Translate

Friday, December 19, 2014

ይልቅ ወሬ ልንገርህ ስለ ሜሮን ጌትነት ግጥምና ውዝግቡ

ቁም ነገር መፅሔት ቁጥር 193 ታህሣስ 2007
ለሶደሬ
ስለ ሜሮን ጌትነት ግጥምና ውዝግቡ
መቼም ሰሞኑን በማህበራዊ ድረ ገፆች ላይ ህዝቡ እየተቀባበለው ያለውን ‹አትሂድ› የሚለውን የሜሮን ጌትነት ግጥም አልሰማሁም አትለኝም? ወር በገባ በመጀመሪያው ረቡዕ በራስ ሆቴል በሚቀርበው የግጥም ምሽት ላይ ያቀረበችው ግጥም የመንግስት ደጋፊና ተቃዋሚዎችን የጦፈ ውዝግብ ውስጥ ከቷቸዋል አሉ፡፡
እናስ? እናማ አንዳንዶች ግጥሙ የሜሮን አይደለም፤ ሜሮን የሌላ ሰው ግጥም ነው ያነበበችው ሲሉ ሌሎች ደግሞ ግጥሙ የራሷ ነው ለዚሁም ማስረጃ የሚሆነው ከሳምንት በፊት ሜሮን ራሷ አንድ ከፍተኛ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን መ/ቤት ባለስልጣን ቢሮአቸው ድረስ አስጠርተዋት‹በእርግጥ ይህ ግጥም ያንቺ ነው? › ብለው ጠይቀዋታል አሉ፡፡

እናስ? እናማ ግጥሙ የራሷ እንደሆነ ስትገልፅላቸው በግጥሟ ውስጥ የጠቀሰቻቸው ሀሳቦች በግልፅ ከመንግስት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ጋር የሚላተሙ እንደሆኑ በመግለፅ በቅርቡ በሚዘጋጅላት አንድ የሬዲዮ ጣቢያ/ዛሚ?/ ላይ ለቃለ ምልልስ ላይ ቀርባ እንድታስተባብል ጠይቀዋታል አሉ፡፡ እናስ? እናማ ሜሮንዬ ‹ወይ ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ!› ከሬዲዮ ጣቢያው በተደጋጋሚ ቢደወልም የሜሮን ስልክ ዝግ ሆኖ ይከርማል፡፡
በዚህ መሀል የህዳር 29 የብሔር ብሔረበሰቦች ቀን ሊከበር ነው ሲባል የህዳሴው ግድብ ከሚሰራበት ቤንሻል ጉል ክልል አሶሳ ስታዲየም በዕለቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በሚገኙበት ሲከበር ‹መድረኩን ማን ይምራ?› የሚል ጥያቄ ይነሳል፡፡ አስቀድመው በጀት አስመድበው በዓሉን ለማክበር ወዲያ ወዲህ ከሚሉት አርቲስቶች ጋር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን ጋር ስብሰባ ይቀመጣሉ አሉ፡፡
 እናስ? እናማ የዕለቱን መድረክ ማን ይምራ ሲባል ‹ሜሮን› የሚል ስም ይነሳል፡፡ ዋንጫውን ከክልል ክልል ይዘው በማስጎብኘት ላይ ካሉት አርቲስቶች መሀከል ሁለቱ የሜሮንን ኢ ልማታዊ ግጥም በመጥቀስ ‹መንግስትን በግልፅ እየተቸች እንዴት?‹ ብለው ሽንጣቸውን ገትረው መቃወም ይጀምራሉ አሉ፡፡ እኛ ከመንግስት ጋር በመስራታችን ውግዘት እየደረሰብን እንዴት በግልፅ የሚቃወሙትን መድረክ ላይ እናወጣለንም ብለዋል አሉ፡፡
እናስ? ዳኛው የፌዴሬሽ ምክር ቤት አፈ ጉባኤው ምን ቢሉ ጥሩ ነው? በሜሮን ግጥም የተነሳ ዲያስፖራው ከፍተኛ መነቃቃት ላይ በመሆኑ ይህንን መነቃቃት ላይ ውሃ መቸለስ የምንችለው ሜሮንን ስናሰራት ብቻ ነው አሉ ተባለ፡፡ እናም የሜሮን ስልክ ለዚህ በዓል እንደተፈለገ ሲያውቅ በራሱ ጊዜ ተከፈተ አሉ እና ወደዚያው አመራች፡፡›
የአምስት ወር ነፍሰ ጡር የሆነችው ሜሮን በሬዲዮ የግጥሙን መልዕክት ‹አስተባብይ› በተባለች ማግስት ወደ እጮኛዋ ጋር አሜሪካ ሄዳ ልጇን ለመገላገል ትኬት መቁረጧ ሲታወቅ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዘወትር እሁድ ከሚቀርበው ዳና ድራማና ዘወትር ሐሙስ ከሚተላለፈው የኢቲቪ የጥያቄና መልስ ፕሮግራም ላይ ትገለላለች ተብሏል፡፡ በተለይም ከዳና ድራማ ላይ ዋና ገፀባህሪ ሆና ከመጫወቷ አንፃር ድራማው ክፍተት ሊኖረው እንደሚችል የተሰጋ ቢሆንም በድራማው ላይም ነፍሰጡር መሆኗን መነሻ በማድረግ በድራማው ላይ ከደረሰባት አደጋ ጋር በተያያዘ ‹ለህክምና ወደ ውጪ ሀገር ሄደች› በሚል ታሪክን ለማስቀጠል እየተሞከረ እንደሆነ ይወራል፡፡ ከሁለት ሳምንት በኋላ ወደ አሜሪካ የምትሄደው ሜሮን ‹አትሂድ› በሚለው ስደትን በሚሰብከው ግምሟ እንዲህ ትላለች..
አትሂድ አትሂድ ብዬህ ጮኬ ነበር ብዕሬን አንስቼ
የሀገርን ጥቅም የወገንን ፍቅር በአክብሮት አይቼ
እዚህ ለፍተህ ስትኖር በሀገርህ አፈር ላይ
በርታ ጎብዝ የሚል ያንተን ልፋት የሚያይ
አንዳችም ሰው የለ
ህዝቡ ውጪ አምልኳ ልቡ ተንበርክኳል
ለሀገር ስታነባ በጥቅም ይለካል
በነፃ ያላበህ በዶላር ይለካል… ብል ቻዎ....

No comments:

Post a Comment