Translate

Wednesday, March 11, 2015

የ119ኛው የአድዋ ድል በዓል በኖርዌይ ስታቫንገር በደመቀ ሁኔታ ተከበረ

119ኛው የአድዋ ድል በዓል በኖርዌይ በስታቫንገር ከተማ እሁድ የካቲት 19.2007 .  ቁጥራቸው በርከት ያሉ ኢትዮጵያን በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተከበ ዋለ፡፡ Description: C:\Users\tesfalem\Downloads\11065444_10204886873349986_1299872600_o.jpg

ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የስታቫንገር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባዝጋጀው 119ኛው የአድዋ ድል በአል ላይ ከተለያዩ የከተማው አካባቢ የተሰባሰቡ ኢትዮጲያዊያን የተገኙ ሲሆን የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስብሳቢ  በአሉን በተመለከት ስፊ የመክፈቻ  ንግግር አድርገው በአሉን አስጀምረዋል፡፡
በማስከተልም በቅደም ተከተል የድርጅቱ(የቅርንጫፉ) አባላት የአድዋን ድል በአል ታሪካዊ ክንውንና አሁን በሃገራችን ያለውን ዘረኛው የወያኔ ፋሽስት ቡድን በሃገራችንና በሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን መረን የለቀቀ ግፍና ሰቆቃ በድምጽና በምስል በተደገፈ ማስረጃ እጅግ ማራኪ ብሆነ መልኩ ለታዳሚው አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም የማርች  8   የሴቶች በአልን ምክንያት በማድረግ በዚሁ ሁለት መሰረታዊ ክብረ በአላትን ለማክበር የታድሙ ሴት እህቶቻችን (የጣይቱ ልጆች)የአደዋን ሴት አርበኞች ገድልና በአሁኑ ወቅት በሃገራችን ኢትዮጲያ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ዘርፈ ብዙ የሰብአዊ የመብት ጥሰቶችን በማውሳት የዘመናችንን ሴት የነጻነት ታጋዮች ሲዘክሩ አምሽተዋል፡፡እጅግ መሳጭ በሆነና ቀልብን ሰቅጦ በያዝ ትንታኔ ታዳሚውን አስደምመው አምሽተዋል፡፡ በማስከተልም በሃገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

``ዘራፊ ዘራፍ የማለት ሞራል የለውም !!

(አሌክስ አብርሃም)
አንድ የገባኝ ነገር የቱንም ያህል በወኔ የሚከበር የሚያኮራና የእውነት ታሪክ ቢኖር ዘራፊ ዘራፍ የማለት ሞራል የለውም !! ዘራፍ ባዮችንም ይፈራል ይጠላል !! የእውነትና የነፃነት ልጆች ግን አንገታቸውን ቀና አድርገው የተደረገላቸውን በተደረገላቸው ልክ ይመሰክራሉ !! ታሪክን ማድበስበሻ ቁርሾ አነፍንፈው አይፈለጉምዛሬን ለማድመቅ የትላንትን ብርሃን ከትውልድ ፊት አይከልሉም ! ይሄንኑ ነው ያደረግነው ዛሬ !! በአደባባይ ቀና ብለን እንዲህ አልንከእናተ በኋላ የተሰራው በጎ ነገር ሁሉ ከእኛም በኋላ የሚሰራው ማንኛውም ታላቅ እና ታናሽ ነገርየእናተ መሰረት ነው !!

የትኛውም የአገሪቱ ክፍል የትኛውም የአገሪቱ አፈር ሰማይና አየር ላይ የከፈላችሁልን የፍቅርና የክብር እዳ በክብር ተፅፎ ይነኖራል !!ኢትዮጲያዊነታችንን ካደፈ ውርደት አንገት ከሚያስደፋ የታሪክ ጭቅቅት በደማችሁ አጥባችሁ የሰጣችሁን እናተ ናችሁ !! ክብር ለአድዋ ጀግኖችክብር ስለዚች አገር በተግባር በሃሳብ በመንፈስ ሁሉ ቀናውን ላሰቡ ! ቀናውን ለከፈሉ ንፁኃን ጀግኖች ሁሉ ! 
መልካም የአድዋ በዓል !! ’’
ድል ለኢትዮጲያ ሕዝብ!!!
Ftih_lewegen

No comments:

Post a Comment