Translate

Wednesday, July 2, 2014

የአንዳርጋቸዉ ፅጌ መታሠር

ግንቦት ሰባት እንደሚለዉ የብሪታንያ ዜግነት ያላቸዉ አቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌ ባለፈዉ ሳምንት ሰኞ የመን አዉሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በፀጥታ አስከባሪዎች ከተያዙ በኋላ ያሉበት ሥፍራና ሁኔታ አይታወቅም

የአንዳርጋቸዉ ፅጌ መታሠር
በሥደት የሚገኘዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲ ግንቦት ሰባት የመን ዉስጥ የታሠሩትን ዋና ፀሐፊዉን አቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌን ለማስፈታት የተለያዩ ዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ ዘመቻዎች መጀመሩን አስታወቀ።አንድ የግንቦት ሠባት ባለሥልጣን እንዳስታወቁት አቶ አንዳርጋቸዉን ለማስለቀቅ የብሪታንያ ዲፕሎማቶችም እየጣሩ ነዉ።በለንደን የየመን ኤምባሲም ጉዳዩን እየተከታተለዉ መሆኑን አስታዉቋል።ግንቦት ሰባት እንደሚለዉ የብሪታንያ ዜግነት ያላቸዉ አቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌ ባለፈዉ ሳምንት ሰኞ የመን አዉሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በፀጥታ አስከባሪዎች ከተያዙ በኋላ ያሉበት ሥፍራና ሁኔታ አይታወቅም።የለንደንዋ ወኪላችን ሐና ደምሴ ዝርዝር ዘገባ ልካልናለች
ሐና ደምሴ
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ

No comments:

Post a Comment