Translate

Sunday, May 25, 2014

<< ለሰፊው ህዝብ ጥቅም >> የተቆጣጠርነው ሬዲዮ ጣቢያ የት ሄደ ?

( አሌክስ አብርሃም )
Photo: << ለሰፊው ህዝብ ጥቅም  >> የተቆጣጠርነው ሬዲዮ ጣቢያ የት ሄደ ?
( አሌክስ አብርሃም )

የዛሬ 23 አመት (ጊዜው እንዴት ይሮጣል ) የአንድ ታጋይ አጭር ንግግር የኢትዮጲያን  አየር ሞላ  እንዲህ ሲል ….
‹‹ የጭቁን ህዝብ ብሶት የወለደው  ጅግናው  የኢህዴግ ሰራዊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የአዲስ  አበባ የሬዲዮ ጣቢያ ለ(((ሰፊው ህዝብ ጥቅም )))ተቆጣጥሮታል !! ግንቦት 20  ሽ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት  ዓመተ ምህረት ! ›› ወዲያው ‹‹አሳ በለው በለው ›› የሚል ሙዚቃ ተከተለ (አሳና የትጥቅ ትግል ምን እንደሚያገናኛቸው ባይታወቅም አሳ በለው ሞቅ ብሎ ተሰማ . . . ምናልባትም እንደባህር የሰፋችው አዲስ አበባ ውስጥ  ታጋዮች አንደአሳ ነባሪ በነፃነት መዋኘታቸውን ለመጠቆም እንደሆነም እንጃ  ) 

እንግዲህ ኢህዴግ  የሬዲዮ ጣቢያውን  ለሰፊው ህዝብ ከመቆጣጠሩ በፊት  ሬዲዮ ጣቢያው ‹‹የሰፊው ህዝብ ›› እንደነበር ደርግም ሲናገር ነው የኖረው ! ከሰፊው ህዝብ መጠቀሚያነት ወደሰፊው ህዝብ መጠቀሚያነት የተላለፈው ሬዲዮ ጣቢያ ግን ከሰፊ የመንግስት ፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያነት ወደ በጣም ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ድምፅ ማጉሊያነት ከመተላለፍ ያለፈ ምንም ለውጥም እድገትም አላሳየም !   
  
በደርግ ጊዜ  ‹‹ልጅህን  ለብሄራዊ ውትድርና  ላክ ›› ሲባል ህዝቡ እንዲህ ይል ነበር  ‹‹እኛ ልጆቻችንን እሳት ውስጥ መማገድ አንፈልግም ››  ሬዲዮው  ግን  ህዝቡ ያላለውን  እንዲህ በማለት ዜና ያውጅ ነበረ  ‹‹ ሰፊው የኢትዮጲያ ህዝብ  ተገንጣይ ወንበዴን ለማደባየት ልጆቹን  ሃብቱን ለመስጠት ቃል ገባ !! ›› 
‹‹ ምንም የማያውቁ ልጆቻችንን በግፍ ረሸናችሁብን ›› ሶል ህዝቡ ሬዲዮው ‹‹ ፀረ አቢዮተኞች ላይ የህዝብና የአቢዮት ጠላት የሆኑት ላይ ርምጃ ተወሰደ ›› ህዝቡ ግራ ገባው !  ሃቁን ፍለጋ  ደበቅ ብሎ ከጫካ የምትተላለፈውን  የ‹‹ትሃት ››ን ሬዲዮ ማዳመጥ ጀመረ  እሷ መቶ ገደልኩ  ሶስት መቶ ማረኩ ስትል ያምናታል ….አገር የሚያስተዳድረው መንግስት ውሸታም ነበራ ! ገዡ ከዋሸ  ማንም ተነስቶ ህዝብን ውሸት ቢነግረው ያምናል ! ውሸት እንዲያምን የሚገደድ ህዝብ የሌሎችንም ውሸት የማያምንበት ምክንያት የለማ ! 

ኢህዴግ ስልጣን ላይ ወጣ …. ሬዲዮው ከአልጋ ስር ወጥቶ ጠረጴዛ ላይ ተቀመጠና  ህዝቡም ያለመሳቀቅ ማድመጥ ጀመረ ! ምን ያደርጋል  ህዝቡ ‹‹ኧረ ልጆቻችን ስራ አጡ ›› ሲል ሬዲዮው ‹‹ ወጣቱ ስራ ፈጥሮ ሃብት በሃብት ሆነ›› ማለት ጀመረ ! በቃ ይሄ ነገር ከቤቱ ነው ሬዲዮ  ጣቢያውን ጠበል እንርጨው   ወይም  ብሄራዊ ሬዲዮ ጣቢያችን  መሳሪያውን ነቅሎ ጫካ ይግባና  ከጫካ  ፕሮግራሙን  ያስተላልፍልን  እግራቸው ከተማ ሲረግጥ ነገር እየተበላሸ ነው ያሉም ነበሩ . . . 

በዛም በዚህም ሬዲዮው የሚያወራው  የመንግስትን ጉዳይ እንጅ የህዝብን እውነት አልሆን ቢለው ህዝቡ መለስ ብሎ ሰውየውን   ማሰብ ጀመረ የቱን ሰውየ  ? ኢሃዴግ  ሬዲዮ ጣቢያውን  ሲቆጣጠር  ብስራቱን ለህዝብ ያደረሰውን ነዋ ! እስቲ ይሄን ነገር እንስማው እያለ አባባሏን ተመልሶ አጤናት !
 የጭቁን ህዝብ ብሶት የወለደው ………..ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን አዲስ  አበባ የሬዲዮ ጣቢያ ለ(((ሰፊው ህዝብ ጥቅም )))ተቆጣጥሮታል !! 
‹‹ ወራጅ አለ››  እውነቱን እንነጋገር ከተባለ  ሰፊው ህዝብ  እስካሁንም ብሶቱን የሚናገርበት  ሬዲዮ ጣቢያ  የለውም ! የህዝብ የራሱ ልሳን   የሆነ  ቴሌቪዥን ጣቢያ የለውም !  ለሰፊው ህዝብ  ጥቅም  ኢሃዴግ የተቆጣጠረው ጣቢያ ሰፊውን  ህዝብ  በሰፊው የሚያጉርበት   ፖሊስ ጣቢያ ብቻ ነው !  እንደውም የሰፊው ህዝብ ጣቢያ ግንቦት 20 ሽ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት ‹በሽብር ተጠርጥሮ › የታሰረና  መንግስት ምርመራውን ስላልጨረሰ የሃያ ሶስት አመት የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀበት ተቋም ይመስላል !  

በእርግጥ መንግስቱ ሃይለማሪያም   ግልፍተኛ መሪ ነበሩ  ! ኢሃዴግ ግን የተረጋጋ መንግስቱ ሃይለማሪያም ሆነ !ፊት ለፊት ባያፍንም  አፋኝ ህግ ያወጣል …በማን አለብኝነት ያፀድቃል ! ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ መጥፎ ታሪክ  እየፈጠረና  ጥላቻ ይዘራል …ይህም ታሪካዊ ሃላፊነቱን የመወጣት ብቃት እንዳነሰው የሚያሳይ ድርጊት ነው ! ደርግ ‹‹በምስራቅ አፍሪካ አንደኛ የሆነ ጦር ገነባንልህ ›› እያለ ህዝቡ ጭቆናውን እንዳያነሳ ዝም ለማስባል የብድር መሳሪያ ሰልፍ እያሳየ እንደልጅ ህዝብን ሊያታልል እንደሞከረው ኢህዴግም በብድር የተሰራ  መንገድና ድልድይ እያሳየ አፈናውን በህዝብ ስም በሚመጣ የትውልድ እዳ ሊሸፍን ይሞክራል ! እና ኢህዴግ እንደስርአት የደርግን ስርአት ናፋቂ ሆኖብናል ! 

አሁንም ካለምክንያት ማሰር ምክንያት እያፈላለጉ ዜጎችን ስር ቤት መወርወርና ማንገላታት፣ማሸማቀቅ ፣ እና ማስፈራራት  በሰፈነበት  አገር ‹‹ሰፊው ህዝብ›› በብሶት የተረገዘ እንጅ ብሶት የወለደው ነፃነት አላጣጣመም ! መንግስት የጎረምሳ እድሜ ያለው ስልጣን ላይ ተፈናጦ ከትላንቱ ካልተማረ እየተድበሰበሰ  በሚታለፍ መሰረታዊ ችግር ውስጥ ፣ህዝብ በማይተማመንበት የፍትህ ስርአት ውስጥ ፣ የኑሮ ውድነት ሰማይ በነካበት ድህነት ውስጥ ሁነን ግንቦት ሃያን ስናስብ ….ትዝ የሚለን መስከረም ሁለት ነው !

አዎ  ግንቦት ሃያ የኢህዴግ መስከረም ሁለት ነው !! መንግስት  እራሱ  የደርግ ስርአት ናፋቂ ሆነብን እኮ !   ለማንኛውም ወደሰፊው ህዝብ  ሬዲዮ ጣቢያ የበአለ ዝግጅት አዘጋጆች ደውለን እንዲህ ማለት እያማረን ነው  ‹‹ ሃሎ  በአሉን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ለማስተላለፍ ነው . . . ለጓድ መንግስቱ ሃይለማሪያም ባሉበት . . . የተገረሰሱ ሳይሆን በምትከዎት ሰው አስቀምጠው ረፍት የወጡ ስለመሰለን እንኳን ስሙን ለቀየረው መስከረም ሁለት በአልዎት በሰላም አደረሰዎ  …አሳ በለው  በለው የሚለውን ዘፈን ይጋበዙልን ማ  ››የዛሬ 23 አመት (ጊዜው እንዴት ይሮጣል ) የአንድ ታጋይ አጭር ንግግር የኢትዮጲያን አየር ሞላ እንዲህ ሲል ….
‹‹ የጭቁን ህዝብ ብሶት የወለደው ጅግናው የኢህዴግ ሰራዊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የአዲስ አበባ የሬዲዮ ጣቢያ ለ(((ሰፊው ህዝብ ጥቅም )))ተቆጣጥሮታል !! ግንቦት 20 ሽ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት ዓመተ ምህረት ! ›› ወዲያው ‹‹አሳ በለው በለው ›› የሚል ሙዚቃ ተከተለ (አሳና የትጥቅ ትግል ምን እንደሚያገናኛቸው ባይታወቅም አሳ በለው ሞቅ ብሎ ተሰማ . . . ምናልባትም እንደባህር የሰፋችው አዲስ አበባ ውስጥ ታጋዮች አንደአሳ ነባሪ በነፃነት መዋኘታቸውን ለመጠቆም እንደሆነም እንጃ )
እንግዲህ ኢህዴግ የሬዲዮ ጣቢያውን ለሰፊው ህዝብ ከመቆጣጠሩ በፊት ሬዲዮ ጣቢያው ‹‹የሰፊው ህዝብ ›› እንደነበር ደርግም ሲናገር ነው የኖረው ! ከሰፊው ህዝብ መጠቀሚያነት ወደሰፊው ህዝብ መጠቀሚያነት የተላለፈው ሬዲዮ ጣቢያ ግን ከሰፊ የመንግስት ፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያነት ወደ በጣም ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ድምፅ ማጉሊያነት ከመተላለፍ ያለፈ ምንም ለውጥም እድገትም አላሳየም !

በደርግ ጊዜ ‹‹ልጅህን ለብሄራዊ ውትድርና ላክ ›› ሲባል ህዝቡ እንዲህ ይል ነበር ‹‹እኛ ልጆቻችንን እሳት ውስጥ መማገድ አንፈልግም ›› ሬዲዮው ግን ህዝቡ ያላለውን እንዲህ በማለት ዜና ያውጅ ነበረ ‹‹ ሰፊው የኢትዮጲያ ህዝብ ተገንጣይ ወንበዴን ለማደባየት ልጆቹን ሃብቱን ለመስጠት ቃል ገባ !! ››
‹‹ ምንም የማያውቁ ልጆቻችንን በግፍ ረሸናችሁብን ›› ሶል ህዝቡ ሬዲዮው ‹‹ ፀረ አቢዮተኞች ላይ የህዝብና የአቢዮት ጠላት የሆኑት ላይ ርምጃ ተወሰደ ›› ህዝቡ ግራ ገባው ! ሃቁን ፍለጋ ደበቅ ብሎ ከጫካ የምትተላለፈውን የ‹‹ትሃት ››ን ሬዲዮ ማዳመጥ ጀመረ እሷ መቶ ገደልኩ ሶስት መቶ ማረኩ ስትል ያምናታል ….አገር የሚያስተዳድረው መንግስት ውሸታም ነበራ ! ገዡ ከዋሸ ማንም ተነስቶ ህዝብን ውሸት ቢነግረው ያምናል ! ውሸት እንዲያምን የሚገደድ ህዝብ የሌሎችንም ውሸት የማያምንበት ምክንያት የለማ !
ኢህዴግ ስልጣን ላይ ወጣ …. ሬዲዮው ከአልጋ ስር ወጥቶ ጠረጴዛ ላይ ተቀመጠና ህዝቡም ያለመሳቀቅ ማድመጥ ጀመረ ! ምን ያደርጋል ህዝቡ ‹‹ኧረ ልጆቻችን ስራ አጡ ›› ሲል ሬዲዮው ‹‹ ወጣቱ ስራ ፈጥሮ ሃብት በሃብት ሆነ›› ማለት ጀመረ ! በቃ ይሄ ነገር ከቤቱ ነው ሬዲዮ ጣቢያውን ጠበል እንርጨው ወይም ብሄራዊ ሬዲዮ ጣቢያችን መሳሪያውን ነቅሎ ጫካ ይግባና ከጫካ ፕሮግራሙን ያስተላልፍልን እግራቸው ከተማ ሲረግጥ ነገር እየተበላሸ ነው ያሉም ነበሩ . . .
በዛም በዚህም ሬዲዮው የሚያወራው የመንግስትን ጉዳይ እንጅ የህዝብን እውነት አልሆን ቢለው ህዝቡ መለስ ብሎ ሰውየውን ማሰብ ጀመረ የቱን ሰውየ ? ኢሃዴግ ሬዲዮ ጣቢያውን ሲቆጣጠር ብስራቱን ለህዝብ ያደረሰውን ነዋ ! እስቲ ይሄን ነገር እንስማው እያለ አባባሏን ተመልሶ አጤናት !
የጭቁን ህዝብ ብሶት የወለደው ………..ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን አዲስ አበባ የሬዲዮ ጣቢያ ለ(((ሰፊው ህዝብ ጥቅም )))ተቆጣጥሮታል !!
‹‹ ወራጅ አለ›› እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ሰፊው ህዝብ እስካሁንም ብሶቱን የሚናገርበት ሬዲዮ ጣቢያ የለውም ! የህዝብ የራሱ ልሳን የሆነ ቴሌቪዥን ጣቢያ የለውም ! ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ኢሃዴግ የተቆጣጠረው ጣቢያ ሰፊውን ህዝብ በሰፊው የሚያጉርበት ፖሊስ ጣቢያ ብቻ ነው ! እንደውም የሰፊው ህዝብ ጣቢያ ግንቦት 20 ሽ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት ‹በሽብር ተጠርጥሮ › የታሰረና መንግስት ምርመራውን ስላልጨረሰ የሃያ ሶስት አመት የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀበት ተቋም ይመስላል !
በእርግጥ መንግስቱ ሃይለማሪያም ግልፍተኛ መሪ ነበሩ ! ኢሃዴግ ግን የተረጋጋ መንግስቱ ሃይለማሪያም ሆነ !ፊት ለፊት ባያፍንም አፋኝ ህግ ያወጣል …በማን አለብኝነት ያፀድቃል ! ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ መጥፎ ታሪክ እየፈጠረና ጥላቻ ይዘራል …ይህም ታሪካዊ ሃላፊነቱን የመወጣት ብቃት እንዳነሰው የሚያሳይ ድርጊት ነው ! ደርግ ‹‹በምስራቅ አፍሪካ አንደኛ የሆነ ጦር ገነባንልህ ›› እያለ ህዝቡ ጭቆናውን እንዳያነሳ ዝም ለማስባል የብድር መሳሪያ ሰልፍ እያሳየ እንደልጅ ህዝብን ሊያታልል እንደሞከረው ኢህዴግም በብድር የተሰራ መንገድና ድልድይ እያሳየ አፈናውን በህዝብ ስም በሚመጣ የትውልድ እዳ ሊሸፍን ይሞክራል ! እና ኢህዴግ እንደስርአት የደርግን ስርአት ናፋቂ ሆኖብናል !
አሁንም ካለምክንያት ማሰር ምክንያት እያፈላለጉ ዜጎችን ስር ቤት መወርወርና ማንገላታት፣ማሸማቀቅ ፣ እና ማስፈራራት በሰፈነበት አገር ‹‹ሰፊው ህዝብ›› በብሶት የተረገዘ እንጅ ብሶት የወለደው ነፃነት አላጣጣመም ! መንግስት የጎረምሳ እድሜ ያለው ስልጣን ላይ ተፈናጦ ከትላንቱ ካልተማረ እየተድበሰበሰ በሚታለፍ መሰረታዊ ችግር ውስጥ ፣ህዝብ በማይተማመንበት የፍትህ ስርአት ውስጥ ፣ የኑሮ ውድነት ሰማይ በነካበት ድህነት ውስጥ ሁነን ግንቦት ሃያን ስናስብ ….ትዝ የሚለን መስከረም ሁለት ነው !
አዎ ግንቦት ሃያ የኢህዴግ መስከረም ሁለት ነው !! መንግስት እራሱ የደርግ ስርአት ናፋቂ ሆነብን እኮ ! ለማንኛውም ወደሰፊው ህዝብ ሬዲዮ ጣቢያ የበአለ ዝግጅት አዘጋጆች ደውለን እንዲህ ማለት እያማረን ነው ‹‹ ሃሎ በአሉን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ለማስተላለፍ ነው . . . ለጓድ መንግስቱ ሃይለማሪያም ባሉበት . . . የተገረሰሱ ሳይሆን በምትከዎት ሰው አስቀምጠው ረፍት የወጡ ስለመሰለን እንኳን ስሙን ለቀየረው መስከረም ሁለት በአልዎት በሰላም አደረሰዎ …አሳ በለው በለው የሚለውን ዘፈን ይጋበዙልን ማ ››

No comments:

Post a Comment