Translate

Monday, July 21, 2014

ቀጭኗ፤ ፖለቲከኛ ሀሙስ ፍርድ ቤት ትቀርባለች፤ እና ሌሎች ቀጫጭን መረጃዎች

983744_10152978488915830_7057766400299394261_nAbe Tokchaw
ወይንሸት ሞላ የሰማያዊ ፓርቲ አባል እና የወጣቶች ጉዳይ ውስጥ አመራር ላይ ካሉት ሃላፊዎች አንዷ ነች። ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ ሲገልጻት ”ቀጭን እና ጠንካራ” ይላታል። ይቺ ልጅ አርብ እለት (ጁምዓ) በአንዋር መስጊድ ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶቻችን ሰላማዊ ጸሎት ለአላህ፤ እና ሰላማዊ ተቃውሞ ለመንግስት በሚያሰሙ ጊዜ የመንግስት ታጣቂዎች ያገኙትን መደብደብ እና ማፈስ ሲጀመሩ ወይ ጉዳዩን ለመታዘብ ስትበር በቦታው ተገኝታ፤ አልያም በአጋጣሚ በአንዋር መስጊድ አካባቢ ስታልፍ ብቻ ለጊዜው ለዚህ ዜና ጸሀፊ ግልጽ ባልሆነ አጋጣሚ አንዋር መስጊድ አካባቢ ከዚህ በፊት ይከታተላት የነበረ ደህነነት አያት፤ ከዛም ለቀም አድርጎ እየደበደበ ከፖሊሶች ጋር ተባብሮ ወሰዳት። ከዛም ማንም የርሷ ወገን ባልተገኘበት ፍርድ ቤት አቀረቧት፤ ይቺ ቀጭን ወጣት እና ጠንካራ ፖለቲከኛ ዳግም ለሐሙስ ሐምሌ 16 ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኝ ፍርድ ቤት ትቀርባለች።
10526174_10202973686676502_6338511177552984735_nሌላ የፎቶ ጋዜጠኛ የሆነችው አዚዛ መሃመድ የፎቶ ካሜራ ለአዲስ ጉዳይ መጽሄት ዘገባ በአንዋር መስጊድ ባለፈው አርብ የተፈጸመውን ድርጊት በካሜራዋ ስታነሳ በመገኘቷ የመንግስት አሳሪዎች አስርዋታል። አዚዛም ማንም በሌለበት ፍርድ ቤት የቀረበች ሲሆን አሁንም ሀሙስ ሃምሌ አስራ ሰባት በቂርቆስ ከፈለከተማ ምድብ ችሎት ከሌሎች በርካታ ታፍሰው የተወሰዱ ንጹሃን ጋር ዳግም ፍርድ ቤት ልትቀርብ ቀጠሮ ተይዞላታል።

ሌላ ሀምሌ አስራ አንድ የመንግስት ታጣቂዎች በሰላማዊው ጸሎተኛ እና ሰላማዊ ተቃዋሚ ህዝብ ላይ ያደረሱት ድበደባ አፈሳ እና ማሰቃየት ”ጥቁር ሽብር” የሚል ስያሜ እንደተሰጠው የድምጻችን ይሰማ ልጆች ነግረውኛል።
ሌላ ቅድም ያልኳችሁ የመሬ ነገር የምር መሆኑን ከመሬ አረጋግጠውልኛል። መሬ እምቢኝ ብሏል! (የከፋ ጉዳት ተወዳጇ መሬ ላይ እንዳይደርስ መጸለይ አትርሱ!) ኢህአዴግ ሰው ብትሆን ይሄ አይነቱ ነገር ሲገጥማት ጦሯን ወደ መሬ ከማዝመቷ በፊት ለሚ ላይ ቁጭ አድርጌ ብመክራት ደስ ይለኝ ነበር። ህዝብ ካመረረ ጥይት ሳይሆን ጸሎት ነው መፍትሄው እላት ነበር። ችገሩ ኢህአዴግ ሰው አይደለችም ግንባር ነች እንጂ… ለዛውም ቴስታ ካልተማታ የሚታመም ግንባር!

No comments:

Post a Comment