Translate

Monday, May 25, 2015

የምርጫው ማግስት መቼ ነው ? ( ሄኖክ የሺጥላ )

የምርጫው ማግስት መቼ ነው ? ( ሄኖክ የሺጥላ )
ታሪክ በሕይወት ዑደትና ሂደት ፣ ድርጊት ና በጊዜ ቀመር ተለክቶ ፣ ነገ ፣ ትናንት ፣ አምና ፣ ካቻምና ፣ የዛሬ ወር ፣ የዛሬ ዓመት ይባላል ። ይህም ታሪክ ድርጊቱ የሆነበትን ወቅት ከመለካት አልፎ ፣ የዘመኑን እድገት ፣ ፍልስፍና ፣ የህዝቦች ስነ ልቦናና ፣ አኗኗር አስረጅ አማዳዊ እና እምርታዊ ፣ ስለ ያኔው በመንገር ዛሬን ምን እንደሚመስል እና መምሰል እናዳለበት መሪ መንገድ ይሆናል ።
ለምሳሌ የአድዋ ድል ታሪክነቱ ትልቅነትን የተላበሰው ፣ ድሉ ቀን ስለነበረው ነው ። ድሉ ስል እና ብልህ አርበኞች ስለነበሩት ነው ። ድሉን የሚመሰክሩ ቋሚ ምስክራን ስለነበሩን ነው ። ድሉ የህዝብ ስለነበረ ነው ። ድሉ በነጻነት እና በባርነት መሃከል ስለተደረገው ትግል ጀግንነት ምስክር ስለነበረ ነው ። የአደዋ ድል ቀን አለው ። የድሉ ማግስትም ይታወቃል ።
የአድዋ ድል መጽሐፍ ተጽፎለታል ፣ የውጭ ሀገር ጸሐፊያን ( እነ አሉላ ፓንክረስት ስለ እኔ አሉላ ገጥመዋል ፣ እነ ጆሴፍ ሬሞንድ ስለ እቴጌ ጣይቱ ጽፈዋል ) የሀገራችን ገጣምያን እና ጸሐፊያን ( እነ ጳውሎስ ኞኞ የማይነጥፍ ብእራቸው ቃላቱን እስኪያጥጥ ተርከውለታል ፣ እነ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ተቀኝተውለታል ፣ ብላቴናው ቴዎድሮስ ካሳሁን የጥበብ ጥንፋሱን እፍ ብሎለታል ፣ እነ ገብረክርስቶስ ደስታ ፣ እነ ፣ እነ ከበደ ሚካዔል ፣ እነ መንግሱ ለማ ፣ ራሳቸው አለቃ ለማ ፣ እነ ሐዲስ አለማየሁ ፣ እና ሌሎቹም ስለ አድዋ ድል መስክረዋል ፣ አመስግነዋል ፣ ዘምረዋል ) ። ለምን አድዋ ድል ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ድሉ ቀን ስላለው ፣ ድሉ ማግስት ስላለው ፣ ድሉ ከድልነት ባሻገር ለታሪክ በረከት ስለነበረ ፣ ድሉ ድል ስለነበረ ።

ይህም የሚያሳየን ቀን ያለው ድል ማግስት እንዳለው ነው ። ሕዝብ ያመነበት ድል ባለ ቀን እና ባለ ክብረ ዓመት እንደሚሆን ነው ። ቀን ያለው ድል ፣ ሕዝብ እንደሚዘክረው ፣ ሁኔታዎች ቢቀያየሩም ፣ የድሉን እውነትነት የሚክዱ ሁኔታዎች ድሉን ትተው እንዲምያልፉ ነው ።
ወደ ወያኔ-ትግሬ ምርጫም ስንመጣ ይህንኑ ነው ያስተዋልነው ። ታሪክ መሆን በማይችል ተጋድሏቸው ውስጥ ተራራ አንቀጥቅጠዋል ፣ ቀን በሌለው ትግላቸው ውስጥ ለሕዝቦች እኩልነት ተጋድለዋል ፣ ማግስት በሌለው ዲሞክራሲያቸው ውስጥ ሃገራዊ የአስተዳደር ለውጥ ምርጫ አድርገዋል ። ያለ ቀን ፣ በቀን ያሸነፉ ፣ ያለ ሕዝብ ምርጫ ህዝብን የወከሉ ፣ ያለ ፍላጎት የተፈልጉ ፣ ያለ ድል ያሸነፉ ፣ ያልተመረጡ ተመራጮች በመሆናቸው የምርጫው ድል ማግስት የለውም ። በየዓመቱ የሚዘክሩት የግንቦት-20 ድል ፣ የወራሪዎች ድል ስለሆነ ፣ ድልነቱ እነሱ እስካሉ ብቻ የሚከበር ነው የሚሆነው ። መስከረም በአንድ ወቅት ከእንቁታጣጣሽነቱ ይልቅ የአብዮት በዓልነቱ ነበር የሚጎለው ፣ ግን መጉላቱ በፍቅር ሳይሆን በጉልበት ስለነበረ እንቁጣጣሽ ብቻ ሕልውናውን እንደያዘ ቀጠለ ። ዛሬም ግንቦት ሐያት የህዝቦች እኩልነት ፣ የዜጎች መብት የተከበረት ቀን ነው ቢሉም ፣ ድሉ ቀን የለውም ፣ ስለዚህ ከውድቀታቸው ማግስት ግንቦት ሃያ አዘቦት ይሆናል ፣ ይረሳል ፣ እንደውም እጅግ የጠላ ቀን ይሆናል ። አድዋ ግን ያኔም ድል እንደሆነ ይቀጥላል ።
አዎ ማግስት በሌለው ምርጫ ያሸነፈ መንግስት ፣ ቀን በሌለው ታሪክ ውስጥ ይኖራል ። አዎ ታሪክ በሌለው መሰረት ላይ የቆመ ስርዓት ፣ ሕዝቡን ሳያውቅ እና ስይረዳ ፣ እንደተጠላ ያልፋል ። ተንቆ እና ተጠልቶ ንጉስ ከመሆን ፣ ተወዶ እና ተከብሮ ባርያ የሆነው ውለታው ታሪክ አለው ። በድንቁርና እና ፍጹም እውቀትን በነጠፈ ማንነት ውስጥ ሆኖ ከፊት ከመቆም ፣ ትቢያ መሆን ዋጋ አለው ። ከምንም በላይ ግን ፣ ታሪክ ቀን እንዲኖረው ፣ ታሪኩ የህዝብ መሆኑ የግድ ነው ።
ይህ የመነሻ እና የመቆጫ ጊዜ ነው ። ይህ የዝምታ እና የተስፋ መቁረጥ ጊዜ አይደለም ። ይህ ትውልድ ነጻ የሚሆን ትውልድ ነው ። ምክንያቱም ይህ ትውልድ ፣ ሲነሳም ድል ሲያደርግም ፣ ሲጥልም ቀን አለው ። ይህ ትውልድ ( In the movie Sarafina the monk said "You are courageous and countless because you are the generation to be free" ) ልበ ደንዳና እና ፍርሃት አልባ ትውልዶች ናችሁ ምክንያቱም እናንተ ነጻ የምትሆኑት ትውልዶች ስለሆናችሁ ይላል ። ከምርጫ ውጤቱ ባሻገር ፣ በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ተስፋ የማደርገው ያንን ነው ።
ሰማያዊ 255 ንብ 500 የሚሉ የምርጫ ውጤቶች አይቻለሁ ። ምርጫው ተጭበርብሯል ከማለት ፣ በሌላ አቅጣጫ ሁኔታውን ካየነው ቢያንስ ሰማያዊ 255 ከጎናቸው ሊቆሙ የሚችሉ ሰዎች አሏቸው ማለት ነው ። ትግል አያልቅም ። ትግል አይቆምም ። ትግል ከቆመ ወይ ነጻ ነህ ወይም ትግል ቀን የለውም ! ቀን በሌለው ትግል ውስጥ ታሪክ የለም !
አሸናፊው 500 ድምጽ ያገኘው የትግሬ -ወያኔ የሚሆነው ፣ 255 ድምጽ አግኝቶ ተሸነፈ የተባለው ሰማያዊ እነዛን 255 ድምጽ የሰጡትን ሰዎች ከጎኑ ማቆም ያልቻለ እንደሆነ ነው ።
ከወንድሜ ዔርምያስ ለገሰ ጋ ስናወራ ፣ የትግሬ ወያኔ በሌለ ታሪክ የትግራይን ሕዝብ በቁጭት አነሳስቶ ለድል እንደበቃ ተነጋገርን ። ( ሀውዜን አንዱ የቁጭት መነሻሻ ታሪክ ነበር ) ፣። እናንተ ( ሰማያዊ ) ባለ ድል ለመሆን ግን የቁጭት ታሪክ መስራት የሚሻችሁ አይመስለኝም ። ሕዝቡን ለቁጭት ማነሳሳት የሚያስችል የተነጠቀ ድል ታሪክ ባለቤት ናችሁና ። ድላችሁ ግን ቀን ይኑረው !
ሄኖክ የሺጥላ

No comments:

Post a Comment