Translate

Monday, July 14, 2014

አዋጅ አዋጅ !!!……….. ልብ ያለዉ ልብ ይበል ጆሮ ያለዉ ይስማ !!

አዋጅ አዋጅ !!!……….. ልብ ያለዉ ልብ ይበል ጆሮ ያለዉ ይስማ !!
የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል የተሰጠ መግለጫ
አዋጅ አዋጅ !!!
ልብ ያለህ ልብ በል ጆሮ ያለህ ስማ !!
የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በየመን መታገት አስመልክቶ አጭር መግለጫ ማውጣቱ ይታወቃል።በመግለጫችን የመን ታጋዩን ልታግት የምትችልበት የጸጉር ስንጣቂ የምታክል ምክንያት እንደሌላት ሊኖራትም እንደማይችል ስለሆነም ታጋዩ ባስቸኳይ እንዲለቀቅ በተደጋጋሚ ጠይቀን፣ ይህ ሳይሆን ቀርቶ የነጻነት ታጋዩ ለፋሽስቱ የወያኔ ቡድን ተላልፎ ቢሰጥ የመን የማይሰረዝ ታሪካዊ ስህተት የምትሰራ መሆኑን ህዝባዊ ሃይላችንም የበቀል እርምጃዎችን እንደሚወስድ አሳውቀን ወያኔም ምናልባት ትግሉን አስቆማለሁ በሚል የሞኝ ስሌት ያደረገው ከሆነ ድርጊቱ ትግሉን በዕልህ እና በበቀል አጅቦ ከመውሰድ እና ከማፋጠን የዘለለ ትልቁ የሃሳብ አባት አንዳርጋቸው በሃገሪቱ ሰማይ ላይ የለቀቀውን የኢትዮጵያዊነት ጸረ ወያኔ መንፈስ አስሮ አሰቃይቶ፣ገሎ ማስቆም እንደማይችል አሳስበን አስገንዝበን ነበር። መግለጫችን የተጻፈበት ቀለም ሳይደርቅ ግን የየመን መንግስት እንደሰጋነው ትልቁን የቁርጥ ቀን ልጅ ለወያኔ አሳልፎ መስጠቱን አውቀናል።

የተከበርከው የታላቅ ታሪክ ባለቤት የሆንከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ አሁንስ ምን ትጠብቃለህ?? ምንቀረህ ?? ያለህበትን ሁኔታ የሚገልጽ ከዚህ በላይ ገላጭ ነገር ከቶ ከወዴት ይመጣል??ወያኔ የአንዳርጋቸው በእጁ መግባት ለጊዜውም ቢሆን ከሚፈጥርለት ፌሽታ ጎን ለጎን እገታው በይፋ ከተገለጸበት ቅጽበት ጀምሮ ግን የሚፈራው የሚጠላው ነገር ብቅ ብሏል፦የአንድነት መንፈስ!! የጋራ ድምጽ!!እገታው ለኢትዮጵያ ህዝብ በይፋ ከተነገረ በኋላ በሁሉም አቅጣጫ የሚኖር መላው ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ አመለካከት እና ፍልስፍና ሳያግደው ለአንዳርጋቸው ያለውን ድጋፍ እና ያገባኛል ባይነቱን አሳይቷል፣እያሳየ ነው፤ገልጿል እየገለጸ ነው።
ይህ መጥፎ አጋጣሚ ለተቃውሞ የፖለቲካ ትግሉ ይዞት የመጣው መልካም ሁኔታ እና ክስተት ይኸው ነው:፤ተባብሮ መጮህ!! የተባበረ ነጎድጓዳዊ ቁጣ!!
በእውኑ ከዚህ በላይ ወያኔን የሚያሸብር ዙፋኑን የሚያርድ ጉዳይ ከወዴት ይገኛል?? የትም።
የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ከቶ በምን አይነት አመክንዮ እና የታሪክ ምጸት ነው ወያኔን የመሰለ አንድ ተንቀሳቃሽ የሽፍታ ቡድን ተሰደን እንኳን መተንፈስ እንዳንችል አድርጎ ለ 23 ዓመታት ቀጥቅጦ እና አዋርዶ ሊገዛን የቻለው??
እራሳችን በዘር፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ከፍለን የተባበረ ክንዳችን የጋራ ጠላታችን ላይ ማንሳት ባለመቻላችን አይደለምን?? ነው እንጅ!!!
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል በዚህ ታሪካዊ ወቅት የታሪክ ጠርዝ ላይ ቆሞ የሚያስተላልፈው መልዕክት አለው፦
እስከመቸ ነው ጥቁሩን በሬ ጅብ ሲበላው ነጩ በሬ ሳይደንቀው፣ያጣማጁ ደም ሳይሸተው ፣ ነጩን በሬ ጅብ ሲከበው ጥቁሩ በሬ አደጋውን የነጩ ብቻ አድርጎት ጉዳዩን ችላ ሲለው በመጨረሻ ግን ሁለቱም የጅብ መንጋ ሲሳዮች ሲሆኑ ተረት እየተተረተብን የምንጓዘው???? ሃገራችን ጨርሳ እስክትጠፋ ማህበረሰባችን እስኪበተን ነውን?? ብዙዎቻችን የምናውቀውን አንድ ታሪክ እዚህ ላይ ብንጠቅስ ያለንበትን ሁኔታ በተወሰነም ደረጃ ቢሆን ለማሳየት የሚረዳ ይመስለናል።ናዚ ወደ ስልጣን ሲመጣ እና የስልጣን ማማ ላይ ቆሞ የሚሰራውን እየሰራ በነበረበት ወቅት ላይ የወቅቱ የጀርመን ልሂቃን ዝምታ የገረመው አንድ አስተዋይ ታላቅ ሰው ይህን ታዝቦ ነበር፦
በቅድሚያ ኮሚንስቶች ላይ አነጣጠሩ
የዚያን ጊዜ ኮሚንስት ስላልነበርኩ ዝም አልኩ
ቀጥለው በሶሻሊስቶች ላይ አነጣጠሩ
የዚያን ጊዜ ሶሺያሊስት ስላልነበርኩ ዝም አልኩ
ለጥቀው ወደ ሰራተኛው ማህበር አነጣጠሩ
የዚያን ጊዜ የሰራተኛው ማህበር አባል ስላልነበርኩ ዝም አልኩ
በመጨረሻ ወደ እኔ መጡ በዚያን ጊዜ ለኔ የሚጮህልኝ አንድም ሰው አልተረፈም ነበር።
እስከመቼ ነው አንዳንችን ለአንዳችን እና ተባብረን እንዳንጮህ የዘር፣የእምነት እና የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት አሎሎ ትናጋችን ውስጥ ተቀርቅሮ በጩሀት እንኳን እንዳንደጋገፍ የሚያንቀን???? በ እውኑ ከላይ የተቀመጠው ትዝብት በትክክል ወቅታችንን አያንጸባርቅምን??!
ስለዚህ የአንዳርጋቸው መታገት እና ለወያኔ ተላልፎ መሰጠት የፈጠረው የአንድነት ስሜት በስርዓት ተኮትኩቶ በፍጥነት ፋፍቶ ወያኔን ወደመጣል እና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የመገንባት ዋና ዓላማችን ድረስ ሊወስደን ይገባል።ምንድን ነው የምንጠብቀው? እንዴትስ ነው በዚህ ደረጃ ያፍዝ ያደንግዝ የተደገመብን?? ምን ዓይነት የመንፈስ ክሽፈት ነው እግር ከዎርች ያሰረን??
ምናልባት የምናሳድጋቸው ልጆች ይኖሩናል።አንዳርጋቸውም እኮ እንደሰው የወለዳቸው ህጻን ልጆች አሉት ።አንድም ቀን አብሯቸው ውሎ አያቅም እንጅ። እዚህ በረሃ ውሃ እና ትርፍ ስዓት ሲገኝ የታጋዩን ልብስ የሚችለውን ያህል ያጥብ ነበር፣ የልጆቹን ልብስ እንዳላጠበ ግን እርግጠኝ ሆኖ መናገር ይቻላል:፡ ከ ዓመት በላይ በረሃ ውስጥ ከረሃብ እና ጥም ጋር ሲታገል ልጆቼ የሚል ቃል ካፉ ወጥቶ አያቅም ። እንደሰው ልጆቹን ስለማይናፍቅ ግን አይደለም። ለዚች መከረኛ ሃገር ሙሉ ራሱን ስለሰጠ የልጅና የቤተሰብ ናፍቆት የመሰሉ ሰዋዊ ፈተናዎችን ታላቅ ራዕይን በሰነቀች ልቡ ውስጥ አስቀምጦት እንጅ። እና አንዳርጋቸው ልጆቹን ስለሚጠላ አይደለም የት እንደሚሄድ እንኳን ሳይነግራቸው ወደ በረሃ ሹልክ ያለው። ልጁን ማን ይጠላል!! የአንዳርጋቸው ጭንቀት ልጆቻችን ያለ ሃገር ወልደናቸው ምን ሊሆኑ ነው የሚል ነበርና ሃገር ሰርቶ፣ ማህበረሰብ ገንብቶ የማስረከብ ስራውን ቅድሚያ ሰጠው።
ምናልባት ሃብት፣ ትዳር ይኖረን ይሆናል። ግን ያለሃገር እና ያለነጻነት ሃብትና ትዳር ምንምን ይላል?? ይጣፍጣል?? አይመስለንም።በዘርህ እና በፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነትህ ምክንያት ከሞያሌ አሜሪካ፣ ከጎንደር አውስትራሊያ፣ ከጋምቤላ ካናዳ ድረስ በምትሳደድበት እና በምትታደንበት ሁኔታና ዘመን ውስጥ እስከ አፍንጫ ተነክሮ ሃብትና ትዳር ምንድን ናቸው?? ምናልባት እንደቀንድ አውጣ ራሳችንን የምንቀብርባቸው ቅርፊቶች ካልሆኑ በስተቀር። አንዳርጋቸው ለዚች ጣጣዋ ያላላቀ ሃገር፣ለዚች የምትንገላታ ባንዴራ ኪሱ ውስጥ 5 የአሜሪካን ዶላር እስኪቀረውና አላላውስ እስኪለው ኢትዮጵያዊ እምነቱን ለመግለጽ፣ለማስተማር፣ ለመቀስቀስ ዞሯል ወጥቶ ወርዷል።
ምናልባት_________እያልን ብዙ እንደምክንያት የሚጠቀሱ ነገሮችን ስንደረድር ልንውል እንችላለን። አንድን ሃገር እና ትውልድ ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋ እየጣረ ያለ ስርዓትን በግልጽ እስከ ህይወት መስዋዕትነት ላለመታገል ብዙ ምክንያት እያነሳን ራሳችን ልንሸነግል እንችላለን። ከቁም ሞት እያዳነን አይደለም እንጅ!!
ከቶ በምን ዓይነት ተፈጥሯዊ ወይ ሰው ሰራሽ ተጠየቅ ይሆን አንድ የሽፍታ ቡድን 97 ሚሊዮን ህዝብ ለ 23 ዓመታት አምበርክኮ ለገዛ የሚሞክረው?? ለቆመ አይደለም ለሞተ የሚገርም ጉድ አይደለምን?? ከዚህ በላይ አሳፋሪ ነገርስ በየትኛው የዓለም ጫፍ ቢታሰስ ይገኛል??? ይህ አዋጅ ለተደራጁ የፖለቲካ ሃይሎች ብቻ አይደለም፣ ለሲቪክ ተቋማት ብቻ አይደለም፣ ለወጣቱ ሃይል ብቻ አይደለም፣ ለወንዶች ብቻም አይደለም። ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የታወጀ አዋጅነው። ተነስ !!! መሳሪያ አንሳ !!! ወያኔን በጉልበትህ ከራስህ ላይ አውርድ!!! የመከራ እና የውርደት ዘመን ይብቃ !!! ያለበለዚያ ሁለት ምርጫዎች እጃችን ላይ አሉ፦ አንድ በጋራ ታግለን ነጻነታችን ማዎጅ ሁለት ባርነትን መርጦ ፣ባርነትን ተቀብሎ እንደባሪያ መገዛት!! በቃ !!
አንድ አለመሆናችንን የታዘቡ እናም የናቁን፣ በየስርቻው መወሸቃችንን የተገነዘቡ እናም የተጸየፉን የተጻፈ እና ያልተጻፈ የረጅም ጊዜ ፖሊሲ ያላቸው የብሄራዊ ቤተሰብ ምስረታ ሂደታችን አደናቃፊ ብሄራዊ ጠላቶቻችን ነጻነታችንን ስለማይፈልጉ ቅኝ ገዝዎቻችን ሌት ተቀን እየተባበሯቸው ነው። የሚፈልጉትን ሰው አንስተው እየሰጧቸው ነው።
እልፍ አዕላፍ ኢትዮዮጵያዊያን ከተጠጉበት እየታደኑ ለእርድ ሲቀርቡ ይሀው ድፍን 23 ዓመት ሞላን። አንዱ ከሆነ ሃገር ሲያዝ እና ተላልፎ ሲሰጥ እንደነጩ በሬ የጓዳ አጋራችን ደም አልከረፋ ሲለን፣ እኔ ምን አገባኝን ስንቀኝ፣ይህ እኮ የኮሚኒስቶች ጉዳይነው፣የነከበደ ጣጣ ነው እዛው ይወጡት ስንል በየተራ እየተለቀምን እያለቅን ነው።
አንዳርጋቸው ለዕርድ ቀርቧል!!ምናልባት ታሪካዊ ጠላቶቻችን የእርድ ቢላዎቻቸውን ስለው ደም በቋጠረ የበቀል አይን ከበው እያዩት ይሆናል።ሊያርዱት!!እንደታሳሪ ፈርቶ ሳይሆን መልካም ስራ ሰርቶ ክርስቶስ/አላህ ዙፋን ፊት እንደቀረበ ጻድቅ በኩራት ቆሞ አንገቱን እንደሚሰጥ ግን ጥርጥር የለንም። ታዲያ የኛ አዋጅ አንኳር መልዕክትም ያለው እዚህ ጋር ነው። አንዳርጋቸው በየሰርጡ እና በየእርሻው እየዞረ የዘራው የአንድነት፣ የኢትዮጵያዊነት፣ የነጻነት፣ የፍትህ ፣የዴሞክራሲ ዘር የሱ በድን ላይ ይብቀል፣ደሙን ጠጥቶ ይፋፋ ከሱ በኋላ ግን ይብቃ የሚል ነው። ኢትዮጵያዊዪ አንድ ሆኖ ተቆጥቶ እንደ አንበሳ ያገሳ ዕለት የሰሜን ነፋስ እንደነካው ጉም በነው እንደሚጠፉ እናውቃለን።ያውቃሉ። ማድረግ ያቃተን ተደጋግፈን መቆም፣ እጅለ እጅ መያያዝ፣ አንድ ላይ መጮህ አንድ ላይ የቁጣ ክንዳችን መሰንዘር ብቻ ነው። ታዲያ ካሁን በኋላ የአንዳርጋቸውን አንገት የቆረጠ ካራ ለሌሎች ተረኞችም ተስሎ እንዲቀመጥ እንፈልጋለን?? የማንፈልግ ከሆነ እጆቻችንን እርስ በርስ አጣምረን መብረቅ እናስተፋቸው፣ ነጎድጓድ እንሙላቸው። ከዚያ ውጤቱን በታሪክ ገጽ ላይ ጎልቶ ተጽፎ እናየዋለን። ያለበለዚያ ኢትዮጵያዊያን የለንም ጨርሰን ጠፍተናል ማለትነው። ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ አዋጅ አዋጅ፣ ልብ ያለው ልብ ይበል፣ ጆሮ ያለው ይስማ !!!ምታ ነጋሪት ክተት ሰራዊት ሳትጠፋ ጠላቶችህን አጥፋ !!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

No comments:

Post a Comment