Translate

Thursday, October 24, 2013

የአሲምባ ፍቅር (ክፍል ሁለት)

የአሲምባ ፍቅር

ደራሲ- ካህሳይ አብርሀ (አማኑኤል)
ትችት-(ሐተታ)- ሽፈራው
Assimba.org web site ethiopian information
አንባቢ ሆይ : በክፍል አንድ ባጭሩ አንደገለፀሁት ጓድ “አማኑኤል” ጋር በሕብረ ብሔራዊዉ የኢትዮጵያ ህዝባዊዉ አቢዮታዊዉ ሠራዊት (ኢሕአሠ) በወሎ፣ በቤጌምድር እና በትግራይ በብዙ ፈተናና ችግር አብረን ተካፍለናል። ከ30 አመት በኋላም ተገናኝተን ስለ ኢሕአሠ መጽሃፍ ለመጻፍ እንዳሰበ ሲነግረኝ እንደምረዳዉ ቃሌን ሰጥቸ በሰፊው አስተዋጽዖ አድርጌአለሁ ።መጽሐፉ እስኪወጣ ብዙ ጓጉቻለሁ ጠብቄአለሁ። እንደወጣም በተቻለኝ አቅም በብዙ መንገድ ለአንባቢያን እንዲደርስ አድርጌአለሁ። በፌስ ቡኩ(Face book) እና በጉግል(Google) እውነተኛ ታሪክ ሁሉም ሊያነበው የሚገባ በማለት አስተዋውቄአለሁ።ይህን ሁሉ ሳደርግ ግን መጽሃፉን አንብቤ ሳይሆን ታሪኩ አማኑኤል ጋር በስልክ ለብዙ ጊዜ ያወራነዉን ነዉ ከማለት ግምት በመነሳት ነው።
ሌላው ቀርቶ መጽሐፉ ከመታተሙ በፊት አማኑኤል ተመልከተው ብሎ ባለመስጠቱ እንኳን ጥርጣሬም አላደረብኝም። በአጠቃላይ በመጽሀፉ መውጣት የተደሰትኩ መሆኔን ስገልጽ፤በታሪኩ ዉስጥ ሆን ብሎ ወይም ታሪኩን ለአንባብያን ለማጣፈጥ የተጻፉትን አንዳንድ ብረዛና የፈጠራ ተረቶች ስመለከት “የአሲምባ ፍቅር” በበረሃና በከተማ፤ተንገላተዉ መስዋትነት ለከፈሉት መታሰቢያ መሆኑ ቀርቶ ፤ ሌላም ተልእኮ ያለው ሆኖ ነው ያገኘሁት ። በኢሕአሠ ውስጥ በነበረበት ጊዜ በትግሉ የነበረውን መማረር ለትግላችን እንቅፋት ለሆነው ለዘር ክፍፍል ችግር ማወደሻና መኩሪያ መሆኑ በጣም አሳዝኖኛል። ኢህአፓ እና ኢሕአሠ ውስጥ በነበሩበት ወቅት የትግሉ መራራነት ከሚችሉት አቅም በላይ ሆኖባቸው ድርጅቱን በመክዳት፤ንብረቱን ይዘው ከኮበለሉ በኋላ በድርጅቱ ላይ ወቀሳ፤ዘለፋ የሚያቀርቡትን በጣም አጥብቄ እቃወማቸዋለሁ። የኢሕአፓ/ኢሕአሠ ታሪክ በኢትዮጵያዊነታቸዉ ሳያወላዱ ከተለያዩ ህብረ-ብሄር በኢትዮጵያዊነታቸው ብቻ ተሰባስበው በመካከላቸው መጠራጠር ሳይኖር ውድ ህይዎታቸውን ለመላዉ ሕዝብ እኩልነት አሳልፈው የሰጡ ትዉልድ ታሪክ ነዉ። የራሳቸውን ድክመት ለመሸፈን ከጠላት ጋር በማበር ኢህአፓ/ኢሕአሠን ሲዘልፉና ሲያንቋሽሹ ስሰማ ወይም የጻፉትን ሳነብ ፤ በከተማዉ፤ በሸለቆዉ፤ በወንዙ ዳር፤ በበረሀዉ ፤በአሸዋዉና በድንጋዩ ስር የወደቁትን ጓዶች ታሪክ ማናናቅ በመሆኑ ያናድደኛል። “የአሲምባ ፍቅርም “ በአንድ አካሉ ሌሎችን ለማስደሰት በኢሕአፓ/ኢሕአሠ አሰራር ላይ የሰነዘረው በጣም አሳዝኖኛል። ይህንንም ስል ስህተቶች አልነበሩም ለማለት አይደለም። የአማኑኤልን ” የአሲምባ ፍቅር”መጽሀፍ በሚመለከት የኔን የግሌን ትችት በስምንት ነጥቦች በማተኮር አቀርባለሁ።
1ኛ- የወሎ ኦፕሬሽን፤-

No comments:

Post a Comment