
አርባ ምንጭ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ አካባቢውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ታወቀ፡፡ ህወሓት በሁመራ የሚገኙ 40 የንግድ ቤቶችን ራሱ በስውር በእሳት አቃጥሎ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ለማላከክ እየሞከረ እንደሚገኝ ከውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን የተገኘው መረጃ አጋለጠ፡፡






በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ትግል ታሪክ ውስጥ ባጠቃላይና በተለይ ደግሞ ህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ስልጣኑን በተቆጣጠረባቸው ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ውስጥ ህወሓት/ኢህአዴግን እንቃወማለን በሚለው ወገን ገንነው የመጡ ሁለት አፍራሽና ኋላቀር የፖለቲካ አዝማሚያዎች (trends ) አሉ። ከነኝህ ውስጥ አንደኛው ራስን በፖለቲካ አመለካከት ዙሪያ ከማሰባሰብ ይልቅ በጎጥና በዘውግ ደረጃ የመመልከትና ሀገራዊ ፖለቲካን በደም ቆጠራ የመመንዘር አባዜ ነው። ሁለተኛውና ከዚሁ ያልተናነሰው ችግር የፖለቲካ ድርጅት በመሰረታዊ ያመለካከት መርሆች ዙሪያ ሰፋ ያለ የማህበረሰብ ክፍልን የማሰባሰቢያ ድንኳን መሆኑ ቀርቶ፤ በስራ ሳይሆን ድንገተኛ አጋጣሚን በመጠበቅ ትርፍ ለማጋበስ በሚቋምጡ ሰነፍ “ነጋዴዎች“ የተቋቋሙ ሩቅ የማይሄዱ የንግድ ድርጅቶች ይመስልበ ተግባር ምንም የማይፈይዱ ”የፖለቲካ ድርጅቶች“ እንደ አሸን የመፍላታቸው ፈሊጥ ነው። እነኝህ ሁለቱም አዝማሚያዎች የህወሓት/ኢህአዴግን ህይወት ከማራዘም አልፈዉ ማህበረሰቡን ወደሚመኘው እውነተኛ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት አንድ ጋት እንኳን ፈቀቅ አላደረጉትም። ይልቁንም ዴሞክራሲን የሚናፍቁ ታጋዮች ተሰባስበውና ተጠናክረው ስርዓቱን ከመግፋት ይልቅ በግለሰብ ደረጃ ወይንም በትናንሽ ቡድኖች በመሰባሰብ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች በስርዓቱ በቀላሉ እየተመቱ ብዙ ታጋዮች ለሞት፤ ለስቃይና ለእስር ተዳርገዋል። አሁንም እየተዳረጉ ነው።




ስለ ቀድሞው ጠቅላይ ምስትር መለስ ዜናዊም ሆነ በአንድ ቅኝት ሲያዘፍኑዋቸው ስለነበሩ ፓርቲዎች እንዲሁም ከተከታይነት ያለፈ ምንም ፋይዳ ስላልነበራቸው ሹማምንት ብዙ የተባለ ቢሆንም ዛሬም አድናቂ ነን ባዮች እወደድ ባዮች በመንግሥታችሁ አትርሱን ባዮች ወዘተ ታላቁ ባለ ራዕዩ ወዘተ ከማለት አልፈው አቶ መለስ ለኢትዮጵያና ለህዝቧ ሲሰሩና ሲባትሉ እንደሞቱ ሊነግሩን ይዳዳቸዋል፡፡