Translate

Monday, May 25, 2015

የአቶ አዳርጋቸው ጽጌ ምስል ለጨረታ ቀርቦ 22,300 የአሜሪካ ዶላር አውጥቷል

ኢትዮጵያ ውስጥ የወያኔን እድሜ ለማራዘም የሀሰት ምርጫ በሚደረግበት ቀን በመላው አለም ተበትነው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን “በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ” (Ethiopian Current Affairs Discussion Forum) ተሰብስበዋል።Ato Andargachew Tsige's Picture
አላማቸው ወያኔ እድሜውን ለማራዘም ከሚያከናውነው የሀሰት ምርጫ የተለየ ነው “አርበኞች ግንቦት 7ን ለማጠናከር ገንዘብ ማሰባሰብ” በእለቱ የአቶ አዳርጋቸው ጽጌ ምስል ለጨረታ ቀርቧል ኢትዮጵያውያኑ በቡድን ተከፋፍለው ጠንካራ ፉክክር ሲያካሂዱ ከርመው በመጨረሻም ለጨረታ የቀረበው የአቶ አዳርጋቸው ጽጌ ምስል 22,300 የአሜሪካ ዶላር አውጥቶ ለአሸናፊው ተሰጥቷል።
የገንዘብ ማሰባሰቡ በቀጥቃ ወደ አርበኞች ግንቦት 7 የባንክ አካውንት ገንዘብ መላክንም ያካትታል።
“በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ” እየተደረገ ያለው አርበኞችን በፋይናንስ የማጠናከር ተግባር “ለሚቀጥሉት ሳምንታትም ተጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል ጉዳዩን የያዙት ታዳሚዎች።
በተመሳሳይ በአውሮፓ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አርበኞች ግንቦት 7ን ለማጠናከር የገንዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራሞችን እያካሄዱ ነው።

እነኝህ ኢትዮጵያውያን በሀገር ቤት ወያኔ እያካሄደ ስላለው ምርጫ የሰሙም አይመስሉም፣ ወይንም ደግሞ ወያኔ በስልጣን እስካለ ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ምርጫ የሚባል ነገር ቀልድ ነው ብለው ስለሚያምኑ ምርጫ ተብዬው እነሱን አይመለከትም።
ዘግይቶ በደረሰን ዜና “አርበኞች ግንቦት 7ን ለማጠናከር የተዘጋጀ ህዝባዊ ሰብሰባ እና የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በሰሜን አሜሪካ ሲያትል ከተማ ይካሄዳል” ዝርዝሩን እዚህ ያገኙታል
ስለ ገንዘብ ማሰባሰቡ የበለጠ ለመረዳት እዚህ ይጫኑ

No comments:

Post a Comment