Translate

Saturday, August 13, 2016

በደብረማርቆስ ንግድ ቆሟል | አልሞ ተኳሾች ብዙ ሰው አቁስለዋል

በደብረማርቆስ ንግድ ቆሟል | አልሞ ተኳሾች ብዙ ሰው አቁስለዋል
(ዘ-ሐበሻ) በጎጃም ደብረማርቆስ የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር አልሞ ተኳሽ (ስናይፐር) ፖሊሶችን መጠቀሙ ተሰማ:: እነዚህ አልሞ ተኳሾችም ያቆሰሏቸው ስዎች ቁጥር ከ20 እንደሚበልጥ ዘ-ሐበሻ በስልክ ያነጋገረቻቸው የደብረማርቆስ ነዋሪዎች ገልጸዋል::

የደብረማርቆስ ሕዝብ የሚነዛበትን ፕሮፓጋንዳ ሳይሰማ; እንዲሁም የመንግስት ባለስልጣናት ከሐሙስ ጀምሮ ሰልፍ እንዳይወጣ ሲያስፈራሩት ቢቆይም የነርሱን ማስፈራራት ከምንም ሳይቆጥር ዛሬ ተሰባስቦ በመውጣት ተቃውሞውን ቢያሰማም ከአራት አቅጣጫ የወጣውን ሕዝብ በአንድ ላይ እንዳይሰባሰብ የትግራይ ነጻ አውጪ ስርዓት ወታደሮች ሕዝቡ ላይ በመተኮስ እንዳይገናኝ አድርገውታል::
የደብረማቆስ ነዋሪ ሰልፈኞች በኦሮሚያ እየፈሰሰ ያለው ደም የወንድሞቻችን ነው; ወልቃይት አማራ ነው; በጎንደርና በባህዳር የተፈጸመው ግድያን እናወግዛለን; የፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞች ይፈቱ; የሕወሓት መንግስት አይገዛንም የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች ተሰምተዋል::
“ደብረማርቆስ በተኩስ እየተናጠች ነው:: ሰላማዊ ሰልፉ ወደ ድብደባ ተሸጋግሯል” ያሉን ዘ-ሐበሻ ያነጋገረቻቸው የደብረማርቆስ ነዋሪ በከተማው የአምቡላንስ ድምጽ ነው የሚሰማው ብለውናል:: በከተማዋም ምንም አይነት የንግድ እንቅስቃሴ እንደሌለና ሱቆችም መዘጋጋታችውን ገልጸውልናል::

No comments:

Post a Comment