Translate

Monday, July 21, 2014

’’የነብርን ጂራት አይዙም ከያዙም አይለቁም’’!

’’የነብርን ጂራት አይዙም ከያዙም አይለቁም’’!

ከአየነው ብርሃኑ

የኢትዮጵያ ህዝብ አዋቂ ነው ታጋሺም ነው። ቸኮሎ ለዉሳኔ አይነሳም የፊቱን የኋላዉን የቀኙንም ሆነ የግራዉን የማየት ነገሮችንም የማመዛዘን ብቃቱ አለዉ።
ለዚህም ነው እነዚህ ጥቂት የዘር ልክፍት የተጠናዎታቸዉ ጥቂት የትግሬ ዘረኞች በዘር መከፋፈል የዘላለም ገዢንታችንን ያረጋግጥልናል በሚል ከንቱ  ተስፋ  በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ የዘመቱት።
እኛ እየናቅናቸዉ እነሱ እየፈሩን ይኸዉ ሩብ ዓመት ሞላቸዉ።የፈሪ በትራቸዉን ያለ ርህራሄ ኣሳረፉብን አሳደዱን ፤ ሲፈልጉ በመርዝ ስያጠፉን ፤እንዲያም ሲል በአደባባይ ሲረሽኑን ይኸው ድፍን ሩብ ምዕተ ዓመት ሊሞላ ነው።

በሰዉ ለጅ ያዉም ደግሞ በ21ኝዉ ክፍለ ዘመን ይፈጸማል ተብሎ የማይታሰብ ግፍ በዚች ጥንታዊትና በለታሪክ ሀገር ተፈጸመ።
ጨዋና ኩሩዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የሰዉ ልጅ ይሸከመዋል ተብሎ ሊታሰብ የማይችል ግፍ ተፈጸመበት። ግፉም ሞልቶ መፍሰስ ከጀመረ ቆይቶአል።
ዛሬ  ግን በቃ የመጨረሻዉ መጀመሪያ ላይ ደርሰናል ክብር እነሱ እንደ ሻማ እየቀለጡ ለዚህ ጊዜ ላደረሱን ጀግኖቻችን !!!
አንዳርጋቸዉ ጽጌ ዕድሜዉን ሙሉ ለአገሩ አንድነት ለወገኑም ነጻነት የታገለ እና እያታገለ ያለ የ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያዊ ጀግና ነዉ። የዜግነት ግዳጁን ባግባቡ የተወጣ የትዉልድ ፈርጥ !!!!
አንዳርጋቸዉ ተግባሩን አጠናቋል ። የቀረዉ የእያንዳንዳችን ኢትዮጵያዊ ነን የምንል ዜጎች ድርሻ ነው።
ይኸን ሃላፊነት ለመዎጣት ቆርጦ የተነሳዉ  በሀገር ዉስጥም ይሁን በዉጭ ሃገር ያለ ኢትዮጵያዊ እያሳየ ያለዉ ከዎያኔ ጋር አንገት ለአንገት የመተናነቅ ዝግጅት እዉነትም በኢትዮጵያዊንታችን እንድንኮራ ያደርገናል። የመጨረሻዋ ቀን ስትደርስ ኢትዮጵያዊ ያዉ ኢትዮጵያዊ ነዉና !!!
ወያኔ አንዳርጋቸዉን ለመያዝ ያልወጣበት ያልወርደበት የለም ። ለሰሚዉ የሚደንቅ የገንዘብ መጠን ከፍሎ አንዳርጋቸዉን በእጁ አስገባ። ይህ ድርጊቱ ግን አልፋና ኦሜጋ አልሆነለትም። ፈንጠዝያም አልፈጠረም ዪልቁንም ሊዎጣ በማይችለው አዙሪት ዉስጥ ከተተዉ እንጂ ።
ወያኔዎች አንዳርጋቸዉን እንዲሚያዉቁት ሁሉ እሱም ጠንቅቆ ያዉቃቸዋል። በመሆኑም አንዳርጋቸዉን በማሰቃየት መረጃ እናገኛለን ማለት ድንጋይ ፈልጦ ከንንጋይ ዉሓ መጠበቅ ሆኖባቸዋል ።
በዓለም ያሉ የማሰቃያ መሣሪያ ዓይነቶችን ሁሉ እንደተጠቀሙ መረጃዎች አሉ ። በአንጻሩ ግን ጠብ ያለ ነገር የለም።
በሌላ በኩል ትግሉ በሀገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ ሀገር እንዲቀጣጠል አደረጉት ። ለ23 ዓመታት የዘሩት በዘር የመከፋፈል አሺክላ ተሰበረ።
ዛሬ ትግሉ የአንዳርጋቸዉ ብቻ አይደለም። የግንቦት 7 ብቻም አይደለም ። ኢትዮጵያዊ ነኝ የአገሬ ድቀት የወገኔ ብሶት የኔም ነው። የትዉልድ አደራ አለብኝ ብሎ ለሚያምን ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንጂ !!
ለዚህም ነው የወያኔ አንዳርጋቸዉን መያዝ ደስታ ሳይሆን  ሃዘን ድል መሆኑም ቀርቶ ወደ ዉድቀት ያመራዉ።
ውያኔ ዛሬ አንዳርጋቸዉን መያዙ ትክክል ነዉ የለም ትክክል አይደልም በሚል ጉንጭ አልፋ ክርክር እንደተጠመደና አስሮ ማቆየትም ሆነ አሁን ባለበት ሁኔታ ፈቶ መልቀቅ ድምር ዉጤታቸዉ ከዉድቀት እንደማያድኑት ከድምዳሜ ለይ እንደደረሰና የዉሃ ላይ ኩበት እንደሆነ መገመት አያዳግትም።
የነብርን ጅራት አይዙም፤ ከያዙም አይለቁምና !!
የግንቦት 7 ሊያስብባቸዉና ማከናዎን ያለበት  ሁለት አስቸኳይ ተግባራት አሉ ።
የመጀመሪያዉ የመጨረሻዉ የዎያኔ ካርድ አንዳርጋቸዉን በድብቅ እንደያዘ የእንደራደር ጥያቄ ሊያቀርብ እንደሚችል ከግምት ዉስጥ በማስገባት ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ ግንቦት 7 በአንድም ይሁን በሌላ የትዉልድ አደራ ተሸካሚ ሆኖአል።
በዚህም ትግልን የማስተባበር አቅሙን በማጎልበት ትግሉ የሚጠይቀዉን ጊዜ ማሳጠር በወያኔ ምክንያት ሊደርስ የሚችለዉን ጥፋት መቀንሰ ድርጅታዊ አቅሙን  በማጎልበት የመሪነት ሚናዉን በአግባቡ መወጣት ይኖርበታል።
ይህን ለማድረግ የቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ሥራ በስፋት መሠራት ዪኖትበታል። ዛሬ ዎያኔ የመዉደቂያ ቀኑን ከመጠባበቅ በስተቀር ሌላ የለዉም ። ለዉጊያ የተዘጋጀዉ ጦር እየከዳዉ ለክፉ ቀን ያስቀመጣቸዉ ቅልቦች ፊታቸዉን እያዞሩበት በመሆኑ ይህን ህዝብ ማወቅ አለበት። ከባድሜ አካባቢ ብቻ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ ያዉም አንዲት ጥይት ሳትተኮስ ከአንድ ሺህ ወታደር በላይ ከዳ ማለት ያች የቁርጥ ቀን ስትደርስ ዉጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት ጠንቋይ ወይም ነብይ መሆንን አይጠይቅም።
ስለዚህ የፕርፕፓጋንዳ ሥራ ጉድለት የመረጃም ክፍተት ይታየኛል እና ለትግል የትሰለፈ ሁሉ በዚህ መልክ የርድሻዉን ዪወጣ!!!
በመጨረሻም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተለይም ለግል ጥቅሙ ቅድሚያ በመስጠትና ከወያኔ የሚወድቅለትን ፍርፋሪ ተስፋ በማድረግ ማደናገር ጊዜዉ ያለፈት የአበባየ ሆይ ጨዋታ መሆኑን ማወቅ አለበት። መርጫዉ አንድ በቻ ነውና።
ከዘረኞች ጎን በመቆም ኢትዮጵያን እና እትዮጵያዊነትን መዋጋት
ወይም ደግሞ
የኢትዮጵያንና  የኢትዮጵያኒነትን ክብር ለመመለስ፤ ዉርደት በቃ፤ በደልም በቃ በሚል መንፈስ ትግሉን መቀላቀል !!
ምርጫዉ የአንተዉ/ችው ነው። ድሉ  ግን አይቀሬ መሆኑን አትጠራጠር/ሪ !!!
የአንዳግጋቸዉ ዉጥን ከግብ ማድረስም ብቻ አይደልም ።
አንዳርጋቸዉን ከወያኔ እጅ ፈልቅቀን እናወጣዋለን !!!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!!!

No comments:

Post a Comment