Translate

Friday, June 12, 2015

በዛሬው ኢሳት ሬዲዮ ስርጭት



-ከኤርትራ በረሃ፤ ከኢትዮጵያ የነጻነት ታጋዮች የጦር ካምፕ ሰራዊቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልእክት አስተላልፏል። በስልጣን ላይ ያለውን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚመራውን መንግስት ለማስወገድ ኢትዮጵያውያን ትግሉን እንዲቀላቀሉ ሰራዊቱ ጥሪ አድርጓል።

-የሱዳን የመከላከያ ሰራዊት ድንበር ጥሶ፤ ወሰን አልፎ፤ ከኢትዮጵያ አፈር፤ ከኢትትዮጵያ ምድር ላይ ሰፍሮ ኢትዮጵያውያንን ማጥቃቱን አጠናክሮ ቀጥሏል። ባለፈው ቅዳሜ በአብደራፊ አከባቢ የሱዳን ወታደሮች በሁለት ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች ይዞታ ላይ ጥቃት ፈጽመው አውድመውታል። ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚመራው ሰራዊት ለሱዳን ወታደሮች ፍቃድ ሰጥቶ ጥቃቱን እንዲፈጽሙ እንዳደረገ ተገልጿል። ኢትዮጵያውያንን የህወሀት ሰራዊት ማስደብደቡን የኢሳት ምንጮች ከላኩት መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
-የቴፒው ትንቅንቅ አሁንም ቀጥሏል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የቴፒ ወጣቶች ቡድን በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ በወሰደው ድንገተኛ ጥቃት 3ፖሊሶችን ከገደለና በርካታ እስረኞች እንዲያመልጡ ካደረገ በኋላ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ሰራዊት አከባቢውን በመክበብ ጥቃት መፈጸም ጀምሯል። የወጣቶቹ ቡድን መሽጎበታል በሚል ውጊያ የጀመረው የህወሀት ሰራዊት ጠንከር ያለ የአጸፋ ምላሽ እንደገጠመው ለኢሣት የደረሰው መረጃ ያመለክታል። በውጊያው በርከት ያሉ የህወሀት ሰራዊት ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውም ታውቋል። የህወሀት ልሳን የሆነ ሬዲዮ ፋና እስር ቤት ሰብረው እስረኞችን ያስመለጡ ሽፍቶች ተገደሉ ሲል ዘግቧል።
- ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚመራው መንግስት በሀገሪቱ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ማፈኑን ተከትሎ የተቃዋሚ ፓርቲዎች "ቅድሚያ ነጻነት" ወደሚል ትግል ማዘንበላቸውን የእንግሊዙ ዘ-ጋርዲያን ጋዜጣ ዛሬ ዘገበ። አፈናው በመባባሱ ተቃዋሚዎች ሌሎች አማራጮችን እንዲመለከቱ እያስገደዳቸው እንደሆነ ጋዜጣው አስነብቧል።
http://ethsat.com/?p=33289

No comments:

Post a Comment