Translate

Tuesday, May 31, 2016

የጃዋር ስኬት እና የፖለቲካ ፈላሻዎች ( ሄኖክ የሺጥላ )

የብሄራዊ ፈተና ምስጢርን ለህዝቡ ቀድሞ በማሳወቅ ( « በማሰረቅ» የሚለው ስለማይጥም ነው ) ፥ ታቅዶ የነበረው የብሄራዊ ፈተና ክንውን ቢያንስ በታቀደለት እለት እንዳይከናወን ስለማድረጉ ብዙ እየተወራለት ነው ። ኦቦ ጃዋር
እርግጥ ጃዋር እጁ ረዝሞ ፥ ከሚኒሶታ አዲስ አበባ ተዘርግቶ ፥ ወያኔን ብስጭት እና ቁጭት ውስጥ የሚጥሉ ጉልህ ነገሮችን እያደረገ ሰለመሆኑ ተደረጉ የተባሉት ነገሮች ገላጭ ሊሆኑ ይችሉ ይሆናል ( መመርመር እንደሚኖርባቸው ባምንም)!! ። ባንፃሩ ግን ጃዋር እና ህቡዕ ድርጅቱ ፥ ፈጠሙ ከተባለው ጉዳይ ጀርባ ምናልባችም በበለጠ አንድ በረጋ እና በሰከነ ልቦና ልናጤን የሚገባው ጉዳይም አለ ። ይኽም ምንድን ነው ፥ የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ በትር ላለፉት 25 አመታት ሲሰቃይ የመኖሩን ያህል ወያኔን በዚህ ኣንድ እና ሁለት አመት ውስጥ ጃዋር እንዴት ሊፈትነው ቻለ? ፈተናውን ሰርቀው ለጃዋር የላኩት ግለሰቦችስ ፥ በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ ፥ ሃገርን ከወያኔ ክርን ለማውጣት በሚደረገው ትግል እና ትንቅንቅ ፥ ካሉት ተቃዋሚዎች መርጠው እና አወዳድረው ፥ ለጃዋር ሲገብሩ ለምን እና እንዴት ብሎ መጠየቁም አግባብነት አለው ባይ ነኝ ።

ከማየው እና ከምረዳው የ ኦቦ ጃዋር ፈተናውን ቀድሞ መለጠፍ እና የፈተናው መሰረዝ ፥ የብዙ ኢ ጃዋር ልቦናዎችን ያማለለ ነገርም መስሎ ተሰምቶኛል ። የጠላታችን ጠላት ፥ ጠላታችንን ስለፈተነው ፥ በአቅሙ ተማርከን ወዳጅ ልናደርገው የምንዳዳ ፥ ወይም ድል ስለራቀን ፥ ከገደሉን በላይ ጥላቻ በሰነቀ ፥ ሞት ባረገዘ ግለሰብ ርዮት ስር ለመውደቅ የምንደፍር ምስኪኖች ነን ብዬ ግን ገምቼ አላውቅም ።
መዘንጋት የሌለብን ጉዳይ ፥ ጃዋር ልክ እንደ ሌሎቹ እየታገለ ነው ። የሚታገልለት ህዝብ ወይም አካል ደሞ እንደ ማንኛውም ህዝብ የወያኔ በትር የደረሰበት ነው ። ከዛ ባለፈ ግን ፥ ወያኔን ከመጣል እና ከማሸነፍ በዘለለ ፥ የኦሮሞ ህዝቦችን መብትም ከማስከበር ባለፈ ፥ በጃዋርኛ ሌላ ጠላት ህዝብ አለ « ሚኒሊክ እና የሚኒሊክ ዘሮች » የሚባሉ ። ከዚህ አንጣር አይደለም ፈተና ወያኔን በሙሉ ሰርቆ ህርጣሌ እቶን ውስጥ የመክተት አቅሙን ቢያገኝ ፥ የመጨረሻ ግቡ የኔን ማንነት እንደ ወያኔ ማጥፋት ስለሆነ በዚህ ሰው ማንኛውም አይነት የፖለቲካ ድል አልደመምም!
ሌላ መማር ያለብን ጉዳይ ፥ በኢትዮጵያዊነት ሃገር ለማዳን ተደራጅተው የሚቧችሩት ያልተሳካላቸው ጃዋር ግን የተሳካለት ( የሚመስለው ) የመዋቅሩም ሆነ የግቡ መሰረት አንድን ብሄር ማዳን ብቻ ሳይሆን በድህረ ከድህነቱ መልስ ትናንት ጨቆኑን ብለው ዛሬ ለመሰባሰባቸው ምክንያት የሆኗቸውን ዘሮችም ማጥፋት ነው ።
ለዚህም ነው ቀልዱን ትተህ አማራ ተደራጅ የምለው። ለኔ የጃዋር ድል የወያኔን የመውደቂያ ቀን መቅረቡን ብቻ ሳይሆን ፥ የአማራንም ሙሉ በሙሉ የመጥፊያ ሰአት መዳረሻ ያሳየኛል ( ይነግረኛል)!
በህይወቴ በዚህኛው አውሬ ድል የምደሰት ፥ በዛኛው አውሬ ስልጣን የምናደድ ግብዝ መሆንን አልሻም ። ከጠላቶቻችን ጠላቶች ድል ይልቅ የወዳጆቻችንን ውድቀት ያንገበግበናል ። በምክንያት እና በትግሉ መሰረታዊ ማንነት ላይ ብዥታ የሌለው ሰው ( አካል ) ፥ በቅፅበታዊ ድሎች ሳይሆን ፥ በዘላቂ ሰላሞች ላይ ያለውን ኢ ረፋድ መድረሻ ያውቀዋልና ፥ ነገሩን ሁሉ በጥሞና ብናይስ ። የወያኔ መውደቅ አስፈላጊ ነው ። የትግሬ ወያኔ ወድቆ የኦሮሞ ወያኔ እንዳይመጣ መጠንቀቅ ደሞ እጅግ አስፈላጊ ነው ።
ጃዋር ፈተና ሲሰርቅ ወይም እንዲሰረቅ ሲያስደርግ ፥ በፍጥነት የጃዋር አራጋቢ በመሆን የፖለቲካው ፍልሰት ፥ ሰው አቅም በማጣቱ አቋም ስለመምከኑ ማሳያ ነው ። ይህ ማለት ፥ ነገ ደሞ ግንቦት ሰባት አንድ ነገር ሲያደርግ ተገልብጦ ግንቦት ሰባት ለመሆን የሚጠይቀው ነገር ግፋ ቢል ተገለባባጭ ስብዕና ነው ፥ እኔ ግን እላለሁ ለምን እና ማንን እንደምትታገል እወቅ!

No comments:

Post a Comment