Translate

Wednesday, December 6, 2017

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ፈጸምን ያሉትን ጥቃት በተመለከተ ህወሃት ጥቃቱ መፈጸሙን አምኗል

Patriotic Ginbot 7 attack TPLF convoy
የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ህዳር 26 – ለህዳር 27/2010 ንጋት ላይ ለወያኔ (አጋዚ) ጦር ሊውል የነበረ ነዳጅ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ጭነው ከሱዳን ወደ ጎንደር ሲጓዙ በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ በጭልጋ ነጋዴ ባህር በሰነዘሩት ጥቃት ተሽከርካሪዎቹን ሙሉ ለሙሉ ማውደማቸውንና ተሽከርካሪዎቹን አጅበው የነበሩ ወታደሮችን መግደላቸውን ገልጸዋል።

አርበኞቹ ከዜናው ጋር አያይዘው ባስተላለፉት መልእክት “አርበኞች ግንቦት 7 በሀገር ውስጥ በዘረኛው ህወሃት ወያኔ ንብረት ላይና ህዝብን በሚያሰቃዩ ተላላኪ ባንዳና ሆዳም ካድሬ ባለስልጣን ላይ እያደረሱ ያለው ጥቃት ገና ይቀጥላል፡፡” ብለዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ እንዲህ አይነት ጥቃቶች በአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ሲፈጸሙ ለወትሮው ዝምታን የሚመርጠው እና አልፎ አልፎም የሚያስተባብለው ህወሃት ይህ ጥቃት መፈጸሙን አምኗል።
Nigussu Tilahun
አቶ ንጉሱ የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ሃላፊ ናቸው።

No comments:

Post a Comment