Translate

Monday, July 28, 2014

ሳውዲ የሚገኙት በረከት ስምዖን ጤና እያነጋገር ነው


bereket_simon

እሁድ ከአዲስ አበባ አንድ የጦር ሃይሎች ሆስፒታል ዶ/ር አስከትለው በሼክ አላሙዲን የግል አይሮፕላን እኩለ ሌሊት ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ለህክምና በድብቅ እንደገቡ የሚነገርላቸው አቶ በረከት ስሞኦን በተለምዶ ብግሻን እየተባለ የሚጠራ አንድ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የልብ ደም ቧንቧ ለማስፋት ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ከሳውዲ አየር መንገድ ምንጮቻችን ለማረጋገጥ ተችሏል። የበረከት ጤንነት በአሁኑ ሰዓት በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የሚገልጹት እነዚህ ምንጮች ዛሬ ጠዋት ከመካ የዒድ አል ፈጠር የፀሎት ስርዓት በኋላ ሼክ አላሙዲን በስልክ እንዳነጋገሯቸው ይናገራሉ።
አቶ በረከት ስምኦን ለህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ በድብቅ መምጣታቸውን የሚናገሩ እነዚህ የሳውዲ አየር መገድ ምስጢራዊ መረጃ አቀባዮች ባለስልጣኑ በአሁኑ ሰዓት ጅዳ ሆስፒታል መተኛታቸው በተለያዩ የዜና ማስራጫዎች በመዛመቱ ህክምናቸውን በተረጋጋ ሁኔታ ሳይጨርሱ ወደ ሃገር ሊመለሱ እንድሚችሉ ገልጸዋል።
እስካሁን የመንግስት መገኛኛ ብዙሃን በኚህ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ዙሪያ ምንም ያሉት ነገር አለመኖሩን የሚናገሩ አንዳንድ ወገኖች የአቶ በረከት ስሞኦን ተደብቆ እንደ ተራ ሰው ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ሆስፒታል ለህክምና መግባት ምናልባትም ለደህንነታቸው ሲባል የተወስደ እርምጃ ሳይሆን እንደማይቀር ይገምታሉ። ጅዳ ብግሻን ሪፈራል ሆስፒታል 4 ፎቅ ከበሽታቸው በማገገም ላይ እንደሚገኙ የሚነገረው አቶ በረከት ፍጹም መረጋጋት እንደማይታይባቸው የሚያመለክቱ መረጃዎች የደም ግፊታቸው አለመስተካከል በልባቸው ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ወደፊት ለከፍተኛ የጤና መታወክ ሊዳርጋቸው እንደሚቸል ገልጸዋል።
bereket and wife
በረከትና አስፉ
በሼክ አላሙዲን የግል አይሮፕላን ተደብቀው ለህክምና ከትላንት ሌሊት ሳውዲ ጂዳ ስለገቡት በረከት ስሞኦን በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤትም ሆነ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ምንም የሚያቁት ነገር እንደሌለ ለማረጋጋጥ ተችሏል።
በአሁን ሠዓት መካ ፀሎት ላይ የሚገኙት ሼክ አላሙዲን ማምሻውን በረከትን ይጎበኟቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
አቶ በረከት አንድ ሴት ልጃቸውን እና ሚስታቸውን አስከትለው መምጣቸውን የአየር መንገዱ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።
በዚህ ዜና ዙሪያ የሚደርሱንን አዳዲስ ተጨማሪ መረጃዎች እየተከታተለን የምናቀርብ መሆኑንን እናስታውቃለን።
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በሰበር ዜናነት የላኩት

No comments:

Post a Comment