Translate

Tuesday, May 10, 2016

ይህ ምሁር የት ነው ያለው??

በስዩም ወርቅነህ
የቀድሞ ሟች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከምርጫ 97 ሦስት ዓመት በፊት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሁራን በሰበሰበበት ወቅት ታሪካዊ ንግግር ያደረገው በፎቶ የምትመለከቱት ምሁር ቪድዮ ብዙ ሰው በማህበራዊ ድረ-ገፆች ሲወያይበት፣ ሲያካፍል፣ ሲያዳምጠው ቆይቷል ሆኖም ይህ ምሁር የት እንዳለ ሲጠይቅ አላየሁም። እሱም እንደተነበየው ኢትዮጵያ አዘቅት ውስጥ ስትወድቅ ምንም አይነት አስተያየት ሲሰጥ አልተመለከትኩም። እውን ይህ ምሁር በህይወት አለን? ወይስ መሰሪው አፓርታይዱ ፋሽስት የወያኔ/ኢህአዴግ ስርዓት እንደ ሌሎች ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን አስሮታል? ገሎታል?Confronting Meles Zenawi
ለሁሉም መራጃ ያላችሁ ብታሳውቁን። አልያም ሚዲያዎች ይህን ምሁር ምን ላይ እንዳለ ሙያዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም እጠይቃችኋለሁ። ይህ ምሁር ሃገራዊ ግዴታውን ለመወጣት በድፍረት በመናገሩ የደረሰበት ነገር ካለ የኢትዮጵያ ህዝብ ማወቅ መቻል አለበት።
በህይወት ካለና በሚዲያ መቅረብ የማይችል ከሆነ ፎቶውን በማስደገፍ መረጃ ስጡን!
ታሪክ የሰሩትን በደል ሲደርስባቸው ከጎናቸው መሆን ካልቻልን ሌላ ታሪክ ሰሪ መፍጠር አንችልም!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

No comments:

Post a Comment