Translate

Sunday, January 12, 2014

ታሪካዊ የተቃውሞ ድምጽ ጥሪ! ዳር ድንበር ሲቆረስ ዝም ብለን አናይም!

ጸረ ኢትዮጵያ የሆነዉ ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ አባቶቻችን በደማቸዉ አስከብረዉ ያቆዩትን ያገራችንን ዳር ድንበር ለግዚያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሲል አሳልፎ እየሰጠ ያለ መሆኑ ለሁላችንም ግልጽ ነዉ። ሰሞኑን የሱዳኑን የአልበሺር ስርኣት ለማስደሰት እና ተባባሪው ለማድረግ ኢትዮጵያዊ ዜጎቻችንን ለዘመናት ከኖሩበት ቀያቸው እያፈናቀለ 1200 ኪ.ሜ. የሚሆን የድንበር ክልል ለመለገስ እየተዘጋጀ ይገኛል። በመሆኑም ይህ ሀገርን የመሸጥ፤ የመክዳት ድርጊት በኢትዮጵያ ህዝብ እና በታሪክ ተቀባይነት እንደማይኖረው እንዲሁም ይዋል ይደር እንጂ ህዝባችን ይህን ዳር ድንበር እንደሚያስመልስ ለአለም ህብረተሰብ በዋናነትም ለሱዳን ህዝብ ለማሳወቅ በሱዳን ኤምባሲ በመቀጠልም በወያኔ ኤምባሲ ፊት ለፊት በተጠራዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመገኘት የዜግነት ታሪካዊ ግዴታችንን እንወጣ። ድምጹን ማሰማት ለማይችለው ህዝባችን እና በግፍ ለሚፈናቀሉት ወግኖቻችን ድምጽ እንሁናቸው።

TPLF regime is to hand over legitimate Ethiopian territory to Sudan

No comments:

Post a Comment