Translate

Wednesday, July 9, 2014

ሶስቱ አምባገነኖች (እየሩሳሌም አርአያ)

አገሪቱ በሶስት ሰዎች ቁጥጥር ስር እንደወደቀችና አሁን እየተካሄደ ያለው የጅምላ እስርና ድብድባ በነዚህ የሕወሐት ባለስልጣናት ትእዛዝ እየተፈፀመ እንደሚገኝ ታማኝ የቅርብ ምንጮች አረጋግጠዋል። የፌዴራል ደህንነት መሪ ፀጋዬ በርሔ (ሃለቃ)፣ የደህንነት ሃላፊ ጌታቸው አሰፋና ጄ/ል ሳሞራ የኑስ ሲሆኑ፣ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ታፍነው እንዲወሰዱና በዛሬው እለት አብርሃ ደስታን ጨምሮ ሃብታሙ አያሌውና የሺዋስ አሰፋ እንዲሁም ሌሎች የተቃዋሚ አመራር አባላቶች የሃይል ጥቃት እየተፈፀመባቸው እስር ቤት እንዲገቡ ማድረጋቸውን ምንጮቹ ገልፀዋል። አብርሃ ደስታ በፌዴራል ፖሊሶች ተይዞ ሲወሰድ ከፍተኛ ድብደባ የተፈፀመበት ሲሆን በመቀሌ በሚገኙ እስር ቤቶች ውስጥ እንደሌለና ወዴት እንደተወሰደ እንደማይታወቅ ምንጮች ከስፍራው አረጋግጠዋል። ይህ ሁሉ ጥቃትና የመብት ረገጣ እየተከናወነ ያለው በሶስቱ አምባግነኖች መሆኑን ያስታወቁት ምንጮቹ አክለውም እስር፣ ድብደባና ድራማ በመስራት የስልጣን እድሜን ማራዘም አይቻልም ብለዋል። የኢትዮጵያ ነገር ያበቃው በነሃለቃ ፀጋይ በርሄ (ደናቁርት) መመራት የጀመረች እለት ነው- ሲሉ አክለዋል።

No comments:

Post a Comment