Translate

Wednesday, May 11, 2016

ሰበር ዜና..አል ሸባብ የኢትዮጵያን ወታደሮች ጠለፈ


ወደ ባይ_ዶዋ አካባቢ የተወረወሩ የአል_ሸባብ ታጣቂዎች ሶስት የኢትዮጵያን ወታደሮች አግተዉ የአል_ሸባብ ወታደራዊ ጣቢያ ( base ) ወደ ሆነው ኢል_ ቡር ( El_bur ) መዉሰዳቸዉን የሚጥቁሙ መረጃዎች ለወያኔዉ የምስራቅ እዝ ወታደራዊ ደህንነት ደርሰዉታል!
በቅኝት ላይ ተሰማርተዉ ከነበሩ ጥቂት የዝዝዉር ወታደሮች መካከል ሶስቱ መሰወራቸዉን ተንተርሶ ፍለጋ ቢደረግም ምንም አይነት ፍንጭ ጠፍቶ የነበረ ሲሆን ወታደሮቹ በአል_ሸባብ መጠለፋቸዉን የሚጠቁሙ መረጃዎች ከወደ ኢል_ቡር መንደር እንደደረሰዉ የስምሪት አዛዡን ተንተርሶ አንድ የምክትል መቶ አለቅና ሌሎች ተራ ወታደሮች መጠለፋቸዉን በሶማሌያ የኢትዮጵያዉ ጦር አዛዥ ኮነሬል የማነገብረ ማርያም ለምስራቅ እዙ አሳዉቋል።
በታህሳስ ወር 2006 እ.ኤ.አ የተመሰረተዉ አል_ሸባብን ማጥፋት ማለት መላዉ የሶማሌያን ሕዝብ ማጥፋት ማለት ነዉ! ያሉት ምንጫችን አክለዉ አል_ሸባብ ማለት እጅግ ጨካኝና አረመኔ የጥፋት ቡድን ነዉ። ከአልሸባብ ጋር የሚደረጉ ትንቅንቆች በሙሉ ከሶማሌያ ህዝብ ጋር የሚደረግ ትንቅንቆች ናቸዉ። ምንም እንኳን በዚህ በሶማሌያ ያሉት የኢትዮጵያ ወታደሮች መጠን ቢቀነስም የአል_ሸባብ ድንገተኛ ጥቃት ግን ፈጽሞ አልቀነሰም አሁን የተጠለፉት ወታደሮቻን የሚጠብቃቸዉ የከፋ ሞት ብቻ ነዉ ብለዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )

No comments:

Post a Comment