Translate

Wednesday, August 31, 2016

ሰበር ዜና! የትግራይ ወጣቶች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ትእዛዝ ተሰጠ


የትግራይ ወጣቶች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ትእዛዝ ተሰጠ 
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱ እና ከፍተኛ የህወሓት ሹማምንቶች እምነት የሚጣልባቸው የፓርቲው ወጣት አባላትን ስብስበው ጠንካራ ትእዛዝ አስተላለፉ::

"በእናቶቾቻችሁ፥ በአባቶቻችሁ፥ በእህት፥ ወንድሞቻችሁ ደምና አጥንት ማንነታቸሁ ተከብሯል:: ደርግ ወንበዴ እያለ ሲጨፈጭፈን መስዋዕትነት ከፍለን በሰላም የምትኖሩበት፥ የምትማሩበት፥ የምትሰሩበት እና በክብር ወጥታችሁ የምትገቡበት ናጽነት አግኝተናል::
አሁን ግን የጥፋት ኃይሎች በሻእቢያ እና ግብጽ በመታገዝ ደርግን መልሰው ሊያመጡብን ትግራዋይ ላይ ግልጽ ጦርነት አውጀዋል:: ስለዚህ ይህን የመመከት ኃላፊነት በእናንተ ወጣቶች ላይ ተጥሏል::
ወላጆቻችሁ ትምክህተኞችን ጠባቦችን ደምስሰው በኢትዮጵያ ሰላም ልማት እና ዲሞክራሲ አንዳሰፈኑት ሁሉ እናንተም አኩሪውን ታሪክ የመድገም ግዴታ አለባችሁ:: አለበለዚያ የተጋሩ ህልውና አደጋ ላይ ይወድቃል ብሎም ከላይ የሻእቢያ ከታች የትምክህተኞች ጥቃት መፈንጫ ሆኖ እንደ ሕዝብ የመቀጠል እድል የማይታሰብ ይሆናል:: በተለይ በ አሁኑ ሰዓት በአማራ ክልል ሁከት በተጋሩ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ይህንኑ ያመላክታል::
ይህን አውቃችሁ ህወሓትንም ትግራይንም ከጥፋት በማዳን የተጋሩን ቀጣይነት አረጋገጡ:: ባለራዕዩ መሪያችን መለስ ዜናዊ የጣለብንን አደራ እንወጣ::በእናንተ ፍጹም እምነት አለን::"
በትላንትናው ዕለት ገዢው ስርዓት በግልጽ አማራ ክልል በወታደራዊ እዝ ስር እንደሚሆን በመግለፅ በከባድ መሳሪያ የታገዘ መከላከያ ሰራዊት ወደስፍራው አሰማርቷል ::
ኦሮሚያ ክልል አብዛኛው ክፍሉ በህወሓት ሰራዊት የታጠረ መሆኑ ይታወቃል::
የህወሓት ትእዛዝ ፈጻሚ የሆነው ብአዴን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አያፈነገጠ በመምጣቱ እና ሕዝባዊ ንቅናቄው ላይ የሚጠበቀውን የኃይል እርምጃ ባለመወሰዱ በኦህዴድ አመራሮች ላይ እንደደረሰው የመባረር እጣ የሚገጥማቸው ባለስልጣናት ይኖራሉ:: በተጨማሪ የብአዴን እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ በህወሀት ቁጥጥር ስር ይሆናል

No comments:

Post a Comment