Translate

Wednesday, May 13, 2015

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲንቅናቄ ከውህደቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን አርበኛ ታጋዮችባለፈው እሁድ ግንቦት 2 2007 ዓ.ም ደማቅናታሪካዊ በሆነ ስነ-ስርዓት አስመረቀ፡፡

አርበኞች ግንቦት 7

 አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከውህደቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን አርበኛ ታጋዮች ከትናንት በፊትእሁድ ግንቦት 2 2007 . ደማቅና ታሪካዊ በሆነ ስነ-ስርዓት አስመረቀ፡፡
Ginbot 7 and EPPF
እነዚህ በርካታ ቁጥር ያላቸው የመጀመሪያ ዙር ተመራቂ አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ተከታታይ ወራት የተሰጣቸውን የፖለቲካ፣ የወታደራዊ እናእንዲሁም የመረጃና ደህንነት ስፋትና ጥልቀት ያላቸውን ትምህርቶች በመውሰድ በብቃት የተወጡና በተግባር የተፈተኑ መሆናቸውን የአርበኞችግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ታጋይ ተስፋሁን ተገኘ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግርገልፀዋል፡፡

አርበኛ ታጋዮች በተመረቁበት ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያ የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የሌሎች ደርጅቶች አመራሮችና ልዩ ልዩእንግዶች የተገኙ ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር አርበኛ ታጋይ ማዕዛው ጌጡ ለተመራቂዎችባስተላለፉት መልዕክት ታጋዮች ከውህደቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በመመረቃቸው ታሪካዊና ልዩ እንደሆኑና ነባሩን ሰራዊት ሲቀላቀሉ ተረክበውበረሃ የወረዱበትን ታላቅ የህዝብ አደራ በማናቸውም የነፃነት ትግል ሜዳ ላይ ሙሉ በሙሉ መወጣት ስለመቻላቸው ታላቅ ዕምነት እንዳላቸውናእንዲሁም የህወሓት አገዛዝ ግብአተ መሬት መቃረቡንም ጭምር ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ወታደራዊ መምሪያ ዋና ኃላፊ አርበኛ ታጋይ ኮማንደር አሰፋ ማሩም በበኩላቸውበአሁኑ ጊዜ የህወሓት አገዛዝ ህዝባዊነትና ወታደራዊ አቅም እየተሸመደመደ በእጅጉ እየተዳከመ ባለበት ሁኔታ በተቃራኒው አርበኞች ግንቦት 7 ሰፊየህዝብ ድጋፍ እያገኘ ወታደራዊ ጡንቻውም እየፈረጠመ የመጣ መሆኑን፤ የጭቆና ቀንበር ተሸክሞ አንገቱን የደፋው ህዝብ አለንላችሁ ተብሎ ቀናእንዲል የሚደረግበት ጊዜ መድረሱን እና ከእንግዲህ ወዲህ ማናቸውም ምድራዊ ኃይል አርበኞች ግንቦት ሰባትን ፋጽሞ ሊያቆመው እንደማይችልተናግረዋል፡
ginbot 7
አርበኞች ግንቦት 7

No comments:

Post a Comment