Translate

Friday, August 23, 2013

ሆስኒ ሙባረክ በነጻ ተፈቱ

ኢ.ኤም.ኤፍ. – በዛሬው እለት በ እስር ላይ የነበሩት የቀድሞው የግብጽ ፕሬዘዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከእስር በነጻ ተፈተዋል። የ85 አመቱ የቀድሞው ፕሬዘዳንት ከአንድ አመት በላይ በ እስር ላይ የቆዩ ቢሆንም፤ አሁን ግን ፍርድ ቤት ቀርበው፤ ዳኛው በነጻ እንዲሰናበቱ አድርጓል። ፍርድ ቤቱ የቀድሞውን ፕሬዘዳንት በነጻ ሲያሰናብት፤ ወታደራዊው አመራር ደግሞ ፕሬዘዳንቱን፤ በሄሊኮፕተር ጭኖ ወደ ጦር ኃይሉ ሆስፒታል ወስዷቸዋል።

እንደዜናው ምንጭ ከሆነ፤ የቀድሞው ፕሬዘዳንት ቀጣይ ዘመናቸውን ወታደራዊ ጥበቃ እየተደረገላቸው፤ በነጻነት ከቤተሰቦቻቸው እና ከወዳጆቻቸው ጋር እየተገናኙ እንዲኖሩ የሚደረግ መሆኑ ታውቋል።ግ
ሆስኒ ሙባረክ ከእስር ሲፈቱ ደጋፊዎቻቸውን በደስታ የገለጹ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ህዝቡ እና የመሃመድ ሙርሲ ደጋፊዎች ቅሬታቸውን አሰምተዋል። የአሜሪካ መንግስት በሆስኒ ሙባረክ መፈታት ጉዳይ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም፤ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰኣት ድረስ ምንም የተባለ ነገር የለም። ሆኖም ነገ አርብ ሊነሳ የሚችለውን ስጋት በመፍራት፤ አሜሪካ ዜጎቿ ከቤት እንዳይወጡ አስጠንቅቃለች።
የቀድሞው የግብጽ ፕሬዘዳንት ሆስኒ ሙባረክ

No comments:

Post a Comment