Translate

Wednesday, January 22, 2014

በኢትዮያ እና ሱዳን ድንበር ዙሪያ ወቅታዊና ትምህርታዊ የውይይት መድረክ (ሰማያዊ ፓርቲ )

Blue Party Ethiopia



ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮ ሱዳን ጉዳይ ላለፉት ወራት ነገሩን በቅርበት ሲከታተል የቆየ ሲሆን በጉዳዩም ላይ አቋሙን በመግለጫ መልክ ማውጣቱ ይታወሳል አክሎም ፊታችን ጥር 25 ቀን ለቦታው ቅርበት ካላቸው ከተሞች አንዷ በሆነችው ጎንደር ከተማም ተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱ ይታወቃል፡፡
ከነዚህ አንቅስቃሴዎች በተጨማሪም ድንበራችንን ጉዳይ በተመለከተ በተጨባጭ መረጃ በህብረተሰቡ ውስጥ ግንዛቤ ይፈጠር ዘንድ ትምህርታዊ ውይይት መድረክ ያዘጋጀ ሲሆን በዝግጅቱ ላይም በዘርፉ ለረጅም አመታት በመስራት የሚታወቁት የረጅም ጊዜ የጆግራፊ ባለሞያ የሆኑት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ድንበሩን በተመለከተ ሰፋ ያለ ትምህርት ይሰጣሉ፡፡ እርስዎም በዝግጅቱ ላይ እንዲሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል!
ቀን፡- ቅዳሜ ጥር 17 ቀን
ሰዓት፡- ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ፡- በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት
(የጽ/ቤታችን መገኛ ከካሳንችዝ ቶታል ወደ አዋሬ በሚወስደው መንገድ ላይ “የአዋሬ አጥቢያ ወንጌላውያን ቤተክርስቲያን” ጋር ሲደርሱ ወደ ቀኝ በሚያስገባው መታጠፊያ 50 ሜትር ላይ ነው)

No comments:

Post a Comment