Translate

Tuesday, May 6, 2014

73ኛውን የአርበኞች ቀን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ሚያዚያ 27/2006 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ታላላቅ አርበኞች በተገኙበት ደማቅ የመታሰቢያ ፕሮግራም ተካሄደ

ይድነቃቸው ከበደ

Addis Ababa Ethiopian patriots day 2014
ዘሬ ከ8 ሰዓት ጀምሮ እስከ 11፡30 ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፣አቶ አበባው አያሌው፣አቶ ፍፁም ወ/ማርያም ፣ ተሾመ ገ/ማርያም እንዲሁም አቶ ታዲዎስ ታንቱ በጀግኖች አርበኞች ገድል እና ማንነት ዙሪያ ያደረጉት ገለፃ እና ውይይት እጅግ ማራኪ እና ቀልበ የሚስብ ነበር፡፡
በተልይ በጀግኖች ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ታሪክ አፃፃፍ እና ገለፃ ላይ የሚታዩ ችግሮች ለማረም ተብሎ በተነሳው አሳብ ላይ ከላይ በገለፅኳቸው ሰዎች መካከል የነበረውን የመፍትሔ አሳብ አቀራረብ በቦታው ለነበርነው ሁሉ እጅን አፍ ላይ አስጭኑ የሚያስቀር ተናጋሪዎቹ ሲጨርሱ ቀልብ በሚስብ ከልብ በመነጨ ከበሬታ በጭብጨባ የታጀበ ነበር፡፡ በተለይ ዶ/ር ዳኛቸው በሳቅ እያዋዛ የሚያቀርባቸው አሳቦች ሁሌም የሚናፈቁ ናቸው፡፡ በክብር እንግድነት የተገኙት ዶ/ር ያቆብ ኃ/ማርያም እንዲሁም ወጣቱ ፓለቲከኛው እና ደራሲ በቅርብ አንድነት ፓርቲ የተቀላቀለው አቶ አስራት አብራሃ የተገኙ ሲሆን የሰማያዊን ፓርቲ ጥሪ የተቀበሉ እንዲሁም የፓርቲው አባላቶች የአስደሳች ጊዜ ተጋሪ ናቸው፡፡
የደስታው ምንጭ ደግሞ አንገታችንን ቀና አድርገን በኢትዮጵያዊነታችን እንድኮራ ላደረጉን ሁሌም በክብር የምንዘክራቸው ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ናቸው፡፡ ዛሬ ቀኑ የአርበኞች ቀን ነው! አርበኝነት ሲታሰብ ደግሞ ጃገማ ኬሎ በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዘንድ የሚታወሱ ናቸው፡፡ ጀገና አርበኛ ጃገማ ኬሎ በህይወት ከቆዩልን መካከል እርሳቸው አንዱ ናቸው፤ በዛሬው እለት ኢትዮጵያዊ ጀግና አርበኛ ጃገማ ኬሎ በተገኙበት ስለ አርበኞች የተደረገው ውይይት እና ገለፃ ትምህርት ሰጪነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ አስደሳችነቱ ደግሞ ልዩ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው ካዛንቺስ በሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ ፅ/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ነው !
ክብር ለጀግኖች አርበኞቻችን!!!
Ethiopian patriots day celebration in Addis Ababa (Photo: Semayawi party)
Ethiopian patriots day celebration at Semayawi office

No comments:

Post a Comment