Translate

Wednesday, December 13, 2017

“እንጨርሳቸው፤ አንድም አኙዋክ መትረፍ የለበትም”


  • እነዚህም የህወሓት ነፍሰበላዎች ይፈለጋሉ!
የሰላም ሰዎች የሆኑት አኙዋኮች ከህወሓት ጋር መቃቃር ውስጥ የገቡት ገና ከጅምሩ ነበር። የቀድሞው የአኙዋክ ምክርቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ኦባንግ ሜቶ እንደሚሉት ችግሩ የተያያዘው ህወሓት የጋምቤላን ለም ምድር የራሱ ለማድረግ ከመፈለጉ ጋር ነው። ህወሓት ሥልጣን ላይ እንደተቆናጠጠ የጋምቤላን ብቸኛ ጄኔሬተር በመንቀል ከመውሰድ አልፎ በአሎሮ ግድብ ላይ የነበሩትን ወደ 400 የሚሆኑ ማሽነሪዎች እና የእርሻ መሣሪዎች በምሽት ወደ ትግራይ ነቅሎ ወስዷል ይላሉ አቶ ኦባንግ። በመቀጠልም ተዝቆ የማያልቀውን የጋምቤላን ድንቅ ሃብት በረኸኞቹ ህወሃቶች ለመዝረፍ ውሳኔያቸው አደረጉ

“መሬቴን አላስነካም” በሚለው አኙዋክና ህወሓት መካከል ያለውን መቃቃር አንድ “ዕልባት” ላይ ለማድረስ በሚል አኙዋክን ማጥፋት የህወሓት ቀዳሚ ሃሳብ ሆነ እንደ አቶ ኦባንግ ሜቶ ገለጻ። ጉዳዩን አቅጣጫ ለማስቀየርም ከዚህ በፊት ተነስተው የማያውቁ የጎሣ ግጭቶችን ህወሃት መቆስቆስ ጀመረ። ሸመጋይ መስሎም የመከላከያ ሠራዊት በቦታው ማስፈር ተግባሩ አደረገ። በመጨረሻም “እንጨርሳቸው፤ አንድም አኙዋክ መትረፍ የለበትም” የሚለውትዕዛዝ ወጣ። Let us kill them all! From today forward there will be no Anuak! There will be no more Anuak land! No one will arrest us! Erase the trouble makers!
አዲሱ ለገሰ፣
ስብሃት ነጋ፣
በረከት ስምዖን፣
ኦሞት ኡባንግ ኡሎም (ያኔ የጋምቤላ ደኅንነት ኃላፊ)፣
አባይ ጸሃዬ፣
ሳሞራ ዩኑስ፣
ዮሐንስ ገብረመስቀል (ያኔ የወታደራዊ ስለላ ኃላፊ)፣
አባዱላ ገመዳ ተገኝተዋል።
የዕቅዱ አፈጻጸም ላይ አኙዋኮች እንዲጨፈጨፉ ቀጥተኛ ትዕዛዝ የሰጠው ጸጋይ በየነ (በጋምቤላ የሠራዊቱ ኃላፊ) ሲሆን ፈቃዱ ያገኘው ያኔ የፌዴራል ጉዳይ ኃላፊ ከነበረው ገብረአብ በርናባስ ነበር። የፖሊስ ኃላፊው ታደሰ ኃይለሥላሴም አኙዋኮችን የማስገደል ትዕዛዝ በመስጠቱ ውስጥ ነበረበት። ይህ ሁሉ በማስረጃ የተረጋገጠ መሆኑን አቶ ኦባንግ ያስረዳሉ።
“እንግዲህ ይህ ዘር የማጽዳት ዘመቻ በ1996 ከተካሄደ በኋላ የጋምቤላ መሬት እንደ ካሩቱሪና ሳውዲ ስታር ላሉ ባለሃብቶች በአንድ ዶላር ሒሳብ የተቸበቸበው። ብዙ ጊዜ ለውጭ ባለሃብት ተሰጠ ይባላል እንጂ ከጋምቤላ መሬት 78 በመቶውን የተቀራመቱት ትግሬዎች ሲሆኑ 12 በመቶው ብቻ ነው ለውጭ ባለሃብቶች የተሰጠው። ከዚህ ሌላ ይህ ሁሉ መሬትና ብድር ለትግራይ ተወላጆች ተሰጥቶ የእርሻ ልማት ባለቤቶች ሲሆኑ አንድም አኙዋክ ይህንን ዕድል አላገኘም፤ ይልቁንም ለውሃ ቅርብ የነበሩና በአባቶቻቸው መሬት ላይ የሚገኙትን አኙዋኮች በልማት ሰበብ በህወሃት ተፈናቅለው ወደ ሌላ ቦታ ሰፍረዋል” በማለት ኦባንግ ይናገራሉ።
ኦሞት ኦባንግ ኡሎም ከአገር ኮብልሎ ከመውጣቱ በፊት ከሙስና ጋር በተያያዘ ወንጀለኛ እንደሆነ ሲነገረው “እኔ ከተወነጀልኩና ከታሰርኩ ከእኔ ጋር አዜብ መስፍን አብራ መታሠር አለባት” ማለቱ ይታወሳል።
ከታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ ም ጀምሮ ሟቹ መለስ ዜናዊ በላከው አስገምጋሚዎች ለሳምንት በጋምቤላ በተካሄደ አውጫጪኝ ኦሞት ኦባንግ ኡሎም “የአኙዋክ ተወላጆችን አስጨፍጭፈሃል” የሚል መነሻውና ዓላማው ግልጽ ያልሆነ ጥያቄ ቀርቦለት ነበር። በወቅቱ ግምገማው ላይ የነበሩ እንዳሉት ለዚህ ጥያቄ ኦሞት “እኔ በዚህ ጉዳይ ተጠያቂ ከሆንኩ መሳሪያና ወታደር የሰጠኝ መለስም ይታሰራል” በማለት መልስ ሰጥቶ ነበር።
አስራ አራት ዓመት ቢያልፍም፤ መለስም ወደ ከርሰ መቃብር እንደ ቡሽ ክዳን ተስፈንጥሮ ቢወርድም፤ ኦሞትም ሆነ የህወሓት ነፍሰበላዎች አሁንም ይፈለጋሉ!

No comments:

Post a Comment