Translate

Thursday, October 2, 2014

በተሰዉት እውነተኛ የህዝብ ልጆች ደም በመቀለድ አርበኝነትን ለጊዜያዊ የግል መጠቀሚያና ስሜት ማርኪያ መዋሉን ስንመለከት ውስጣችንን ያመናል

181277_330466667083194_498206512_n
እንደ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አይነት ገዳይ አናሳዎች በሚገዙት ሃገር ዜጎች ሰላም ስለሌላቸው፣ ጠዋት ወጥተው ማታን ለማየት ማረጋገጫ በማጣታቸው፣ የበይ ተመልካች ሆነው ለደናቁርት ሃጥዓን የወረደው የሃብት ማዕበል ከደጃቸው እንኳ ሲያልፍ ማየት እድል ባለማግኘታቸው፣ በከፋቸው ቁጥር የሚተነፍሱባት አደባባይ ተነፍገው ቁጭት በየቤቱ ሲያንገበግባቸው፣ የባሰባቸውም “ምን ይመጣል?” ብለው ለብሶት ብቅ ሲሉ መታነቅ ስለታከታቸው ፣ባህር ኣቋርጠው ከማያውቁት ሃገር ዜጋ እግር ስር መውደቃቸው በአጠቃላይም ስደት ለሚባለው አዋራጅ ስምና ህይወት መዳረጋቸው አይቀሬ ነው።
ቢርበዉም ቢጠማውም በታሪኩ ስደትን የማያውቀው የኢትዮጵያ ህዝብ በመሪሩ የአምስቱ አመት የፋሽስት ኢጣልያ ወረራ ዘመን እንኳ ሃገር ጥሎ አልጠፋም። በዱር በገደሉ ተሰዶ አርበኝነትን ወለደ፣ ለአርበኛው ነጻ ኣውጭ ደጀን ሆኖ አገለገለ እንጂ። ዛሬ ዴሞክራሲ በአሸንዳ በሚንቆረቆርባትና ህዝቦቿ በቀን ስድስት ጊዜ በልተው በሚያገሱባት አዲሲቷ የወያኔ ኢትዮጵያ ተርቦና ተበድሎ የመኖር መብቱን ተነፍጎ መቀመጥ የታከተው ዜጋ፣ የባሰም ቢመጣ ሃገሬን ልልቀቅ ብሎ በባዕድ ሃገር የስደት ካምፖችን አጣቦት እንደሚገኝ ቢታወቅም፣ በኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ስም ወገኔ ናቸው በሚላቸው ዘመን አመጣሽ ብልጣ ብልጥ በላዔ ብሮች እጅ መውደቁ ግን የበለጠ ታሪካችንን ያበላሸውን ያህል ይሰማናል።
በብዙሃኑ ነጻነት ወዳድ ኢትዮጵያዊ የስደተኛ ገንዘብ የራሳቸውንና የመኪናዎቻቸውን ቀፈት ሞልተው የሃሰትን ተስፋ በየመንደሩ በመነስነስ ተራ እውቅናን ለመሸመት የሚሯሯጡትን ወንጀለኛ ግለሰቦች እናውቃቸው ስለነበረ ይህ ወገናችን በቀላሉ የነኝህ ሃሳዊ መሲሆች ሰለባ ሊሆን መቻሉ የበለጠ አሳስቦናል።
EPPF GUARD በሚል እያጭበረበረ የሚገኘው ልዑል ቀስቅስ እና ራሱን ሙሴ ተገኘ እያለ የሚጠራው ግለሰብ ሲሰሩት ከኖሩበት ደረቅ ወንጀል በተጨማሪም በሃሳዊ ፖለቲከኛነታቸውና በድርጅታችን ስምና በሌላቸው የአርበኝነት ገድል በመነገድ የእውነተኛ ሰፋሪ ስደተኞችን የጥገኝነት ማመልከቻ ጥያቄ ውድቅ እንዲሆን ብሎም ለወደፊቱ ከጥያቄ ምልክት ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ላይ መሆናቸው ለእውነተኛው ስደተኛ የብርሃን ግርዶሹ ይታየናል ። እነኝህ ከድርጅታችን ገረገራ ስር የነበሩ ግለሰቦች አለማዊ እንጂ ሃገራዊ ራዕይ ስላልነበራቸው ሰራዊታችን እንዳይደርሱብን ብሎ ያስወገዳቸው ሲሆኑ ሁሉም ሲወገዱና ወደፈለጉበት ሃገር እንዲሄዱ ሲሰናበቱ “ከኤርትራ ለቀን ወጥተናል” በማለት በየአጋር ድረ-ገጾቻቸው ላይ የሃሰት መረጃዎችን በትነዋል። የዜጎችን ትጥቅ ለማስፈታት ሞክረዋል፣ ባገኙት አጋጣሚ ከኛ ያገኙትን መረጃ በየድረ ገጾቻቸው ሳይቀር በመለጠፍ ለወያኔ የእጅ መንሻ አድርገውናል፣ የምንቀሳቀስባቸውን ስፍራዎች ሳይቀር በሳተላይት አስደግፈው ለጠላት ሰጥተውብናል።
ዛሬ በጥቂት ስደተኛ ወገኖቻችን ታጅበው “አባብዬ!” እስከመባል የደረሱት አባይ አዋቂዎች፣ በታሪካቸው አንድም የተሳካ ነገር አከናውነው የማያውቁና የምስኪን ስደተኛ ወገኖቻችንን ፎቶግራፍ በየድረገጾቻቸው ላይ በመለጠፍ መለመኛ እስከማድረግ የደረሱ፣ እርጉዝ በሚያስወርደው ገጻቸውና ገጸ ባህርያቸው በየኢንተርኔቱ የታጋይ ዜጎችን ስም በማጉደፍ ለጠላት ኢላማ ማስደረጋቸው፣ ያስቆጣናል። እየሞትን ባለንበት ድርጅታችን ስም እነዚህን ስደተኛ ወገኖቻችን በማታለል፣ የሃሰት ሰነድ በማዘጋጀት የነዋሪነት ፈቃድ ለማግኘት የሚደረገው ነውር ያሳስበናል። በተሰዉት እውነተኛ የህዝብ ልጆች ደም በመቀለድ አርበኝነትን ለጊዜያዊ የግል መጠቀሚያና ስሜት ማርኪያ መዋሉን ስንመለከት ውስጣችንን ያመናል። በመሆኑም፣ በጀርመን፣ በሲዊስ እንዲሁም በመላው አውሮፓ የምትገኙና፣ በኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ስም በሚነግዱ ግለሰቦች ተወናብዳችሁ፣ ከእጃቸው የወደቃችሁ ስደተኛ ወገኖቻችን በሙሉ በትግል ተፈትኖ፣ የህዝብን ደም ደምቶና ሞቱን ሞቶ፣ ዛሬም ለመኖሩና መስዋዕትነትን እየከፈለ ለመሆኑ የተመሰከረለትን የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርን በመደገፍና በመከተል ታሪካዊ ኢትዮጵያዊ ድርሻችሁን ትወጡ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
የኢህአግ ዓለም አቀፍ ኃይል
EPPF international Force
የኢህአግ ዓለም አቀፍ ኃይል ኢሜል ይጠቀሙ
EPPF International Force contact email :-
በሌላቸው ድርጅት ድርጅት አለን፣ ባልታዩበት አውድማ ጦር አለን፣ እያሉ ዋሽተው የሚያስዋሿችሁንና ለውርደት ሊዳርጓችሁ ታጥቀው የተነሱትን የኢንተርኔት አርበኞች በመታገል የህዝባዊ ትግሉ አካል ትሆኑ ዘንድ ልባዊ መልዕክታችንን ለማስተላለፍ እንወዳለን።
በወንጀለኛ ግለሰቦቹ ላይ እየተሰበሰበ ያለው የሃቀኛ ኢትዮጵያውያኑ ፔቲሽን እናንተን ፈጽሞ የማይመለከት በመሆኑ በጋራ ለሚደረገው አለም አቀፍ የተባበረ ትግል ሙሉ ተሳትፏችሁን ታበረክቱ ዘንድ በወደቁት ሰማዕታትና ዛሬም በየእስር ቤቱ ፍዳቸውን እየበሉ ባሉት ወገኖቻችን ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር አዲስ ባደራጀው አለም አቀፍ ኮሚቴ ጥላ ስር ተሰባስባችሁ፣ ራሳችሁን፣ ድርጅታችሁንና ሃገራችሁን ትታደጉ ዘንድም ስንጠይቅ ማናቸውንም የድርጅታችንን ጉዳይ መወያየት እንዲችሉ ውክልና በሰጠናቸው ከሚከተሉት የየአካባቢው ተወካዮች ጋር በመወያየትና በመገናኘት የህጋዊው ድርጅታችን አካል ትሆኑ ዘንድም በአክብሮት
እንጠይቃለን። በተጨማሪም በምናገኛት ጠባብ ጊዜ ከምናዳብራት ድረ ገጻችንwww.arbegnochginbar.orgብቅ በማለት ገድላችንን፣ ወቅታዊ ዜናችንና መልክታችንን ትከታተሉ ዘንድ እንጋብዛለን።
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!
አንድነት ሃይል ነው!
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር
መስከረም 20/2007

No comments:

Post a Comment