለመሆናቸውን የሚጠቁሙት የዜና ምንጮች በደፈናው የዘር ግጭት ነው ሲሉት ይገልጹታል:: በዚህ ጦርነት ዙሪያ የሶማሊያም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን ለማርገብ ምንም አይነት ንግግር አለማድረጋቸውም ተዘግቧል::


በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር ባሉ መንደሮች ላለፉት ዓመታት በዘር ግጭት የተለያዩ ጦርነቶች ሲደረጉ የቆዩ መሆናቸውን የሚጠቁሙት የዜና ምንጮቹ የኢትዮጵያም ሆነ የሱማሊያ መንግስታት ዜጎቻቸው እየተላለቁባቸው ጉዳዩን በዝምታ ማለፋቸው በጣም አሳፋሪ ነው ብለውታል::በተለይም የኢትዮጵያ መንግስት ጦሩን ወደዚያ ከማስጠጋት ውጪ ጉዳዩን ለማረጋጋት ያደረገው ይኸ ነው የሚባል ሥራ አለመስራቱ እየተተቸ ነው::

No comments:

Post a Comment