Translate

Sunday, February 24, 2013

የደም እንጀራ


ከቴድሮስ ሐይሌ (TADYHA@GMAIL.COM)

“የጤፍ መወደደድ ምክንያቱ ቀድሞ ሊመገብ የማይችለው አርሶ አደር እንጀራ መብላት በመጀመሩ ነው’’ በማለት የተናገረው የሙት ራዕይ ለማስፈጸም ሽር ጉድ እያለ የሚገኘው የከተማ ልጆች በቁሙ የሞተ ሲሉ የሚሳለቁበት ሃይለማርያም ደሳለኝ ፓርላማ ለተባለው የወያኔው አውጫጭኝ የቀድሞ አለቃው መለስ ዜናዊ ስኳርን በተመለከተ በአንድ ወቅት የተናገረውን ምንም ሳይገለበጥ ለጤፍም ችግር መመለሱን ባለፈው ሰሞን ሰምተናል። መጽሃፉ ሙታንን ለሙታን ተዋቸው እንዲል የበድን ጣዖት አምላኪ ወያኔና ጭፍሮቹን ለግዜው እንተዋቸውና ይህንን የሕገ አራዊት አገዛዝ እታገላለሁ የሚለውና በሃገሩ የመኖር ነጻነት አጥቶ የተሰደደው በተለይም በምዕራቡ ሃገራት የሚኖረው ኢትዮጽያዊ ዲያስፖራ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በቀጥታ በሃገር ውስጥ ያለውን ደሃ ወገኑ ላይ ከባድ የኑሮ ክብደት ጫና ሲፈጥር በአንጻሩ የወያኔውን አገዛዝ በውጭ ምንዛሪ እየደጎመ ጥቂት የአገዛዙ ግብርአበር ነጋዴዎችን ኪስ ሲያደልብ ከምናስተውልባቸው የንግድ ዘርፎች ውስጥ ከሃገር ቤት በቀጥታ በአይሮፕላን ተጭኖ ለንግድ የሚቀርበው የእንጀራ መጠን ከቀን ወደቀን እየደገ መምጣቱ ማየት ካስፈለገ በየሃበሻው ሱቅ ያለውን አቅርቦት መታዘብ በቂ ነው።
 (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ)
Addis Ababa restaurant menu

No comments:

Post a Comment