Translate

Friday, February 28, 2014

የዩናይትድ ስቴትስ የሰብአዊ መብት ዘገባ

በዘገባዉ መሠረት ኢትዮጵያ ዉስጥ ሐሳብን የመግለፅ፥ የፕረስና የሃይማኖት ነፃነት ክፉኛ ተደፍልቋል። ኤርትራ ዉስጥም የሠብአዊ መብት ሙሉ በሙሉ መገደቡን ዘገባዉ አዉስቷል።

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በየዓመቱ እንደሚያደርገዉ ሁሉ ባለፈዉ የጎርጎሮሳዉያን ዓመት ሁለት ሺሕ አሥራ-ሰወስት በዓለም ሥለነበረዉ የሠብአዊ መብት ይዞታ ያጠናቀረዉን ዘገባ ትናንት ይፋ አድርጓል። ዘገባዉ የኢትዮዮጵያና የኤርትራን ጨምሮ የሁለት መቶ ሐገራትን የሠብአዊ መብት ይዞታ የዳሰሰ ነዉ። በዘገባዉ
መሠረት ኢትዮጵያ ዉስጥ ሐሳብን የመግለፅ፥ የፕረስና የሃይማኖት ነፃነት ክፉኛ ተደፍልቋል። ኤርትራ ዉስጥም የሠብአዊ መብት ሙሉ በሙሉ መገደቡን ዘገባዉ አዉስቷል። ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ ዘገባዉን ይፋ ሲያደርጉ እንዳሉት ሠብአዊ መብት የሚከበረዉ በሕግ-አዉጪዎች ዉሳኔ ሳይሆን እስክንድር ነጋን በመሳሰሉ ቆራጦች ትግል ነዉ። የዋሽግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
አበበ ፈለቀ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ

AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC


No comments:

Post a Comment