Translate

Friday, October 24, 2014

የአ.አ ከንቲባ ጽ/ቤት ጠባቂ ፖሊሶች ተታኮሱ

የአ.አ ከንቲባ ጽ/ቤት ጠባቂ ፖሊሶች ተታኮሱ

addis ababa M
ፖሊሶቹ የተታኮሱት በከንቲባው ጽ/ቤት ውስጥ የሚሰሩ ፖሊሶች በነበራቸው ግምገማ በተፈጠረ አለመግባባት እንደሆነ ታውቋል፡፡ ፖሊሶቹ የተታኮሱት ከስብሰባው እንደወጡ እንደሆነም ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡
በከንቲባ ጽ/ቤት ፖሊሶች በተታኮሱበት ወቅት የአትክልት ተራን ጨምሮ በአካባቢው የሚገኘው ማህበረሰብ በድንጋጤ ውስጥ እንደነበርና አብዛኛው ከተኩሱ በኋላ ወደ አስተዳደሩ ቢሮ በማቅናቱ በከንቲባው ጽ/ቤት አካባቢ በርከት ያለ ህዝብ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ጠቅሰዋል፡፡
ፖሊሶቹ በተታኮሱበት ወቅት ገላጋዮች መሃላቸው በመግባታቸው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለና ይህም በግምገማው ወቅት ለገላጋይ ያበቃ አጨቃጫቂ ጉዳይ እንደነበራቸው ያሳያል ተብሏል፡፡ (የዜናው ምንጭ እና ፎቶ: ነገረ ኢትዮጵያ)

No comments:

Post a Comment