Translate

Monday, February 17, 2014

'' ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈን የማንሰጥ ለመሆናችን ዋስትና እና ጥገኝነት እንዲሰጠን እንፈልጋለን'' የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጠለፋ ጉዳይ (latest)

 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው የተጠለፈው አይሮፕላን 

-ከ አዲስ አበባ ወደ ሮም ይበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 702 ጄኔቭ ላይ ዛሬ የካቲት 10/2006 ዓም በማዕከላዊ የአውሮፓ ሰዓት ከማለዳው 12 ከ 02 ሲሆን  እንዲያርፍ ተገዷል።

-  ሁሉም ተሳፋሪዎች እና አይሮፕላኑም በደህና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።

- ለ 2 ሰዓት ከ 45 ደቂቃ ተዘግቶ የነበረው የጀኔቭ አየር ማረፍያ  ተመልሶ ተከፍቷል።

- ጠላፊው ረዳት አብራሪው ነው።

- ዋና አብራሪው ወደ ሽንት ቤት ሲሄድ ረዳቱ ሽንትቤቱን ቆለፈበት እና አይሮፕላኑን ጠለፈው።

- አብራሪው ካለ አንዳች ማንገራገር እጁን ለስዊዝ ፖሊስ ሰጥቷል።ጥገኝነት እንዲሰጠውም ይፈልጋል።

- አይሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት ተሳፋሪዎች 143ቱ ጣልያናውያን ናቸው።

- ''ዘ ሎካል'' የተሰኘው የስዊዝ ጋዜጣ ዛሬ እንደዘገበው በስዊዘርላንድ ሕግ መሰረት ወንጀሉ እሰከ 20 አመት እስር ሊዳርግ ይችላል።

- ''ዘ ሎካል''  ጋዜጣ  አክሎም በድረ-ገፁ ላይ የጠላፊውን ቃል በድምፅ እንዲህ ሲል አሰምቷል '' ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈን የማንሰጥ ለመሆናችን ዋስትና እና ጥገኝነት እንዲሰጠን  እንፈልጋለን''
''The local'' Switzerland news paper http://www.thelocal.ch/20140217/ethiopian-plane-lands-in-geneva-after-hijacking

ጉዳያችን
የካቲት 10/2006 ዓም 

No comments:

Post a Comment